እስልምና እና ነፃነት الحرية في الاسلام

n00060764 b 150x150 እስልምና እና ነፃነት     الحرية في الاسلام

እስልምና እና ነፃነት   الحرية في الاسلام

ነፃነትን የማይፈልግ ማን አለ? በርግጥ ወንድም ይሁን ሴት በአጠቃላይ የሰው ልጅ ሆኖ ‘ነፃነትን አልፈልግም’ የሚል ማንም የለም። ፍጡር ሁሉ ነፃነትን ይፈልጋል። ያለው ይንከባከባል፤ የሌለው ይናፍቃል። ሌላው ቀርቶ እንሠሣትም እንኳ ነፃነትን ይፈልጋሉ። ለምሣሌ – እስቲ አንዲት በራሪ ወፍ እንያዝና ትንሽ መውጫ ቀዳዳ ብቻ በማበጀት ጠባብ ጎጆ ውስጥ እናድርጋት። ወፏ ወጥታ ለመብረር ስትጣደፍ እናስተውላለን።

በጎጆዋ ውስጥ ታሥራ ለዘላለም መኖርን አትፈልግምና። አንድ ድመት እንውሰድና በሩን በመዝጋት ከአንድ ጠባብ ቤት ውስጥ እናኑራት- ወዲያውኑ ወደ በሩ በመሄድ መውጫ በሩን ስትጭርና ስትጮህ እንመለከታለን። በተቆለፈ በር ውስጥ ተዘግቶባት ዘወትር መኖርን አትሻምና።

ነፃነት በቅርቡ የመጣ የዘመኑ ሰው ሀሣብ አይደለም። ባለቤቶቹም ምእራባውያን አሊያም ምሥራቃውያን ማህበረሰቦች አይደሉም። ነፃነት ዓለማቀፋዊ የሆነ ሀሣብ ነው። ለራሱም ሆነ ለሌላው ማህበረሰብ ነፃነትን የማይፈልግ ህዝብ አለ ብሎ ማሠብም ስህተት ነው። ሆኖም ግን አንድ እውነታ አለ፤ በምእራቡም ሆነ በምሥራቁ የዓለማችን ክፍል የሚኖሩ አንዳንድ ህዝቦች ነፃነትን ለራሣቸው ብቻ እንጂ ሌሎች እንዲኖራቸው አይፈልጉም። ይህ በርግጥ ትልቅ አፈናና ጭቆና ነው።

እስልምና በነፃነት እንድንኖር፤ ያለ አንዳች ፍራቻ በእኩልነትም እንድናስብና እንድንመኝ ሌሎችም ነፃነት ያገኙ ዘንድ እንድንሠራ ያስተምረናል። ነፃነትና እኩልነት በጥብቅ የተሣሠሩ ነገሮች ናቸው። በእስልምና ዓይን ለአላህ ባላቸው የፍራቻ ደረጃ ካልሆነ በቀር የሰው ልጆች ሁሉ እኩል ናቸው። በመሆኑም ከነፃነት በፊት በእኩልነት ዙሪያ ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል። እኩልነትን ሣንተገብር ነፃነትን መተግበር አይታሠብምና። ማስታወስ የሚገባን ሌላው ነጥብ በኢስላም ውስጥ ነፃነት ስንል የምንወዳቸውንና ስሜታችን የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ አሣድዶ መሥራት ሣይሆን ጥሩ ነገሮችን መርጦ የመሥራት ነፃነት መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል። በዐረብኛ “ሁር”- ነፃ የሚለው ቃል ነፃነትን ብቻ ሣይሆም ክብርንም ያመለክታል። “የሰው ልጅ ነፃነት ይከበር” ስንልም ለሰብኣዊው ፍጡር ተገቢው ከበሬታ ይሠጠው ማለታችን ነው። በአጠቃላይ መልኩ እስልምና ነፃነትን ያበረታታል፣ ይደግፋል፣ ለነፃነትም ያነሳሳል። እስልምና ለሰው ልጅ መከበር ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ የነፃነትና የክብር ሃይማኖት ነው። ሰዎችን አእምሮአቸውንና መንፈሣቸውን ክፍት በማድረግም ላለሙት ግብ እንዲደርሱ ያግዛቸዋል። ነፃነት ትልቅ ክብር ነው። ከጭቆናና ውርደት ተላቆ ክብርን እስካላገኘ ድረስ የሰው ልጅ ነፃ ነው ማለት አይቻልምና።

اللَّهُ وَلِيُّ الَّذِينَ آمَنُوا يُخْرِجُهُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَوْلِيَاؤُهُمُ الطَّاغُوتُ يُخْرِجُونَهُم مِّنَ النُّورِ إِلَى الظُّلُمَاتِ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ [٢:٢٥٧]

አላህ የነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ነው። ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል። እነዚያም የካዱት ረዳቶቻቸው ጣዖታት ናቸው። ከብርሃን ወደ ጨለማዎች ያወጧቸዋል። እነዚያ የእሣት ጓዶች ናቸው፤ እነርሱ በውስጧም ዘውታሪዎች ናቸው። (አል በቀራህ 2፡ 257)

وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا [١٧:٧٠]

የአደምን ልጅ በርግጥ አከበርናቸው፤ በየብስና በባህርም አሣፈርናቸው፤ ከመልካም ነገሮችም ለገስናቸው። ከፈጠርናቸው ፍጡሮች በብዙዎች ላይ ማስበለጥን አስበለጥናቸው። (አል ኢስራእ 17፡ 70)

በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ልጅ ነፃነትና የአላህ ሀይልና እውቀት የሚቃረኑ የሚመስላቸው ብዙዎች አሉ። ይህ ፈፅሞ ስህተት ነው። ነገሮች እኛ ሙስሊሞች በአላህ ቀዷና ቀደር (ቀድመው የተላለፉ ውሣኔዎችና ፍርዶች) ያለ ጥርጥር እናምናለን። ይህም ማለት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ያለፈውን፣ ያለንበትንና የወደፊቱን ሁሉ ያውቃል፤ በሁሉም ነገር ላይም ሀይልና ሥልጣን አለው ማለት ነው። ቢሆንም ግን በራሱ ፈቃድና ሀይል ነገሮችን የመምረጥ ነፃነትን ሠጠን፤ ነፃ ፈቃድና ፍላጎትም ለገሠን። ይህ ማለት ግን እሱ እኛ የምንሰራውን አያውቅም አሊያም በኛ ላይ ሀይል የለውም ማለት አይደለም። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የምንሠራቸውን ነገሮች ጥሩም ይሁኑ መጥፎ አንዲት ሣትቀር ያውቃል። አላህ እንዲህ አለ

إِنَّا هَدَيْنَاهُ السَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًا وَإِمَّا كَفُورًا [٧٦:٣]

እኛ መንገድን መራነው ያመስግንም ይካድም  (አል ኢንሣን 76፤ 3)

የነፃነት ፅንስ ሀሣብ ዑቡዲያህ (አላህን መገዛት) ጋርም አይቃረንም። ኢስላም እራሱ ነፃነትን የሠጠን ሲሆን ፈጣሪያችንን አላህን መታዘዝና ማገልገል እንዳለብንም አስተምሮናል። ኢስላም መሠረቱን ያደረገው ፍፁም በሆነ መልኩ ለአላህ ታዛዠ መሆንን ነው። በመሆኑም የኢስላማዊ ነፃነት ፅንሠ ሀሣብ ማንኛውንም ፍፁም የሆነ ሥልጣን ከግለሰቦች በመንጠቅ ለሚገባው አካል ለፈጣሪያቸው መስጠት ነው። ለምን ከተባለ እነኚህ ሥልጣኖች አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ለሰው ልጅ የሠጠውን ይቃረናሉና ነው። ለአላህ ፈቃድና ትእዛዝ ማደር የሰው ልጅ ነፃነትን አይጋፋም። የአምልኮ ተግባራት ወደ ትልቅ ስኬትና ነፃነት የሚያደርሱ መሠላሎች ናቸውና። አላህን መገዛት ውስጥ ውስጡን ሀላፊነትን ከመወጣት ጋር በእጅጉ የተያያዘ ነው ።

ነፃነት በኢስላም ከሞራላዊ ግዴታና ከተጠያቂነት አሊያም ከእውነተኝነት፣ ከፍትሃዊነት፣ ከበጎ ሠሪነትና ትክክለኛነት ከመሆን ማፈንገጥ አይደለም። እነዚህ አይነት ጋጥወጥነቶች ነፃነት ሊባሉ አይችሉም። ተራ ግርግር ወይንም ሙስና ልንላቸው እንችላለን። የኢስላም አስተምህሮ የሰው ልጆች ሁሉ በአእምሮ፣ በመንፈስም ሆነ በአካል ነፃ መሆን እንዳለባቸው ነው።

ኢስላም ለሁሉም ህዝቦች የእምነት ነፃነትንም አረጋግጧል። በእምነትም ማስገደድ እንደሌለ አውጇል። ሱራህ አል በቀራህ ቁ 256 ላይ የተመለከተውም ይሀው ነው። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል

لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ [٢:٢٥٦]

በሃይማኖት ማስገደድ የለም። ቅኑ መንገድ ከጠማማው በርግጥ ተገለጠ። (አል-በቀራህ 2፣ 256)

በመሆኑም ሰዎች ሁሉ እምነታቸውን በነፃነት ማራመድና የመተግበር መብት አላቸው። ሆኖም ግን እምነታቸውን በግድ ሌሎች ላይ ለመጫን ሙከራ ማድረግ የለባቸውም። እንዲሁም እስልምና ለሰው ልጆች ሀሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይሠጣል፤ ነገር ግን ሰዎች መሠረተ ቢስ ወሬዎችንና ውሸትን መናገር የለባቸውም። ኢስላም ሰዎች በራሣቸው ፍላጎትና ስምምነት መሪዎቻቸውን እንዲመርጡና መሪዎቻቸውም ታማኝ ሣይሆኑ ሲቀሩ አሊያም ሀላፊነትን መወጣት ሲያቅታቸው ያወርዱ ዘንድ የፖለቲካ ነፃነትንም ያስተምራል። ኢስላም የኢኮኖሚ ነፃነትንም ይፈቅዳል፤ ሰዎች በነፃነት ሠርተው የማግኘትና የፈለጉትን ያህል የማከማቸት መብት ያላቸው ቢሆንም ያለ አንዳች ርህራሄ በማግበስበስ ለራሣቸው ብቻ የተንደላቀቀ ኑሮ በመኖር ለሌላው ባለማሠብና በማጭበርበር መሆን የለበትም የሚል አቋም አለው።

እስልምና የነፍስን፣ የእእምሮንና የአካል ነፃነትን ያስተምራል።

እስልምና የግለሰብንና የማህበረሰብ ነፃነትን ያስተምራል።

እስልምና በዚህኛውም ሆነ በመጭው ዓለም ነፃነትን ያስተምራል።

በቁርዓን ውስጥ የነፃነት ፅንሠ ሀሣብ በተለያዩ ሁኔታዎችና ቃላቶች ተገልጿል። “ሁር” ወይንም “ተህሪር”- ነፃነት አሊያም ባሪያን ነፃ ማድረግ፣ “ነጃት”- የደህንነት ዋስትና ማግኘት፣ “ፈውዝ”- የላቀ ስኬት በማስመዝገብ ከግብ መድረስ፣ “ፈላህ”- አስተማማኝ ደህንነት … የሚሉት ጥቂቶች ሲሆኑ በሀዲስ ደግሞ “ዒትቅ” የሚለው ቃል ነፃ ማውጣት /ነፃ ነህ/ ማለትን ያመለክታል።

በሌላ በኩል ደግሞ ነፃነት አሉታዊና አዎንታዊ ገፅታዎች እንዳሉት መገንዘብ ይኖርብናል። ይሀውም አንድን ነገር ለመፈፀም ነፃነትን ማግኘትና ከአንድ ነገር ነፃ መውጣት ሊሆን ይችላል። ኢስላም ነፃነትን የሚፈልገው ለደስተኛና ጤነኛ ህይወት፣ በብልፅግና ለመኖር፣ እንዲሁም ለሞራላዊና ለተከበረ ህይወት ሲባል ነው። ኢስላም የሰው ልጆች በነፃነት የአምልኮ ተግባራቸውን እንዲፈፅሙ፣ ሀሣባቸውን እንዲገልፁ፣ ሰርተው እንዲያገኙ፣ ቤተሰብ እንዲመሠርቱና በምርጫቸውም የራሣቸው የሆነ መንግስት እንዲያቋቁሙ ይፈልጋል። ህዝቦች ሁሉ ከኢኮኖሚ፣ ከፖለቲካና ከማህበራዊ ጭቆና ነፃ እንዲወጡ ያበረታታል። ኢስላም ሰዎች ሁሉ ከቁስ አምላኪነትና ከራስ ወዳድነት ነፃ እንዲወጡ ይፈልጋል። ኢስላም ሰዎች አንዳንድ ሃይማኖቶች ከሚያደርሱባቸወ ስቃይ እንዲገላገሉ ይፈልጋል። በመጨረሻም ዋናውና እጅግ አስፈላጊው የሆነው ነገር ኢስላም የሰው ልጆች በመጨረሻውና ዘላለማዊው በሆነው ዓለም ከጀሀነም እሣት ነፃ እንዲወጡና በጀነት ውስጥ በሀሴት በአላህ ዉዴታ ሥር ተጠቃለው እንዲኖሩ ይፈልጋል።

የነፃነትን ፅንሠ ሀሣብ ለዓለም ያስተማሩት ሙስሊሞች ከመሆናቸው ጋር ዛሬ ዛሬ የዘመናችን ሙስሊሞች እየተገበሩት ከትግበራው የራቁ መሆናቸውን ስናይ በእጅጉ ያሣዝናል። በመሆኑም በሙስሊሙ ዓለም የሚገኘው ማህበረሰብ ከጭቆና፣ ከኢፍትሃዊነትና ከእኩልነት እጦት እየተሠቃየ ነው። ሙስሊሞች ለራሣቸውም ሆነ በሌላው ዓለም በሚደረገው የነፃነት እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ተሣታፊ መሆን ይኖርባቸዋል። ስለ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና እምነት ነፃነት ከመናገር ወደ ኋላ ማለት አይገባቸውም። ስለ ሰብአዊ መብት፣ በማህበረሰቡ ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ስላላቸው ህዝቦች መብት፣ ስለ ሴቶች መብትም እንዲሁ ማንሣትና መታገል ይኖርባቸዋል። እነኚህ ሁሉ መብቶች በእስልምና ሙሉ እውቅናና ድጋፍ ተሠጥቶአቸዋል። በመሆኑም የቁርኣንንና የሀዲስን መመሪያ እንዲሁም የቀደምት ሠለፎችን ፈለግ በመከተል እነኚህ መብቶችና ነፃነቶች በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ለማስረፅ በከፍተኛ ሁኔታ መጣር ይጠበቅብናል።

 

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

የብዙሀን መንገድ ሁሌም ትክክል ወይንስ…..? ?

549666 526000034105788 181125928 n 300x228 የብዙሀን መንገድ ሁሌም ትክክል ወይንስ.....? ?

የብዙሀን መንገድ ሁሌም ትክክል ወይንስ…..? ?

በጃሂልያ ዘመን (ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም ከመላካቸው በፊት) ሕዝብ የበዛበትን መንገድ ልክ እንደ ትክክለኛ መንገድ አድርገው የሚያስቡ ነበሩ። ጥቂቱን (አናሳውን) ደግሞ እንደተሳሳተ አድርገው ነበር የሚወስዱት። ስለዚህ በነርሱ እይታ ሕዝብ ብዛት የሀቅ መንገድ ነገር ግን የሰው ቁጥር ማነስን ልክ እንደ ጠማማ መንገድ ነበር። ይሄ ነበር ለነርሱ የሀቅ እና የተሳሳተ መንገድ መመዘኛ (የሰው ብዛት)።
ነገር ግን ይሄ የተሳሳተ አመለካከት ነው። 
አላህ በቁርዓኑ እንዲህ ይላል

وَإِن تُطِعْ أَكْثَرَ مَن فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا يَخْرُصُونَ [٦:١١٦]
በምድርም ካሉት ሰዎች አብዛኞቹን ብትከተል ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡ አል አንዓም 116

أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ [٧:١٨٧]
ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፤ በላቸው። አል አዕራፍ 187

” ስለዚህ መመዘኛው የሰው መብዛት ወይም ማነስ ሳይሆን መመዘኛው ሀቅ ነው። እናም ማንም ሀቅ ላይ ያለ ሰው ትክክለኛው መንገድ ላይ ነው። ምንም እንኳን ብቻውን ቢሆንም። እርሱ ነው ቅኑን ጎዳና ተከትሎ ለስኬት የሚበቃው። ነገር ግን ምንም እንኳን የሰው ቁጥር ቢበዛም ሀቁን መንገድ ካልተከተሉ ከነርሱ መንገድ መራቁ ግዴታ ነው። እንዳይሳሳትም መጠንቀቅ አለበት። ማየት ያለብን ሀቁን ነው። አንዱ አሊም ብለዋል:- “ሀቅ በሰው አይመዘንም ነገር ግን ሰው በሀቅ ይመዘናል” በመሆኑም ማንም ሀቅ ላይ ያለ ስው ሊከተለው የሚገባው የያዘውን ሀቅ ብቻ እና ብቻ ነው።”

አላህ ስለቀደምት ህዝቦች በቁርዓኑ ላይ ሲያነሳ እንዲህ በማለት ሁሌም አናሳው በሀቅ መንገድ ላይ እንዳለ ይነግረናል

وَمَا آمَنَ مَعَهُ إِلَّا قَلِيلٌ [١١:٤٠]
ከርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም። ሁድ 40

በሀዲስ እንደተገለጸው ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም አየሁኝ አሉ:- ” ነቢይ ሆኖ በጣም ትንሽ ህዝብ የሚከተለው ፤ ነቢይ ሆኖ አንድ እና ሁለት ሰው የሚከተለው ፤ ነቢይ ሆኖ ምንም ሰው የማይከተለው። ” (ሰሂህ ቡኻሪ)

“ሰዎች የበዙበት መንገድ ሁሌም እንደ ሀቅ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባውም። ሊታይና ሊወሰድ የሚገባው የዕውነት ወይም የውሸት መንገድ መሆኑ ብቻ ነው። ስለዚህ ሀቁ ምንም ሆነ ምንም ሰው ሊከተለው ይገባል ምንም እንኳን አናሳውም ወይንም ማንም ህዝብ ባይከተለውም። ስለዚህ ሀቁ መንገድ ነው መከተል ያለብን ይሄ ነው መዳኛው መንገድ።” 
ረሱል ሰለላሁአለይሂወሰለም ብለዋል:- 
“ኢስላም እንግዳ ሆኖ ይመጣል እንግዳ ሆኖ ይመለሳል።”
“ይሄ የሚሆነው ፈሳድ በበዛበት ወቅት ነው። ወሸትና ባጢል ይንሰራፋል:: ጥቂት ሰዎች (እንግዶች) ሲቀሩ ሁሉም ከትክክለኛው መንገድ ይስታል፤ እናም እነዛ ሀቅ ላይ ያሉት ጥቂት ሰዎች እንደ እንግዳ ይታያሉ።”
አልፉደይል ኢብን ኢያድ ረሂመሁላህ ብለዋል
“ያለህበት መንገድ ትክክለኛ ከሆነ አብረውህ ባሉት ጥቂት ሰዎች ቁጥር አትጨነቅ። ሁሌም ቢሆን የጥመትን መንገድ ተጠንቀቅ። በውሽት የተመሰረተ የሕዝብ ባዛት እንዳትታለል ተጠንቀቅ።”
======ሸይኽ ሳልህ አል ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) =======

اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً، وَفِي الآخِرَةِ حَسَنَــةً، وَقِنَا عَذَابَ النَّار

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

የኢስላም ማህበራዊ ስርዓት ክልክል የሆኑ ግንኙነቶች (ሙሀረማት) የዝሙት ክልክልነት

የኢስላም ማህበራዊ ስርዓት

     ከማህበራዊ ችግሮች አንዱ የሰዉ ልጅ ተፈጥሮ የሆነዉን የወሲብ ፍላጎት እንዴት ወግና ፈር ማስያዝ እንደሚችል ዘዴና ስትራቴጂ መቀየሱ ላይ ነ ።

የሰዉ ልጅ ወሲባዊ ፍላጐቱን መገደብ ካልቻለ ማህበራዊ ህይወቱን መቆጣጠር አይችልም ። በርግጥ ለወሲብ ፈላጐት ገደብ ባይበጅም ማህበራዊ ህይወታችንን መቆጣጠር አይሳነንም የሚሉ ወገኖች አሉ ። ግን የሚመሩትን ወይም የሚኖሩበትን ማህበረሰብ ከህሊና ዉጥረትና ከሞራል ዉድቀት ሊያዱት አልቻሉም ።አይችሉምም ። በመሆኑም የ አዳም ዘር ስጋዊ ጥማቱን ተቆጥዓጥሮ ከእንስ ሳዊ ግንኙነት ወደ ሰበ አዊ ግንኙነት ይሸጋገር ዘንድ ኢስላም ፈቃድ ስጋ በባልና በሚስት ብቻ መፈጸም ያለበት መሆኑን ደንጓል ።

ክልክል የሆኑ ግንኙነቶች (ሙሀረማት)

   በቅድሚያ ኢስላም የተፈጥሮ የደምና የስጋ ት ስ ስርና ቅርበት እንዲኖራቸው የደለደላቸዉ ወንዶችና ሴቶች እንዲጋቡ አይፈቅድም ። ለምሳሌ የሚከተሉት ወገኖች በጋብቻ ሊጣመሩ እርም ሃራም ይሆንባቸዋል ።  እናትና ልጅ አባትና ልጅ ወንድምና እህት አክስትና በወንድም በሴትም በኩል የወንድም ወይም የህት ልጅ አጎትና የወንድም የህት ልጅ የእንጀራ አባት የእንጀራ ልጅ የእንጀራ እናትና የእንጀራ ልጅ የሚስት እህትና አማቷ እንዲሁም የጥቢ ግንኙነት ያላቸዉ በተመሳሳይ ሁኔታ ክልክል ይሆናል ። (ሱረቱ ኒሳአ ቁ 23-25)

ኢስላም ከላይ የተጠቀሱትን የቅርብ ዘመዶች እንዳይጋቡ በመከልከሉ በመካከላቸው ምንም አይነት ወሲባዊ መሳሳብ አይኖርም ። አይታሰብምም ።

እንስ ሳዊ ባህርይ የተጠናወታቸዉና በየትኛዉም የሞራል ህግ ለመገዛት ሰበ አዊ ስልጥዓኔ የሚጐድላቸው ወገኖች ግን የቅርብ ዘመዶቻቸዉን እናትና እህቶቻቸዉን ሳይቀር ለወሲብ ጥማታቸዉ ማርኪያ ማድረጋቸዉ አልቀረም ። አላህ ይተብቀን።

የዝሙት ክልክልነት

   ከላይ ከተገለጹት ት ስ ስሮች ባሻገር አንድ ሰዉ ህጋዊ ጋብቻ ያላትን ሴት ማግባት አይፈቀድለትም ፦
(وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ النِّسَاء  )سورة النساء 24

ከሴቶችም እነዚያ ያገቡት እንዲሁ እርም ናቸው ። ሱረቱ ኒሳእ ቁ 24

ከናል ነጻ የሆኑ ሴቶችን ከላይ እንደተጠቀሰዉ ያለ ህጋዊ ጋብቻ መዋሰብ በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

وَلاَ تَقْرَبُواْ الزِّنَى إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاء سَبِيلاً سورة الاسراء  32

ዝሙትን አትቅረቡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ስራ ነዉና መንገድነቱም ከፋ ። ሱረቱ አል ኢስራእ ቁ 32

 

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

ما هو الاسلام ؟ ኢስላም ማለት ምን ማለት ነው?

ኢስላም ማለት ምን ማለት ነው?

ኢስላም ማለት የአላህ (ሱ.ወ) አንድነትን በማወቅና በማመን ለርሱ እጅ መስጠት፣ ለፍላጎቱና ትዕዛዛቱ ማደር፣ ተግባራዊ ለማድረግም በታዛዥነት መንፈስ መንቀሳቀስ፣ ከሽርክ (በአምልኮ ሌላን አካል ከርሱ ጋር  ከማጋራት) መጽዳት ነው። ይህም አላህ (ሱ.ወ) ያዘዛቸውን ነገሮች በመፈጸምና የከለከላቸውን ደግሞ በመራቅ ይረጋገጣል። ኢስላም ከላይ በተሰጠው ትርጓሜ መሰረት በአላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ብቸኛና እውነተኛ ሐይማኖት ነው፤

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል

إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ [٣:١٩]

“አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው።” (አሊ-ዒምራን 3፤91)

አላህ (ሱ.ወ) ለመልክተኞቹና ነብያቶቹ በየዘመኑ ያወረዳቸው ህግጋቶች የተለያዩ ቢሆኑም ለሁለም ነብያትና ህዝቦች የወረዱት ህግጋቶች የአላህን አንድነት በማስተማር፣ ለሰው ልጆች ጠቃሚ ነገሮችን በማረጋገጥና ወደ መልካም ሥነ-ምግባር ጥሪ በማድረግ ያለቸው አስተምህሮት ተመሳሳይ ነው። እንደየ ዘመኑ ሁኔታና ለሰዎች ኑሮ አስፈላጊነት አኳያ አንዳንድ ህጎች ላይ ልዩነቶች ያሉ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በየዘመኑ የወረዱት የአላህ (ሱ.ወ) ህግጋቶች ያላቸውም ስፋትና ጥበት የተለያየ ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል

لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجًا [٥:٤٨]

“ከእናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን።” (አል-ማኢዳ 5፤48)

ከሰማይ የወረዱት መለኮታዊ ህግጋቶች በብዙ ጉዳዮ ላይ ተመሳሳይነት ይንጸባረቅባቸዋል፤ ከነዚህም ውስጥ፡

1. መነሻ (ምንጭ)

የመለኮታዊ ህግጋቶች ምንጭ ከብቸኛውና አንዱ አምላክ አላህ.(ሱ.ወ) ስለሆነ ደረጃው ከፍ ያለ ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል

إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ [٤:١٦٣]

“እኛወደኑሕናከርሱበኋላወደነበሩትነቢያትእንዳወረድንወደአንተምአወረድን።” (አን-ኒሳእ 4፤163)

2. አላማ

መለኮታዊ ህጎች ከአላማዎች መካከል፡-

  • ሰዎችን ለጌታቸው ተገዥዎች እንዲሆኑ ማድረግ። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል

وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ [٢١:٢٥]

“ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።” (አል-አንቢያእ 21፤25)

በሌላ የቁርኣን አንቀጽም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ فَمِنْهُم مَّنْ هَدَى اللَّهُ وَمِنْهُم مَّنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ الضَّلَالَةُ فَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ [١٦:٣٦]  

“በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ‘አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ’ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል። ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ። ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ። በምድርም ላይ ኺዱ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ።”(አን-ነህል 16፤36)

  • ሰዎች ጌታቸውን እሱ በደነገገው ህግጋትና ባዘዘው መሰረት በፍቅርና በፍቃደኝነት መገዛት። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

إِنَّمَا كَانَ قَوْلَ الْمُؤْمِنِينَ إِذَا دُعُوا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ أَن يَقُولُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ [٢٤:٥١]

“የምእምናን ቃል የነበረው ወደ አላህና ወደ መልክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ሰማን፤ ታዘዝንም ማለት ብቻ ነው። እነዚህም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው።” (አን-ኑር 24፤51)

3. አጠቃላይጽንሰሐሳቦች

መለኮታዊ ህጎች ጠቅላላ በሆኑ ጽንሰ ሐሳቦች ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም አላቸው፤ ለምሳሌ ሁለም ሰው የስራውን እንደሚያገኝ፤ ጥሩ የሰራ ጥሩ ምንዳ እንደሚከፈለውና መጥፎ የሰራ ደግሞ ቅጣት እንደሚገባው፤ አንድ ሰው በሌላ ሰው ወንጀል እነደማይጠየቅና ከራሱ ሥራ ውጭም እንደማያገኝ ሁሉም መለኮታዊ ህጎች ይስማማሉ። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ ﴿٣٦﴾ وَإِبْرَاهِيمَ الَّذِي وَفَّىٰ ﴿٣٧﴾ أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ﴿٣٨﴾ وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ ﴿٣٩﴾ وَأَنَّ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَىٰ ﴿٤٠﴾ ثُمَّ يُجْزَاهُ الْجَزَاءَ الْأَوْفَىٰ ﴿٤١﴾

“ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) (እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም። ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም። ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል።” (አን-ነጅም 53፤36-41)

ያለፉት መለኮታዊ ህጎችና መመሪያዎች ሁሉ ለአላህ. (ሱ.ወ) መታዘዝንና ከሰው ልጅ በመረጣቸው መልክተኞቹ አንደበት በደነገገው ህግ መሰረትም እርሱን ብቻ ማምለክን ያስተምራሉ።

የመጀመሪያው መልክተኛ ነቢ ኑህ (ዐ.ሰ) እንዲህ ይላሉ፡-

وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِينَ [١٠:٧٢]

“ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ።” (አን-ነምል 10፤91)

የነብያቶች አባት በመባል የሚታወቁት ነብዩላህ ኢብራሂምና ልጃቸው ኢስማዒልም እንድህ ይላሉ፡-

رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ [٢:١٢٨]

“ጌታችን ሆይ! ላነተ ታዛዦችም አድርገን። ከዘሮቻችንም ላንተ ታዛዦች ሕዝቦችን (አድርግ)። ሕግጋታችንንም አሳየን፤ (አሳውቀን)። በኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና።” (አል-በቀራ 2፤128)

ነቢዩላህ ኢብራሂምና ነቢዩላህ የዕቁብም (ዐማ.ሰ) ዝርዮቻቸው ትክክለኛውን የአላህ ዲን ኢስላምን ብቻ ይዘው እንዲኖሩና እንዲሞቱ አደራ ሲሰጡ እንድህ ብለዋል

وَوَصَّىٰ بِهَا إِبْرَاهِيمُ بَنِيهِ وَيَعْقُوبُ يَا بَنِيَّ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَىٰ لَكُمُ الدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ [٢:١٣٢]

“በርሷም (በሕግጋቲቱ) ኢብራሂም ልጆቹን አዘዘ። ያዕቁብም (እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ)። ‘ልጆቼ ሆይ! አላህ ለናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ’ (አላቸው)።”(አል-በቀራ 2፤132)

ነቢዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ) ይህንኑ ከአላህ ሲለምኑ እንዲህ ይላሉ፡-

رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَنتَ وَلِيِّي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ [١٢:١٠١]

“ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ። ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ። የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ። ሙስሊም ሆኘ ግደለኝ። በመልካሞቹም አስጠጋኝ (አለ)።” (ዩሱፍ 12፤101)

ነቢ ሙሳ (ዐ.ሰ) ትክክለኛ አማኝ ማለት ለአላህ (ሱ.ወ) ያደረ ሙስሊም መሆኑን ለህዝባቸው ሲያስተምሩ እንዲህ ይላሉ

وَقَالَ مُوسَىٰ يَا قَوْمِ إِن كُنتُمْ آمَنتُم بِاللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوا إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ [١٠:٨٤]

“ሙሳም አለ፡- ‘ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ። ታዛዦች እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)’።” (ዩኑስ 10፤84)

ይህን ጉዳይ የሚያስረዱ ሌሎች የቁርኣን አንቀጾች በብዛት ይገኛሉ።

የኢስላም ልዩ ትርጓሜ

እንደሚታወቀው ለሰው ልጆች አስፈላጊና ጠቃሚ ነገሮች ከግዜና ሁኔታዎች መለያየት ጋር ተያይዞ ሊለያዩ ይችላሉ፤ ስለዚህም ጥበበኛ የሆነው ጌታ አላሁ (ሱ.ወ) ቀድሞ በእውቀቱ እንዳሳለፈው ለሰው ልጆች በየጊዜው ጠቃሚና አስፈላጊ የሚሆነውን ነገር ይደነግጋል፤ ስለዚህም ነው ሻሪ ከተሻሪ በአብዛኛው በላጭና የተሻለ ሆኖ የምናገኘው። ምክኒያቱም ከጥሩ ነገር ወደ በላጭ ነገር መሸጋገር አላህ (ሱ.ወ) በፍጡራኑ ላይ ያደረገው ተፈጥሯዊ ህግ ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) ባሮቹን ምንግዜም ቀስ በቀስ ከትንሽ ወደ ትልቅ፣ ከጥሩ ነገር ወደ በላጭና ሙሉ ወደ ሆነ ነገር ይወስዳቸዋል።

ኢስላማዊ ሸሪዓ (ህግ) አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጆች መመሪያ ያወረደው የመጨረሻና የማይሻር መለኮታዊ ህግ ነው፣ ስለዚህ ሁሉንም የህይዎት ዘርፎች የሚዳስስና ሰፊ ይዘት ያለው ሆኖ እናገኘዋለን። የሸሪዓ ህግ ውስጥ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ድንጋጌዎች ናቸው ያሉት፤ አቅመ ደካማዎች እንደ ችሎታቸው የሚሰሩበት የተግራራ ሥርዐት ያለ ሲሆን ጠንካሮችና ብረቱዎችም ባለቸው አቅም ተጠቅመው ሐላፊነታቸውን እንዲወጡ የሚያስችሉ ጠንከር ያሉ ትዕዛዛት ይገኛሉ። ይህም አላህ (ሱ.ወ) ለባሮቹ ያለውን ሰፊ እዝነት ያሳያል። አላህ (ሱ. ወ) እንዲህ ይላል

ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَاتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَ الَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ [٤٥:١٨]

“ከዚያም ከነገሩ (ከሃይማኖት) በትክክለኛይቱ ሕግ ላይ አደረግንህ። ስለዚህ ተከተላት። የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል።” (አል-ጃሲያ ፤18)

አላህ (ሰ.ወ) ነብያችን ሙሃመድን (ሶ.ዐ.ወ) በመላክ መሰረታዊ ጽንሰ ሐሳቦቹንና ድንጋጌዎቹን ያብራራበትና ለሰው ልጆች ሁሉም እንዲያደርሱት ወደ እሱም ያዘዛቸው ዲነል-ኢስላም አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ለባለቤቱም የሚጠቅም ብኛው ሐይማኖት እሱ መሆኑን አወጀ። ስለዚህ ኢስላም ከሱ በፊት የነበሩትን ሐይማኖቶች ሁሉ ሽሯል፤ በመሆኑም ኢስላምን የተከተለ ለፈጣሪው ያደረ (ሙሰሊም) ማለት እርሱ ነው፤ ከኢስላም ያፈነገጠ ደግሞ ለፈጣሪው አላደረም ወይም ሙስሊም አይደለም ማለት ነው።

ወደዚህ የአላህ ዲን ኢስላም መግቢያ በሩ “ላኢላሀኢለሏህሙሃመድረሱሉሏህ” በማለት የአላህን ብቸኛ አምላክነትና የነብዩ ሙሃመድ የአላህ መልክተኝነት መመስከር፤ የዚህ የሰጠኸውን የምስክረነት ቃል ድንጋጌዎችና ቅድመ ግደታዎች ተግባራዊ ማድረግና እንደዚሁም ይህን የምስክረነት ቃልህን የሚጻረርን ነገርን ሁሉ መራቅ ናቸው።

ታለቁ ጌታ አላህ (ሱ. ወ) እንድህ ይላል

وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ [٣:٨٥]

“ከኢስላምሌላሃይማኖትንየሚፈልግሰውፈጽሞከርሱተቀባይየለውም።እርሱምበመጨረሻይቱዓለምከከሳሪዎቹነው።” (አሊ-ዒምራን 3፤85)

ነብያችን ሙሃመድ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ

والذي نفس محمد بيده لايسمع بي أحد من هذه الأمة، يهودي ولا نصراني ثم يموت ولم يؤمن بالذي أرسلت به إلا كان من أصحاب النار )رواه مسلم(

“በዚያየሙሃመድነፍስበእጁበሆነችውጌታእምላለሁ፤ከዚችኡማውስጥማንኛውምሰውየሁዳምይሁንነሳራ (ክርስቲያን) የኔንመልክትሰምቶበዚያእኔበተላኩበትነገር (ኢስላም) ሳያምንከሞተ(እርሱ) ከሳትባልደረባዎችነው።” (ሙስሊም ዘግበውታል)

በዚህም መሰረት ከነብያችን ሙሃመድ (ሶ.ዐ.ወ) መላክ በኋላ ያሉ አይሁድም ይሁን ክርስቲያን ወደ ኢስላም ካልገቡ በቀደምት ነብያቶቻው ማመናቸው አይጠቅማቸውም ማለት ነው፤ ምክኒያቱም ነብያችን ሙሃመድ (ሶ.ዐ.ወ) ይዘውት የመጡት ዲነል-ኢስላም ከሱ በፊት የነበሩትን ሐይማኖቶች የሚሽር ስለሆነ ነው።

 

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

ኢስላምን ለምን ይመርጡታል? لماذا اختارو الاسلام ؟

ኢስላምንለምንይመርጡታል?

ማንኛውም በውስጡ ለሚነሡ ሦስት መሠረታዊ ጥያቄዎች (ማለትም አካላዊ፣ አዕምሯዊና መንፈሣዊ ጥያቄዎች) ፍትሐዊ መልስ የሚሻ ሠው አይነተኛ ምርጫ እስልምና ነው። “እስልምናን ከሌሎች እምነቶችና አመለካከቶች ልዩ የሚያደርጉትን ልዩ መገለጫዎች ምን ምንድን ናቸው?” የሚል ጥያቄ ይነሳ ይሆናል።

የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፡-

  1. እስልምና ምንጩ ፍጹም ጥብቅና እንዲሁም ከሠው ልጆች የትኛውም ዓይነት ጣልቃ ገብነትና ብርበራ የተጠበቀ ብቸኛው እምነት ነው።

  2. መለኮታዊ የሆኑት ኢስላማዊ መጽሃፍትም ፍጹም ረቂቅ የሆነ አምላካዊ ሠንሠለት ከመሆኑም በላይ የሠው ልጅ ዘመናዊ ወደሆነ አመለካከት እና የዓለም እይታ ይመራል።

  3. ቁርኣን-ኢስላማዊው ቅዱስ መጽሐፍ- እጅግ ድንቅ በሆነ ሁኔታ ከሳይንሳዊ እውነታ ጋር የሚስማማ ከመሆኑም በላይ የዚህ ፍጥረተ-ዓለም ጠንሳሽ የሆነው አካል አሻራ በግልጽ ያረፈበት መሆኑ እውነት ፈላጊ በሆኑ ዘንድ በተደጋጋሚ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ምንም እንኳ እነኚህ ሠዎች የተለያየ የሆነ የእውነት አመለካከት መመዘኛ ቢኖራቸውም በዚህ መጽሃፍ ላይ ግን ስምምነት አላቸው። ይህ መጽሃፍ የተለያዩ የተፈጥሮ ክስተቶችን መዝግቧል። ተከታዮቹንም አካባቢያቸውንና ሌሎች ፍጥረታትን እንድንንከባከብ ያዛል።

  4. ይህ መለኮታዊ መጽሃፍ ከሌሎች አመለካከቶችና እምነቶች በተለየና በላቀ ሁኔታ በምክንያታዊነት (reason and logic) የሚያምንና ከምክንያታዊነት የራቀ መረጃን የሚያቀርቡ ሠዎችን የማሠብና የመመራመር አቅማቸው ዝቅ ማለቱን መናገሩ ኢስላም በራዕይ ላይ ብቻ የማይንጠለጠል መሆኑን ያሳያል።

  5. ኢስላማዊ እምነትና ሥርአቶች ቀላል፣ ተፈጥሮን የማይጋፋ ለምክንያታዊነትም ሆነ ለስሜት የማይከብዱ ናቸው።

  6. አብዛኞቹ ኢስላማዊ የሆኑት አስተምህሮዎችና ትዕዛዛት በሠው ልጅ ሕይወት ውስጥ ጉልህ የሆነ ሚና እንደሚጫወቱ በማስረጃዎችና በእውነታዎች በቀላሉ ማረጋገጥ የሚቻል ነገር ነው። ለአብነት ያህል ኢስላም በአልኮል መጠጥ ላይ ያስቀመጠውን ጥብቅ ክልከላ እንመልከት። የአልኮል መጠጥና የመኪና አደጋ ወይም የቤት ውስጥ ግጭት ያላቸውን ቀጥተኛ ተዛምዶ ለማወቅ ስታትስቲክስ ባለሥልጣን ወይም ፖሊስ ኮሚሽን መሄድ ሳያስፈልገን እንዲሁ የምንረዳው ነገር ነው። ሌላ ምሳሌ ካስፈለገ ዘካን ማየት እንችላለን። በዓለም ላይ ያሉ አላህ ገንዘብ የሠጣቸው ሠዎች በየዓመቱ ከጠቅላላ ሐብታቸው ላይ 2.5 ከመቶ የሚሆነውን ዘካ ቢያወጡ ድህነትን በቀላሉ ይቀርፉ እንደነበር ማሠብም በቂ ነው።

  7. ኢስላም በፈጣሪ የተሠጡ ተፈጥሮአዊ ስሜቶችን፣ ዝንባሌዎችንና ችሎታዎችን ትኩረት ከመስጠቱም በላይ ሚዛናዊ የህይወት መመሪያን ያስቀምጣል። ከዚህም አልፎ መሠረታዊ የሆኑ የሠው ልጅ አካላዊ፣ አእምሯዊና መንፈሳዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት ከመጣሩም በላይ የአንዱን ፍላጎት ለማሟላት በሌላኛውን ላይ አይረማመድም።

  8. ኢስላም ለሠው ልጅ ሚዛናዊና ሕያው፣ ህይወታቸው የተገለጠ መጽሐፍ ይመስል ለሁሉም ክፍት የሆኑ አርአያን (ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ)) ሠጥቶናል።

  9. የኢስላም የስነ-ፍጥረት ታሪክ ከውርስ ኃጢያት (original sin) ነጻ ነው። የውርስ ኃጢያት እሳቤ ብዙዎችን የተጫነ አመለካከት መሆኑ ይታወቃል። የውርስ ኃጢያ አሁን አሁን እጅግ ተለዋዋጭ የሆነና ታሪክን እጅግ በተዘበራረቀና ቋሚ ባልሆነ መንገድ እንዲሄድ ያደረገ መሆኑን ሠዎች ያምናሉ።

10. ቁርኣን በዕውቀት ላይ ያለው አቋም ከጥንታዊ ፍልስፍናዎች የተለየ ሲሆን ሳይንስና እውነተኛ መንፈሳዊነትን ላዋሃደው የልምድ ዕውቀት ልዩ ግምት ይሠጣል።

11. ቁርኣን እያንዳንዱ ተመራማሪ አዕምሮ ውስጥ የሚፈጠሩትን የመኖር ዓላማና ከሞት በኋላ ሕይወት የመሳሰሉ ጥያቄዎች አመርቂ በሆነ ሁኔታ ይመልሳል።

12. ለሠው ልጅ ማንነትና ሠብዐዊ ወንድማማችነት አጽንዖት የሠጠው እስላማዊ አስተምህሮ በሕዝቦች መካከል ያለውን የልዩነት ግርዶሽ የማንሳትና የመግፈፍ አቅም እንዲኖረው አስችሎታል። ይኸው እስልምና የሰው ዘርን አጥፊ ከሆነው ብሄረተኝነት እና ዘረኝነት ይታደጋል።

13. ኢስላም በርሱ ጥላ ለሚጠለሉና በሥርዓቱ ለሚመሩ ሕዝቦች በወዲያኛው ዓለም ሙሉ የሆነ ነጻነትን፣ ተድላንና ደስታን ብሎም ሰላም የሠፈነበትን ኑሮ እንደሚጎናጸፉና እንደሚሸለሙ ቃል ገብቷል።

14. ኢስላማዊው ታሪክ ፍትህን፣ ርህራሄን፣ እውነትንና ግልጽነትን በሠው ዘርም ሆነ በተፈጥሮ ላይ ያሠፈነ ሁልጊዜ አርኣያ ሊሆን የሚችልን ማኅበረሠብ አቅርቦልናል።

  1. ኢስላም በሠውና በፈጣሪው መካከል ጣልቃ የሚገቡ ነገሮችን ሁሉ አስወግዶ ሠዎች ከፈጣሪያቸው ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ አድርጓል።

 

 

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

ህይወት ከቁርኣን ጋር الحياة مع القرآن الكريم

 

ህይወት ከቁርኣን ጋር                          الحياة مع القرآن الكريم 

ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ከመላካቸው በፊት በመካና በዙሪያዋ የሚኖሩ የዐረብ ምድር ህዝቦች በመሃይምነት ጨለማ ውስጥ የሚደናበሩ ሆነው እናገኛለን።

መለኮታዊው ራእይ ቁርኣን ደረሠና ከድቅድቁ ጨለማ ውስጥ አወጣቸው፤ ወደ መጠቁ ዘመናዊና ንቁ ህዝቦች አሸጋገራቸው።

ቁርአን ምንጊዜም ህያውና ዘላለማዊ የሆነ የአላህ(ሱ.ወ) ቃል ነው። የአላህ ጥበቃ ስላልተለየው በርካታ ዘመናትን ተሻግሮ ሣይከለስ ሣይበረዝ ዛሬም ድረስ በመካከላችን ይገኛል። ቁርኣን ላወቀው፣ ላስተነተነውና ለሚሠራበት ሁሉ በማንኛውም ዘመንና ቦታ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው። በሱ የፈረደ በፍትህ ፈረደ። በሱ የተናገረ እውነት ተናገረ። በሱ የታከመ አስተማማኝ ጤናን አገኘ። በቁርኣን ውስጥ የቀደሙን ህዝቦች ታሪክ አለ። ወደፊት ስለሚሆኑ ክስተቶችም ትንበያ አለ። ከፊት ለፊታችን ስለሚጠብቀን ስለ ታላቁ የትንሣኤ ቀን ምልክቶችና በውስጡ ስለሚከሰቱት አስፈሪና አስደንጋጭ ሁኔታዎችንም ይዟል።

ቁርኣን ውሽትና እውነትን መለያ ነው። ስህተትንና ትክክሉን ማሣወቂያም ነው። ቁምነገር ነው ቀልድ አይደለም። ቁርኣን የማይበጠስ የሆነ የአላህ ገመድ ነው። አላህንም ለማወቅ የሚረዳ ትክክለኛው መንገድ ነው። የሰው ልጅ ስሜቶችና ፍላጎቶች አያሸንፉትም። የብልሃትና የደመ ነፍስ ሰዎች እሱን ለመቀየር አይቻላቸውም። ፍጥረታት ሁሉ ተሠባስበው አምሣያውን እናምጣ ቢሉ ፈፅሞ አይችሉም። ዑለማኦች ከሱ አይጠግቡም። ተማሪዎች ከእውቀቱ ጨልፈው አይጨርሱም። ደጋግመው ቢያነቡት አይሠለችም። በጊዜ ብዛት አያረጅም። ትንግርቱ በዘመን ብዛት ተነግሮ አያልቅም። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ

سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِي الْآفَاقِ وَفِي أَنفُسِهِمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الْحَقُّ أَوَلَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ [٤١:٥٣]

“እርሱም (ቁርኣን) እውነትመሆኑለነርሱእስከሚገለፅላቸውድረስበአፅናፎቹውስጥናበነፍሦቻቸውምውስጥያሉትንታምራቶቻችንንበርግጥእናሣያቸዋለን።ጌታህምእርሱበነገሩላይሁሉአዋቂመሆኑአይበቃቸውምን!” (ፉሲለት 41፤ 53)

በሌላ የቁርኣን አንቀፅም እንዲህ ይላል

وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا [٢٧:٩٣]

“ምስጋናምለአላህነው።ተዓምራቶቹንወደፊትያሳያችኋል። ‘ታውቋትምአላችሁ’ በላቸው።” (ነምል 27፤ 93)

ይህም ማለት ምልክቶቹንና ሀያል ችሎታውን ታውቃላችሁ ማለት ነው። አስከትሎም

وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ [٢٧:٩٣]

“ጌታህምከምትሠሩትሁሉዘንጊአይደለም።”” (ነምል 27፤ 93) ይላል።

በዚህም ንግግር ውስጥ አላህ ተቆጣጣሪያችን እንደሆነና ከእይታው ያልራቅን ስለመሆኑ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክትና ማስፈራሪያ አለበት።

ቁርኣን ቀልብን ህያው ያደርጋል

ቁርኣን የሞተን ቀልብ ህያው ያደርጋል። ውሃ መሬት ከሞተች በኋለ ነፍስ እንደሚዘራባትና አዝመራን እንደሚያበቅል ሁሉ ህይወት የሌላትንም ሰውነት ሩህ ይመልስባታል። ቁርኣን የወረደው ከሰማይ ነው። ይህ ከሰማይ የወረደ የአላህ ራህመት ልብን ባገኘ ጊዜ ልብ ትፍታታለች፣ ዘና ትላለች፣ ትደሠታለች፣ ነፍስ በመዝራትም መንቀሣቀስ ትጀምራለች። በተቃራኒው ደረቅ ቀልብ ግን እንደ አለት ናት አንዳችም ህይወት የላትም። ቁርኣን አያለዝባትም። أُوْلَئِكَ فِي ضَلالٍ مُبِين  “እነሱምግልፅበሆነጥመትውስጥናቸው።”ይላል አላህ። ህይወት ያላትና የሌላት ቀልብ በምንም መልኩ ፈፅሞ ሊወዳደሩ አይችሉም። በመካከላቸው ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ ነው። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ፡-

أَوَمَن كَانَ مَيْتًا فَأَحْيَيْنَاهُ وَجَعَلْنَا لَهُ نُورًا يَمْشِي بِهِ فِي النَّاسِ كَمَن مَّثَلُهُ فِي الظُّلُمَاتِ لَيْسَ بِخَارِجٍ مِّنْهَا كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلْكَافِرِينَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ [٦:١٢٢]

“ሙትየነበረናህያውያደረግነውለርሱምበሰዎችመካከልበርሱየሚሄድበትንብርሃንያደረግንለትሰውበጨለማዎችውስጥከርሷየማይወጣሆኖእንደለሰውቢጤነውን? እንደዚሁለከሀዲዎችይሠሩትየነበረነገርተጌጠላቸው።” (አል አንዓም 6፤122)

በሌላ አንቀፅም ቁርኣን የያዙ ሰዎች ትልቅ ብርሃንና መመሪያ እንደያዙ ሲገልፅ እንዲህ ይለናል፡-

وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ [٤٢:٥٢]

“እንደዚሁከትእዛዛችንሲሆንመንፈስንወዳንተአወረድን፤መፅሃፍምእምነትምምንእንደሆነየምታውቅአልነበርክም፤ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችንየምንሻውንሰውበርሱየምንመራበትብርሃንአደረግነው።አንተምወደቀጥተኛውመንገድበርግጥትመራለህ።” (ሹራ 42፤ 52)

የህይወት መሠረቱ ሩህ ነው። ሩህ ከሌለች ህይወት የለም። ብርሃን ጨለማን ይገፋል። በሱም አንፀባራቂ የሆነ ወገግታ ይገኛል። ህያው ሊባሉ የሚችሉትም ሰዎች ቁርኣንን በመተግበር ዘውታሪ የሆኑት ናቸው። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ

لِّيُنذِرَ مَن كَانَ حَيًّا وَيَحِقَّ الْقَوْلُ عَلَى الْكَافِرِينَ [٣٦:٧٠]

“እሱመገሰጫናግልፅየሆነቁርኣንእንጂሌላአይደለም።ሕያውየሆነነንሰውሊገስፅበት።” (ያሲን 36፤70)

ከሃዲያን ግን ሙታኖች ናቸውና አይሰሙም። ይህ ማስጠንቀቅያም ጠቃሚነቱ ለህያውያን እንጂ ለነሱ አይደለም። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَجِيبُوا لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ لِمَا يُحْيِيكُمْ [٨:٢٤]

“እናንተያመናችሁሆይ! መልእክተኛውህያውወደሚያደርጋችሁነገርበጠራችሁጊዜለአላህናለመልእክተኛውጥሪምላሽስጡ።” (አል አንፋል 8፤ 24)

ትክክለኛ ህይወት የሚገኘው ለአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላና ለመልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም በመታዘዝ ነው። ከቁርኣን ጋር የሚኖር ቀልብ እሱ ምንጊዜም ህያው የሆነ ቀልብ ነው። በውስጡ ቁርኣን የማይቀራበት ቤትና ኦና/ባዶ ቤት ሁለቱም ባዶ በመሆናቸው ተመሣሣይ ናቸው። በሀዲስ እንዲህ የሚል ዘገባ ተላልፏል።

إن الرجل الذي ليس في جوفه شيء من القرآن كالبيت الخرب )الترمذي(

“በሆዱውስጥከቁርኣንአንዳችምነገርየሌለውሰውእንደባዶቤትነው።” (ቲርሚዚ)

በሌላም ሀዲስ ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም እንዲህ ብለዋል

وإن القلب الذي ليس فيه من كتاب الله شيء، خرب كخراب البيت الذي لا ساكن له )الدارمي(

“ከአላህኪታብአንድምነገርውስጡየሌለሰውነዋሪእንደሌለውቤትባዶነው።” (ዳሪሚ)

ቁርኣን አላህ እኛን ሥርኣት የሚያስይዝበት መመሪያ ነው። በሀዲስ

ليس من مؤدب إلا وهو يحب أن يؤتى أدبه وإن أدب الله القرآن )الدارمي(

“አንድምሥርኣትየሚያስተምርአካልየለምያስተማረውሥርኣትተግባርላይእንዲውልለትየሚወድቢሆንእንጂ።የአላህሥርኣትማስያዣቁርኣንነው።” (ዳሪሚ) ተብሏል። በመሆኑም አላህ እንዲወደን የምንሻ ከሆነ በአላህ ቁርኣን መኖርና መመራት ይኖርብናል። የአላህ መልእክተኛ ሰላሁ ዐለይህ ወሠለም ባህሪያቸው ቁርኣን ነው።

ቁርኣን መቅራት (ማንበብ)

የሰው ልጆች ቁርኣን በሚቀሩበት ወቅት ድምፃቸውን ለማሣመር፣ የአቀራር ሥልታቸውን ጥሩ ለማድረግና ለፊደል አወጣጥም ጭምር እጅግ ሲጨናነቁ እለንያሉ። ይህ በርግጥም ማለፊያና ወሣኝ ነገር ቢሆንም ከዚህ በበለጠ ሊያሣስብ የሚገባው ነገር ቁርኣንን በጥልቀት ማወቅ፣ ማስተንተንና በመመሪያዎቹ መሥራቱ ነው። አብዛኛው የዛሬ ሰው በቁርኣን ከመሥራት ይልቅ በማንበቡ ላይ ብቻ ተወስኗል። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ለሰዎች የቁርኣንን መልእክት ለሌሎች ማድረስ የፈለጉ እንደሆነ ሰዎች በትክክል ይገባቸው ዘንድ እየቆራረጡና እየቆሙ ያነቡላቸው ነበር። ግልጽ ባለና ፊደል በፊደል በሚለይ መልኩም ያነቡላቸዋል። ይህም ሰዎች እንዲመከሩበትና ያስተነትኑት ዘንድ ያግዛቸዋል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ

وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا [١٧:١٠٦]

“ቁርኣንንበሰዎችላይበዝግታላይሆነህታነበውዘንድከፋፈልነው።ቀስበቀስማውረድንምአወረድነው።” (አል-ኢስራእ፤ 106)

ይህም ማለት ቁርኣን በረጅም ጊዜ ውስጥ አንቀፅ በአንቀፅ፤ በምእራፍ በመከፋፈልና ለንባብ እንዲቀል በቀስታና ጊዜ በመውሰድ የወረደ መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን ይህም በቀላሉ ለመገንዘብና በጥንቃቄ በቃል ለማስቀመጥ ይረዳል። ቁርኣን ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ሣይሆን እየተቆራረጠና በክፍፍል የወረደ መሆኑን ያሣየናል። ሁሉንም ግዴታዎች ለማሣወቅ በአንድ ጊዜ የወረደ ቢሆን ኖሮ ሰዎች ከትግበራው በሸሹ ነበር፣ መተግበሩም ይከብዳቸው ነበር። እዚህ ላይ ቂርኣት /ማንበብ/ ሲባል ዝም ብሎ ሽምደዳና ሩጫ ብቻ ሣይሆን በማስተንተን በመገንዘብ መሆን ይኖርበታል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ

كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ [٣٨:٢٩]

“ይህወዳንትያወረድነውብሩከመፅሃፍነው።አንቀፆቹንእንዲያስተነትኑናየአእምሮዎችባለቤቶችምይገሠፁዘንድ” (ሷድ፤ 29)

ይህም ማለት ብዙ መልካም ነገርና በረከት እንዲሁም የቅርቢቱ ዓለምና የመጭውን ዓለም ጥቅም የያዘ ሲሆን ማለት ነው። ከዚህም አልፎ ሰዎች የቁርኣን አንቀፆችን መልእክት እንዲያጤኑ በሷ ውስጥ ያሉትንም ድንቅ ተዓምራትና ምርጥ ጥበባት እንዲያስተነትኑ፤ የትክክለኛ አዕምሮ ባለቤት የሆኑ ሰዎች እንዲመከሩበት ነው። ሀሠን አልበስሪ እንዲህ ይላሉ

والله ما تدبّـُره بحفظ حروفه وإضاعة حدوده حتى إن أحدهم ليقول: والله لقد قرأت القرآن فما أسقط منه حرفًا، وقد أسقطه والله كله، ما يُرى للقرآن عليه أثر في خلق ولا عمل..”

“ወላሂማስተንተንሲባልማለትፊደላቱንመሸምደድናድንበሩንመጣስአይደለም።በዚህምየተነሣአንዲህየሚሉአሉ ‘ወላሂቁርኣንቀርቻለሁአንድንምፊደልሣልጥል።’ እኔምእላለሁ ‘ወላሂበርግጥሁሉንምጥለውታል፤በሥራምይሁንበሥነምግባርበነሱላይአንድምየቁርኣንምልክትለማየትእስኪቸግርድረስ’።”

በሰፍወት አተፋሲር ከሙጃሂድ እንደተዘገበው

يُؤْتِي الْحِكْمَةَ مَن يَشَاءُ وَمَن يُؤْتَ الْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِيَ خَيْرًا كَثِيرًا [٢:٢٦٩]

“ጥበብንምለሚሻውሰውይሠጣል፤ጥበብንየተሠጠሰውብዙንመልካምነገርንተሠጠ።” የሚለው አንቀፅ “ቁርኣንን በትክክል ማወቅ ነው” ተብሎ ተተረጉሟል።

ቁርኣን በሚቀራበት ወቅት ከሚያስፈልጉ ነገሮች መካከል አንዱ አላህን ከእዝነቱ መጠየቅን ከቅጣቱ በመጠበቅ መጠየቅ ነው። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ቁርኣን በሚቀሩበት ወቅት በአንድም የእዝነት አንቀፅ አያልፉም ቆም ብለው ከአላህ ረህመት የለመኑ ቢሆን እንጂ። በአንድም የቅጣት አንቀፅም አያልፉም ከሷ በአላህ የተጠበቁ ቢሆን እንጂ።

ይህም በርግጥም በለሊት ሰላት ነው ተብሏል። በአጠቃላይ መልኩ ግን ቁርኣንን ስናነብ በጥልቅ ማስተንተንና ግንዛቤ መሆን ይኖርበታል። በሀዲስ

أعطوا أعينكم حظها من العبادة: النظر في المصحف والتفكر فيه، والاعتبار عند عجائبه (الجامع الصغير: 1161، ضعيف)

“ከዐይናችሁከኢባዳየድርሻዋንስጡ።ይህምሊሆንየሚችለውቁርኣንንበማስተንተንመመልከት፤ትንግርታዊመልእክቱንምጠልቆበማየትነው።” የሚል ተዘግቧል።

ቁርኣን መስማትን በተመለከተ ደግሞ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ነው ቁርኣን በሚቀራበት ወቅት ዝም እንድንልና በፀጥታ እንድናዳምጥ ያዘዘን።

وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ [٧:٢٠٤]

“ቁርአንበተነበበበትጊዜእርሱንአዳምጡ፤ፀጥበሉይታዘንላችሁዘንድ” (አል አዕራፍ 7፤ 204)።

በዚሁ ምእራፍ ዝቅ ብሎም وَلا تَكُنْ مِنْ الْغَافِلِينَ “ከዝንጉዎችአትሁን” ይላል። ይህም ቁርኣንን ማስተንተን ያለብን ህያው በሆነ ቀልብና በነቃ ሰውነት መሆን እንዳለበት ነው። ለምን ቢባል አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የሚናገረው በትክክል ለሚያዳምጡት ነውና። አላህ እንዲህ አለ፡-

إِنَّمَا يَسْتَجِيبُ الَّذِينَ يَسْمَعُونَ [٦:٣٦]

“ጥሪህንየሚቀበሉትእነዚያየሚሠሙትብቻናቸው።” (አል-አንዓም 6፤ 36)

የማያዳምጡ ሰዎች፣ መሃይሞችና አስተባባዮች ሆን ብለው ነውና የቁርኣንን መልእክት አይሠሙም፤ አይገነዘቡምም። ስለሆነም ለዚሁ ጉዳይ የሚጠቀሙባቸው የሰውነት ክፍሎቻቸውና የስሜት ህዋሣቶቻቸው ትርጉም አልባ ይሆናሉ። አላዋቂ የሆነውን ሰው ግን እውነት ይገለፅለት ዘንድ ማስታወሱ ግድ ይላል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዳለው

وَالَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِنَا صُمٌّ وَبُكْمٌ فِي الظُّلُمَاتِ [٦:٣٩]

“እነዚያበአንቀፆቻችንያስተባበሉደንቆሮዎች፣ዲዳዎችምበጨለማዎችውስጥምያሉናቸው።” (አል-አንዓም 6፤ 39)

እነኚህ ዓይነቶቹ ሰዎች በቁጥር ብዙ ሆነው እናገኛቸዋለን። አላህ ሱብህነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ

أَمْ تَحْسَبُ أَنَّ أَكْثَرَهُمْ يَسْمَعُونَ أَوْ يَعْقِلُونَ إِنْ هُمْ إِلَّا كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ سَبِيلًا [٢٥:٤٤]

“ይልቁንምአብዛኛዎቻቸውየሚሠሙወይንምየሚያውቁመሆናቸውንታስባለህን! እነርሱእንሠሣዎችእንጂሌላአይደሉምከቶውንምከነሱበበለጠመንገድንየሣቱናቸው።” (አል ፉርቃን 25፤ 44)

በሌላም አንቀፅ ቁርኣን ጠቃሚነቱ ለማን እንደሆነ ሲናገር

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِمَن كَانَ لَهُ قَلْبٌ أَوْ أَلْقَى السَّمْعَ وَهُوَ شَهِيدٌ [٥٠:٣٧]

“በዚህውስጥለርሱልብላለውወይንምእርሱ (በልቡ) የተጣደሆኖጆሮውንለጣለሰውግሣፄአለበት።”(ቃፍ 50፤ 37)

ቀልብ ንጹህ የሆነ እንደሆነ እውነታን ያገኛል፤ ማስተንተን በሚገባው ነገርም ያስተነትናል። ቀልብ ህያው ነው ሊባል የሚችለውም ነገሮችን ሲያውቅና ሲገነዘብ ነው። ግንዛቤ የሌለው ሰው ደግሞ ህይወት አለው ለማለት ይቸግራል። በአካል ቢኖርም እንኳ በውስጡ ነገሮችን መረዳት ተስኖታልና። ቁርኣን ትርጉሙን ሣይረዱና ሣያውቁ፣ ከሱ ጋርም ሣይኖሩ፣ የአላህን ጠላቶች ሣይታገሉና በመንገዱም መከራና ችግር ሣያዩ በማንበብ ብቻ ወደ ቀልብ ሊደርስ አይችልም። ቀደምት ሙስሊሞች በብዙ ጦርነቶችና ታላቅ መከራዎች ውስጥ አልፈዋል። ቁርኣንም ሁኔታቸውን በመግለፅ ይወርድ አላህ በዋለላቸው ፀጋና በድሉም ያስታውሣቸው ነበር። የያኔዎቹ ደጋግ ሰዎች ከቁርኣን ጋር በተሀጁድ /በለሊት ሰላት/ ኖረዋል። በቀንም ቁርኣን ህይወታቸው ነበር።

ቁርኣንን ማወቅና በሱም መሥራት ያስፈልጋል። ማወቅ ሲባል ደግሞ ዝም ብሎ እላይ ላዩን ማወቅ ብቻ አይደለም። እሱን ማወቅ ሰውን ለሥራ የሚያነሣሣ መሆን አለበት። ሙስሊሞች ገና ከህፃንነታቸው ጀምሮ በቁርአን አስተምህሮ ተኮትኩተው የሚያድጉት በእውቀቱ ሊሠሩበት ነው። የሚያነቡትም ለዛውን ለማጣጣም ብቻ ሣይሆን የአላህን ትእዛዛት ለመተግበርና በግልም ሆነ በጋራ ጉዳዮቻቸው ውስጥ ለሚኖሩበት ህይወት ሊጠቀሙበት ነው። በመሆኑም ትእዛዙን ተቀብለው ወዲያው እንደሰሙ ሊተገብሩት ይጣደፋሉ። ማንኛውም በግንባር ያለ ወታደር የእለት ትእዛዙን እየተቀበለ እንደሚሠራበት ሁሉ። ከበርካታ ሰሃቦች እንደተዘገበው ነቢዩ ሰላሁ ዐለይህ ወሠለም ሰሃቦችን አሥር አንቀፆችን ያቀሯቸው /ያስተምሯቸው/ ነበር፤ ወደ ሌሎቹ አሥር አንቀፆችም አያልፉም በተማሯት ውስጥ ያለውን መልእክት ተግባር ላይ ማዋላቸውን እስካላረጋገጡ ድረስ። ነቢያችን “ቁርአንንም ተግባሩንም አንድ ላይ ያስተምሩን ነበር” ይላሉ። እንዲህም ብለዋል – ሰሃቦች “አሥር አንቀፅ የተማርን እንደሆነ ሌላ አሥር አንማርም። የተማርነውን አንቀፅ ሀላል ሀራም፤ ትእዛዝና ክልከላ የተማርን ካልሆነ በቀር።”

ቁርኣንን ተግባር ላይ በማዋሉ ረገድ የአላህን መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የሚስተካከል ማንም አልነበረም። እርሣቸው በምድር ላይ የሚሄዱ ተንቀሣቃሽ ቁርኣን ነበሩ። ባህሪያቸውም ሆነ አጠቃላይ ሥነምግባራቸው ቁርኣን ነበር። የርሣቸውም ሰሃቦች ፈለጋቸውን በመከተል አንዲት የቁርኣን አንቀፅ በወረደች ቁጥር በሷ ለመሥራት ይሽቀዳደሙ ነበር። ቁርኣን ለሁሉም አማኝ ከአላህ የወረደ መልእክት ነው። ከወዳጃችን የሆነ መልእክት ሲደርሰን እያንዳንዱን መስመር በጥንቃቄ እንደምናነብ እናውቃለን። ከሀያሉ ጌታችን የሆነውን መልእክትስ ምነዋ ችላ አልን!

ሀሠን አልበስሪ አንዲህ ይላሉ፡-

من كان قبلكم رأوا القرآن رسائل من ربهم، فكانوا يتدبرونها بالليل وينفذونها بالنهار.. ومن الأدب مع القرآن أن تعتبر نفسك المقصود بكل خطاب في القرآن..

“ከናንተበፊትየነበሩህዝቦችቁርኣንንከጌታቸውእንደሆነመልእክትአድርገውይመለከቱነበር።በለሊትጊዜያቸውያስተነትኑታል።በቀኑደግሞመልእክቱንተግባርላይያውሉታል።ከቁርኣንጋርሥርኣትማድረግሊባሉከሚችሉነገሮችመካከል – አላህበሚናገረውበያንዳንዱየቁርኣንአንቀፅ “እኔንነውእያናገረኝያለው” ብሎማሰብአንዱነው።”

አንድ ዓሊም “ቁርኣን የደረሠው ሰው አላህ እንዳናገረው ነው።” ብለዋል። ቁርኣን እምነት፣ መንገድና ህግጋት ሲሆን ሰዎችም በመልካም ሁኔታ እንዲኗኗሩ ያግዛል። በሀዲስ

(طوبى لمن عمل بعلمه.. (الترمذي

“..በእውቀቱየሠራሰውምንኛታደለ..” (ቲርሚዚ) የሚል መጥቷል። ሥራ የእውቀት ፍሬ ነው። እውቀት ያለውና የተማረ ሰው በተማረው ነገር መሥራት ይኖርበታል። ካልሆነ እውቀት በሱ ላይ ማስረጃ ነውና ይጠየቃል። በሀዲስ፡-

لا تزول قدم ابن آدم يوم القيامة حتى يسأل عن عمره فيم أفناه وعن شبابه فيم أبلاه وماله من أين اكتسبه وفيم أنفقه، وماذا عمل فيما علم (الترمذي)

“በትንሣኤቀንየአደምልጅእግሮችአይንቀሣቀሱምእድሜውንበምንእንደጨረሠ፤ወጣትነቱንበምንእንዳባከነ፤ገንዘቡንከየትእንዳገኘናበምንላይእንዳዋለ፤በእውቀቱምንእንደሠራእስኪጠየቅድረስ”(ቲርሚዚ) ብለዋል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም።

የቂያማ ቀን፡-

يؤتى برجل تعلم العلم وعلمه، وقرأ القرآن فأتى به فعرفعه الله نعمه فعرفها، فقال: ماذا عملت فيها؟ قال: تعلمت العلم وعلمته، وقرأت القرآن فيك، قال: كذبت، ولكنك تعلمت العلم ليقال عالم، وقرأت القرآن ليقال قارئ، فقد قيل، ثم أمر به فسحب على وجهه حتى ألقي في النار (جزء من حديث مسلم والنسائي وأحمد).

“በአንድእውቀትንየተማረናያስተማረእንዲሁምቁርኣንንበቀራናአላህምፀጋውንባሣወቀውሰውይመጣል።እሱም ‘(ባወቅከው /በተማርከው/) ምንሠራህበት?’ ተብሎይጠየቃል።ሰውዬውም ‘እውቀትንተማርኩአስተማርኩ።ላንተምብዬቁርኣንንቀራሁ’ በማለትይመልሣል። ‘የለምዋሽተሃልነገርግንየተማርከዉዓሊም /አዋቂ/ እንድትባልነው።የቀራሀውምቃሪእ /ቁርኣንንያውቃል/ እንድትባልነው።ያተብሎልሃል።’ ይባላል።ከዚያምእንዲያዝይታዘዝናተወስዶበፊቱእሣትውስጥእንዲወረወርይደረጋል።” (ሙስሊም፣ ነሳኢና አህመድ)

በአንድ ወቅት ታላቁ ዓሊም ኢብራሂም አብኑ አድሀም ተጠየቁ “ለምንድነው ዱዓእ እያደረግን ምላሽ የማናገኘው” እርሣቸውም “በአምስት ምክኒያት ነው” በማለት ከነዚያ ውስጥ “ቁርኣንን ትቀራላችሁ ነገር ግን በውስጡ በያዘው ነገር አትሠሩም” የሚለው ተጠቅሷል።

ቁርኣን መስማት የሚያሣድረው ተፅእኖ

ሙእሚኖች የታላቁን ጌታ ንግግር በሰሙ ጊዜ በሱ ውስጥ ባለው የቃል ኪዳን፣ የዛቻ፣ የማስፈራሪያና የማስጠንቀቂያ መልእክቶች ይነካሉ። በቁርኣን በሚያሣድረው ተፅእኖ ከሚታዩ ምልክቶች መካከል እነኚህ ይጠቀሣሉ

1.  إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ [٨:٢]

“ፍፁምምእመናንአነዚያየአላህበተወሣጊዜልቦቻቸውየሚፈሩትበነሱምላይአንቀፆቻችንበተነበቡጊዜእምነትንየሚጨምሩላቸውበጌታቸውምላይብቻየሚመኩትናቸው።” (አል-አንፋል 8፤ 2) ይህም ማለት ቁርኣንን በሚያነቡበት ወቅት ማለትም ልባቸው ትፈራለች ትደነግጣለች ማለት ነው።

2.تَقْشَعِرُّ مِنْهُ جُلُودُ الَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ ثُمَّ تَلِينُ جُلُودُهُمْ وَقُلُوبُهُمْ إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ  [٣٩:٢٣]

“ከርሱ (ግሣፄ ) ጌታቸውንየሚፈሩሰዎችቆዳዎቻቸውይኮማተራሉ፤ከዚያምቆዳዎቻቸውናልቦቻቸውወደአላህበማስታወስይለዝባሉ።” (ዙመር፤ 23) ማለትም ቆዳቸው ከፍራቻ የተነሣ ኩምትር ይላል። ኋላም እዝነቱንና ርህራሄውን ስታስብ ተመልሣ ትለሠልሣለች። የቅጣት አንቀፅ ሲወሣ ትሸማቀቃለች፤ የእዝነቱ አንቀፅ ሲነሣ ደግሞ ቀልብም ሆነ የሰውነት ቆዳቸው ይፍታታል ማለት ነው።

3. إِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُ الرَّحْمَٰنِ خَرُّوا سُجَّدًا وَبُكِيًّا [١٩:٥٨]

“የአልረሕማንአንቀጾችበነሱላይበተነበቡጊዜሰጋጆችናአልቃሾችኾነውይወድቃሉ” (መርየም 19፤58) ይህ ስለ ነቢያት የተገለፀው ሲሆን ከነዚያ ምርጥ ምሣሌዎችና መሪዎች ጋር ለመሆን መጣጣር ያስፈልጋል። የአላህ አናቅፆች በሚነበቡበት ጊዜ ከሚያለቅሱትና ሲጁድ ከሚወርዱት ለመሆን መትጋት ይኖርብናል። በአንድ ወቅት ዐብዱላህ ለነቢዩ ቁርኣን ቀራላቸው ሱረቱ ኒሣእ

فَكَيْفَ إِذَا جِئْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ بِشَهِيدٍ وَجِئْنَا بِكَ عَلَىٰ هَٰؤُلَاءِ شَهِيدًا [٤:٤١]

“ከሕዝቦችምሁሉመስካሪንባመጣንጊዜአንተንምበእነዚህላይመስካሪአድርገንበምናመጣህጊዜ (የከሓዲዎችኹኔታ) እንዴትይኾን?” (አኒሳእ 4፤41) የሚለው አንቀፅ እስኪደርስ ድረስ። በዚህን ጊዜም ነቢዩ “አቁም” አሉት። ዐብዱላህ ቀና ብሎ ወደ አላህ መልእክተኛ ሲመለከት ሁለቱ ዐይናቸው በእንባ ታጥበው አገኛቸው።

ኢማም ነወዊ ረሂመሁሏህ:-

“ቁርኣንበሚቀራበትጊዜማልቀስየአዋቂዎችምልክትየደጋግሰዎችምመለያነው” ብለዋል።

ኢማም አልገዛሊም:-

“ቁርኣንንበሚያነቡበትጊዜማልቀሱየተወደደነው።ይህንንምማግኘትየሚቻለውቀልብንበሀዘንናበፍራቻስሜትውስጥበማስገባትየቁርኣንንማስጠንቀቂያዎቹን፣ቅጣቶችንናያለፉትንታሪኮችበማስታወስናበማስተንተንነው።ወደራስበመመለስምያሉበትንከአላህየመራቅናየመዘናጋትሁኔታበማስታወስቀልብንበሀዘንመሙላትያስፈልጋል።ይህሁሉለቀልብፍራቻንናለቅሦንየማያመጣላትከሆነባለቤቱትልቅአደጋውስጥእንዳለሊያውቅይገባል።አላህይጠብቀን።”

በሀዲስ:-

لا يلج النار رجل بكى من خشية الله (الترمذي)

“ከአላህፍራቻያለቀሠችዐይንእሣትአይነካትም” (ቲርሚዚ) የሚል ተዘግቧል።

ቁርኣን በሚቀራበት ጊዜ ሌላው ተወዳጅ ነገር ዱዓእ ነው። ኡሙ ደርዳእ እንዲህ ብላለች፡-“የቆዳመኮማተርየሚሠማህከሆነበዚያንጊዜዱዓእአድርግምላሽአታጣምና”።

ዓኢሻም ረዲየሏሁ ዐንሃ “ቆዳሲሸማቀቅ፣ቀልብሲፈራ፣ዐይንስታለቅስዱዓእምላሽየሚያገኝበትጊዝነው” ብላለች።

ማንኛውም የደዕዋን አደራ መሸከም የሚፈልግ ወጣት ሁሉ ይህንኑ የቁርኣንና የዲን እንቅስቃሴ መንገድ ይዞ መጓዝ አለበት። በመልእክቶቹም ስሜቱ መነካት ይኖርበታል። በርግጥ መንገዱ ከባድ ነው። ቢሆንም ግን ቁርኣን ትክክለኛውን መንገድ ያሣያል። ወደ አላህ መንገድ የሚጠሩ የተለያዩ ሰዎች ሌሎችን ወደ ትክክለኛው መንገድና ወደ ጌታቸው ለመመለስና የአላህን ቃል ከፍ ለማድረግ ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ከሰዎች ጋር መጋፈጥና የሚያደርሱባቸውንም መቻል ግድ ይላቸዋል። ያኔ ቀደምቶቻቸው የቁርኣንን ጥፍጥና እንዳጣጣሙ ሁሉ እነሱም ያጣጥማሉ። ይህም የአላህ ችሮታ ነው። እሱ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው። ይህንኑ ችሮታውንም ለሚሻው ሰው ይሠጣል።

ጌታችን ሆይ! ቁርኣንን ለቀልባችን ማረፊ፣ ለልባችን ብርሃን፣ ለሀሣባችን ማስኬጃ፣ ለጭንቀታችን ማስወገጃ አድርግልን። ምስጋና የዓለማት ጌታ ሁሉ ለሆነው ለአላህ ይሁን።

 

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

በአሸራ ዚል ሂጃ ቀናቶች መልካምን ነገር ለመስራት ተዘጋጁ خطط لعملك الصالح في العشر من ذي الحجة

1596321 300x216 በአሸራ ዚል ሂጃ ቀናቶች  መልካምን ነገር ለመስራት ተዘጋጁ    خطط لعملك الصالح في العشر من ذي الحجة

አሥሩ የዚልሂጃ ቀናት- ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮች

ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ እጅግ በላጮች የሆኑት የመጀመሪያዎቹ አሥሩ የዚልሂጃ ወር ቀናት ናቸው። እነሆ እነኚህ ምርጥ ቀናት ከፊት ለፊታችን ተደቅነዋል። በነዚህም ቀናቶች ሙስሊሙ የአላህን ቤት ከዕባን ለመጎብኘት ያለው ጉጉቱ ድንበር አልፏል፤ በከዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ፣ በሶፋና መርዋ መካከል ለመሮጥ እና ዐረፋ ላይ ቆሞ አላህን ለመለመን ያላቸዉ ፍላጐት እጂግ የበርታ ነዉ ። የታላቁን ነቢይ መስጅድ መስጅደ-ነበዊን ለመጎብኘትና በመስጅዱ ውስጥ በተከበረው ቦታ ረውደቱ ሸሪፋ ላይ ለመስገድ እጂግ ይጓጓሉ፤ በሀሣብ ያምሣል፣  ክንፍ ቢኖረኝ  “ምነዋ ወደዚያ ወደ ተቀደሰው ምድር በበረርኩ!” ያስብላል።

ወዳጆቼ! እኛስ እነኚህ እጅግ የተባረኩና የተከበሩ ቀናቶች ከያዙት ምንዳ ለመቋደስ ምን ማድረግ እንችል ይሆን?

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘወትር በትእዛዙ በመገኘት ለዛኛዉ ሀገራቸው ለሚሰንቁ መልካም ባሮቹ በነኚህ በተባረኩ ቀናት ውስጥ ምን ዓይነት ትልቅ ምንዳ ይሆን ያዘጋጀላቸው?

የዚልሂጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ታላቅነት .

1.አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የማለባቸው ቀናት መሆናቸው

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَالْفَجْرِ ﴿١﴾ وَلَيَالٍ عَشْرٍ ﴿٢﴾ وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ ﴿٣﴾

“በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም። በጥንዱም በነጠላውም።” (አል-ፈጅር 89 1-3)

ከጃቢር ኢብኑ ዐብዱላህ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እነኚህ አሥር ቀናቶች የትኞቹ እንደሆኑ በሚያመላክተው ሀዲሣቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-

العشر عشر الأضحى، والوتر يوم عرفة، والشفع يوم النحر

“አሥሩ ማለት አሥሩ የአድሃ ቀናት ናቸው። ‘ወትር’ /ጥንዱ/ የተባለው የዐረፋ ቀን ሲሆን ‘ሸፍዕ’ /ነጠላው/ ማለት ደግሞ የነህር /የእርዱ/ ቀናት ናቸው።” ብለዋል። ሀዲሱን ኢማም ነሣኢ እና ሃኪም በሙስሊም መስፈርት መሠረት ሰሂህ ትክከለኛ ሀዲስ ነው ብለውታል።

 

2.እነኚህ ቀናትአያም መዕሉማት” /የታወቁ ቀናት/ ይባላሉ

ይህም በሚከተለው የቁርዓን አንቀፅ ውስጥ የተጠቀሠ ነው።

وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ [٢٢:٢٨]

“በታወቁ ቀኖችም ውስጥ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ” (አል-ሀጅ 22፤ 27)

“የቁርዓን ተርጓሚ” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ሰሃባ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ እነኚህ ቀናት “አሥርቱ ቀናት” ናቸው ያሉ ሲሆን በነኚህ ቀናት ውስጥ ታላቁን ጌታ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን በብዛት ማውሳት የተወደደ ነው::

3.ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮቹ

ይህም በሚከተለው ሀዲስ ውስጥ ተነግሯል። ከጃቢር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

أفضل أيام الدنيا أيام العشر، يعني: عشر ذي الحجة، قيل: ولا مثلهن في سبيل الله؟، قال ولا مثلهن في سبيل الله إلا رجل عفر وجهه في التراب، وذُكر عرفة، فقال يوم مباهاة ينزل الله تبارك وتعالى إلى سماء الدنيا، فيقول: عبادي شعثًا غبرًا ضاحين، جاءوا من كل فجٍّ عميق يسألون رحمتي، ويستعيذون من عذابي ولم يروا، فلم نر يومًا أكثر عتيقًا وعتيقة من النار

“ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮቹ አስሩ ቀናት ናቸው። ማለትም አሥሩ የዚልሂጃ ቀናት። በአላህ መንገድ ላይ መውጣትም ቢሆን የነሱ አምሣያ የለምን? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ‘በአላህ መንገድ ላይም ቢሆንም እነሱን የሚመስል የለም። ፊቱ ከአፈር የተገናኘ ሰው (በአላህ መንገድ ላይ የሞተ) ሲቀር።’ አሉ። ስለ ዐረፋም ተወሳና መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ‘እሱ የሙባሃት /አላህ በባሮቹ የሚኩራራበት/ ቀን ነው። አላህ ወደ ቅርቢቱ ዓለም ወደ ሰማ እዱንያ  ይወርድና ባሮቼ ተንጨፋረው፣ አቧራ የለበሱ ሆነውና ተጎሣቁለው እሩቅ ከሆነ አቅጣጫ ሁሉ እዝነቴን ሊጠይቁ እሷን ያላዩ ሲሆን ከእሣቴም በኔ ሊጠበቁ መጡ። ወንድም ሆነ ሴት በብዛት ከእሣት ነፃ የሚወጡበት እንደዚህ ቀን አላየንም’።” (በዛር ሀዲሱን ዘግበውታል)

4.በርካታ የሀጅ ሥራዎች የሚሠሩት በነኚህ ቀናት ውስጥ ነው

ከነኚህም መካከል የዚልሂጃ ስምንተኛ ቀን በሙዝደሊፋ ይታደራል፤ በዘጠነኛው ቀን በዐረፋ ላይ ይቆማል፤ ከዚህም በተጨማሪ ለመስዋእት የሚሆን እንሠሳት መንዳት፣ ጠጠር መወርወር፣ ፀጉር መላጨት አሊያም ማሣጠር፣ በዚልሂጃ አሥረኛው ቀን ጠዋፍ ማድረግንና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

5.የአምልኮ ዘርፍ የሆኑት ዋና ዋናዎቹ የሚሰበሰቡባቸው ቀናቶች ናቸው

ኢማም ሃፍዝ ኢብኑ ሀጀር ፈትሁልባሪ በተሠኘው ታዋቂ ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ይላሉ

والذي يظهر أن السبب في امتياز عشر ذي الحجة لمكان اجتماع أمهات العبادة فيه، وهي الصلاة والصيام والصدقة والحج، ولا يتأتى ذلك في غيره

“የዚልሂጃ አሥርቱ ቀናትን ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ቦታው ከአምልኮ ተግባራት ዋና ዋና የሚባሉት በአንድ ላይ ተሰባስበው የሚሠሩበት መሆኑ ነው። ይሀውም ሰላትን፣ ፆምን፣ ሰደቃን (ምጽዋትን) እና ሀጅን ያጠቃልላል። ከነኚህ ቀናት ውጭ እነኚህ ሁሉ ነገሮች አንድ ላይ የሚሰባሰቡበትን አጋጣሚ አናገኝም።”(ፈትሁልባሪ ቅጽ 2፣ ገጽ 462)

በነኚህ ቀናት ውስጥ ከሚወደዱ ሥራዎች መካከል

1.ሐጅና ዑምራ ማድረግ

በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ ምርጥ የአምልኮ ሥራዎች ናቸው። ምክኒያቱም የነኚህ አምልኮ ሥራዎች ትክክለኛ ወቅቱ ይህ ነውና። ከአቢሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ አሉ:-

العمرة إلى العمرة كفارة لما بينهما، والحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة

“አንደኛው ዑምራ እስከ ሌላኛው ዑምራ በመካከላቸው የተሰራ ወንጀልን ያብሣል፤ መብሩር /የተሟላ/ የሆነ ሀጅ ምንዳው ጀነት ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2.በበጎ ሥራዎች ላይ መበርታት

ከዐብዱላህ ኢበብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما مِن عمل أفضل من عمل فى هذه الأيام العشر، قالوا: ولا الجهاد؟ قال ولا الجهاد إلا رجل خرج بماله ونفسه فلم يرجع منه بشيء

“በነኚህ አሥር ቀናት ውስጥ የሚሠራ ሥራን የሚበልጥ ምንም የለም። ‘ጅሃድም ቢሆን?’ አሏቸው። እርሣቸውም ‘አዎን ጅሃድም ቢሆን ገንዘቡንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ያልተመለሰ ሰው ብቻ ሲቀር።’ አሉ።” (ኢማም አህመድና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

እንዲሁ በሌላ ዘገባም:-

لا تطفئوا سرجكم ليالي العشر

“በአሥርቱ ቀናት ለሊቶች ውስጥ መብራታችሁን አታጥፉ።” የሚል ዘገባ የመጣ ሲሆን ይህም ትርጉሙ “በነኚህ ቀናት ውስጥ ቁርዓን ቅሩ፣ በሰላትም በርትታችሁ ቁሙ ለማለት ነው” ተብሏል።

3.ዚክር ማብዛት

ከኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:-

ما من أيام أفضل عند الله ولا العمل فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر، فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير وذكر الله، وإن صيام يوم منها يعدل بصيام سنة، والعمل فيهن يضاعف سبعمائة ضعف

“በደረጃቸውም ሆነ በውስጣቸው በሚሠራ ሥራ ከነኚህ አሥር ቀናት የሚበልጥ በአላህ ዘንድ አንድም የለም። በነሱ ውስጥ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር ማለትንና አላህን ማውሣት አብዙ። ከነሱ ውስጥ አንድ ቀን መፆም የአመት ፆምን ይስተካከላል። በነሱ ውስጥ የሚሠራ ሥራ እስከ ሰባት መቶ ድረስ እጥፍ ድርብ ይሆናል።” (በይሀቂና ኢማም አህመድ ዘግበውታል)

4.በነሱ ውስጥ ተክቢራ ማብዛት

ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እና አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) በአሥርቱ ቀናት ውስጥ “አላሁ አክበር!” እያሉ ወደ ገበያ ይወጣሉ። ሰዎችም የነሱን ተክቢራ እየተቀበሉ “አላሁ አክበር!” ይሉ ነበር። እንዲህም ብለዋል። “ዑመር በሚና በሚገኘው ቁባቸው ውስጥ ተክቢራ ያደርጉ የነበረ ሲሆን በመስጅድ ውስጥ ያሉ ሰዎችም እርሣቸውን ይሰሙና ‘አላሁ አክበር!’ ይሉ ነበር። ገበያ ውስጥ ያሉ ሰዎችም ሚና በተክቢራ እስክትናወጥ ድረስ ‘አሏሁ አክበር!’ ይሉ ነበር።” ብለዋል። (ፈትሁል ገፋር ቀጽ 5፣ ገጽ 379)

5.ሀጅ ሥራ ውስጥ ላልተሠማራ ሰው የመጀመሪያዎቹን ዘጠኝ ቀናት መፆም

ይህንንም ሀሠን፣ ኢብኑ ሲሪን እና ቀታዳህን የመሣሰሉ ታቢዒዮችን ጨምሮ በርካታ ሰሃቦች ሰርተውታል። ኢማም ነወዊ እንዲህ ብለዋል፡-

ليس في صوم هذه التسعة كراهة بل هي مستحبة استحبابًا شديدًا، لا سيما التاسع منها، وهو يوم عرفة

“አነኚህ ዘጠኝ ቀናት መፆማቸው የሚጠላ አይደለም። ባይሆን እጅግ ተወዳጅ ነገር ነው። በተለይም ዘጠነኛው ቀን። እሱም የዐረፋ ቀን ነው።” (ሸርሁል ሙስሊም ቀጽ 3፣ ገጽ 245)

ከአቢ ቀታዳህ እንደተዘገበው ደግሞ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ። እንዲህም አሉ፡-

يكفِّر السنة الماضية والباقية

“ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል።” (ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል)

6.ቁርዓንን ማንበብ

ከኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

من قرأ حرفًا من كتاب الله فله به حسنة، والحسنة بعشر أمثالها، لا أقول الم حرف، ولكن ألف حرف، ولام حرف، وميم حرف

“ከአላህ ኪታብ አንድ ፊደል ያነበበ ሰው የመልካም ምንዳ አለው። አንዱ መልካም ምንዳ አሥር ተመሣሣይ እጥፍ ይባዛል። አንድ ሰው ‘አሊፍ-ላም-ሚም’ ያለ እንደሆነ አንድ ፊደል አይደለም። ነገርግን ‘አሊፍ’ አንድ ፊደል ነው፣ ‘ላምም’ አንድ ፊደል ነው፣ ‘ሚምም’ አንድ ፊደል ነው።” (ቡኻሪና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

7. እድህያ  ማዘጋጀት

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ [١٠٨:٢]

“ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ ለርሱም ብቻ  ሰዋም።” (አል-ከውሰር 108፤ 3)

እርድ ላይ የ አላህን ስም ብቻ ማዉሳት አለብን (ሳላህ ስም ማርድ)

ከዓኢሻ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما عمل آدمي من عمل يوم النحر أحب إلى الله من إهراق الدم، وإنها لتأتي يوم القيامة بقرونها وأشعارها وأظلافها، وإن الدم ليقع من الله بمكان قبل أن يقع على الأرض فطيبوا بها نفسًا

“ከነህር /እርድ/ ቀን ሥራዎች ውስጥ የአደም ልጅ ደምን ከማፍሠስ በላይ ወደ አላህ ተወዳጅ የሆነ አንድም ሥራ አልሠራም። እርዷም የቂያማ ቀን ከነፀጉሯና ጥፍሯ ትመጣለች። ደሙም መሬት ላይ ከማረፉ በፊት ከአላህ ዘንድ ቦታ ይይዛል። በዚህም ነፍሣችሁን አስደስቱ (ደስ ይባላችሁ)።” (ቱርሙዚ፣ ሃኪም እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል)

ኡድሂያ ማረድ የተዘጋጀ ሰው ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን የሰውነቱን መንካት የለበትም። ከኡሙ ሰለማ (ረ.ዓ) በተላለፈው ሀዲስም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡-

إِذَا دَخَلَتِ الْعَشْرُ وَأَرَادَ أَحَدُكُمْ أَنْ يُضَحِّيَ فَلا يَمَسَّ مِنْ شَعَرِهِ وَبَشَرِهِ شَيْئًا

“አንዳችሁ ኡድሂያ ለማረድ አስቦ አሥርቱ ቀናት የገቡ እንደሆነ ከፀጉሩም ሆነ ከሰውነቱ አንዳቸም ነገር አይንካ።” ብለዋል። (ሙስሊም እና ነሣኢ ዘግበውታል።) 

 

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

ነብዩን (ሶ.ዐ.ወ) ማፍቀር

564696 430302193683357 2042679377 n 300x300 ነብዩን (ሶ.ዐ.ወ) ማፍቀር

ነብዩን (ሶ.ዐ.ወ) ማፍቀር

ኢስላም የአላህና የመልዕክተኛው ፍቅር ማለት ነው። የአላህና የመልዕክተኛው ፍቅር በያንዳንዱ ሙስሊም ልቦና ውስጥ ሊሰርፅ ይገባል። ማንም ሰው ጥልቅ የሆነ የአላህና የመልዕክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) ፍቅር ሳይኖረው እውነተኛ ኢስላማዊ ህይወት ሊኖር አይችልም። ኢስላም እንዲሁ ብቻ እምነትና የቅዱሳን በዓላት ጥርቅም አይደልም።

ይልቅስ፤ በአላህና በመልዕክተኛው ፍቅር የተገነባ ግንኙነት ጭምርም እንጂ። ይህ ፍቅር የእምነታችን አካልና የእምነታችን ማሳያ ነው። እምነት ያለዚህ ፍቅር ጎዶሎ ነው። ይህ ፍቅር በጨመረ ቁጥር ደግሞ እምነታችን ይበልጥ አንጸባራቂ፣ ይበልጥ ውብና ምድርን በቆንጆ ሽታው የሚያጥናት ይሆናል።

الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِندَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنجِيلِ يَأْمُرُهُم بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ وَالْأَغْلَالَ الَّتِي كَانَتْ عَلَيْهِمْ  فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنزِلَ مَعَهُ  أُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ [٧:١٥٧]

“ለነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራት በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነብይ የኾነውን መልዕክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በርግጥ እጽፋታለሁ) በበጎ ሥራ ያዛቸዋል፤ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፤ መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፤ መጥፎ ነገሮችንም በነሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል። ከነሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያም በነሱ ላይ የነበሩትን ንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) ያነሳላቸዋል። እነዚያም እነርሱ በርሱ ያመኑ ያከበሩትም የረዱትም ያንን ከርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚድኑ ናቸው።” (አል-አዕራፍ 7፤157)

قُلْ إِن كَانَ آبَاؤُكُمْ وَأَبْنَاؤُكُمْ وَإِخْوَانُكُمْ وَأَزْوَاجُكُمْ وَعَشِيرَتُكُمْ وَأَمْوَالٌ اقْتَرَفْتُمُوهَا وَتِجَارَةٌ تَخْشَوْنَ كَسَادَهَا وَمَسَاكِنُ تَرْضَوْنَهَا أَحَبَّ إِلَيْكُم مِّنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ وَجِهَادٍ فِي سَبِيلِهِ فَتَرَبَّصُوا حَتَّىٰ يَأْتِيَ اللَّهُ بِأَمْرِهِ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ [٩:٢٤]

“አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ወንድሞቻችሁም ሚስቶቻችሁም ዘመዶቻችሁም የሰበሰባችኋቸው ሀብቶችም መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልዕክተኛው በርሱ መንገድ ከመታገልም ይበልጥ የተወደዱ እንደሆኑ አላህ ትዕዛዙን እስኪያመጣ ድረስ ተጠባበቁ በላቸው፤ አላህም አመጠኞች ሕዝቦችን አይመራም።” (አት-ተውባህ 9፤ 24)

ኢስላም የፍቅር ኃይማኖት ነው። ፍቅሩ የእውነት ፍቅር ነው። ባህሮችና ውቅያኖሶች ቀለም ፈጥረው ቃላት ቢመሰርቱ ይህን እውነተኛ ፍቅር መግለጽ ይሳናቸዋል። ኢስላማዊ ፍቅር የምር ፍቅር ነው። ልቦች የሚርበተበቱለት፣ ዓይኖች የሚያነቡለት፣ እጆችና እግሮች የሚዝሉለት፤ አዕምሮ ሙሉ ለሙሉ የሚንበረከክለት ልዩ ፍቅር። ይህ ፍቅር አላህን ቀጥሎም መልዕክተኛውን ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ከማፍቀር ጀምሮ ለምድር ፍጥረታት ሁሉ የሚሰጥ ፍቅር ነው።

ፍቅር የኢስላም ምሰሶው ነው። እምነት ያለ ፍቅር ባዶ ነው። ፈፅሞ አይሞላም። ፍቅር የእምነታችን ጥንካሬ ማሳያ መነጽር ነው። ፍቅራችን ሲያብብና ውዴታችን ሲጎመራ እምነታችን ያንፀባርቃል፤ ያበራል፤ ሽታውም ለአለም ሁሉ ይደርሳል።

ግን መልዕክተኛውን ለምን እናፈቅራለን?

መልዕክተኛው ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ልዩ ናቸው። የምርጥነት ተምሳሌት የአላህ የመጨረሻ ነቢይ። የፍቅር መፅሀፍ ናቸው። የገለጡት የሚንበረከኩለት፤ ያነበቡት የሚወዱት የውዴታ ድርሳን ነው። መልዕክተኛው የፍቅር ፅጌረዳ ናቸው። ሽታው ያውዳል፤ ሳይፈልጉትም “ውደዱኝ አፍቅሩኝ” እያለ ይጣራል። መልዕክተኛው ሙሐመድ የተሟላ የሚያደርጋቸውን ባህሪያት ሁሉ ከፈጣሪያቸው የተቸሩ ድንቅ ፍጡር ናቸው። ቃላቸውና ተግባራቸው የተጣጣሙላቸው ድንቅ በድንቅነት ብቸኛ ሰው! ያዩዋቸው ሁሉ መስክረውላቸዋል። ያደመጡት ሁሉ ልባቸውን ሰጥተዋቸዋል። ታሪካቸውን ያነበቡ ሁሉ አንብተውላቸዋል።

አራተኛው ኸሊፋ የአጎታቸው ልጅ ዐሊይ እንዲህ ይላል፡- “በድንገት ረሱልን ያያቸው ሰው በማንነታቸው ይመሰጣል፤ የሚያውቃቸው ሰው ሲያያቸው ደግሞ ያፈቅራቸዋል”። ለነገሩ ረሱልን ከማንም በላይ አላህና መላኢካዎች ያፈቅሩዋቸዋል።

ነቢዩ ሙሀመድ ለዓለማት እዝነት የተላኩ ሰው ናቸው (ራህመቱን ሊል ዐለሚን)። ከምሳሌዎች ሁሉ የላቁ ምርጥ ምሳሌ ናቸው (ኡስዋቱል ሀሰና)። የአላህን ውዴታ ድንቅ መንገድም እሳቸው ብቻ ናቸው። የኢስላም ትክክለኛ መንገድ ነቢዩ ሙሐመድን ማፍቀር ነው። እሳቸውን ማፍቀር የስኬትና የጀነት ቁልፍ ነው። ይህች ዓለም ስንት የለውጥ ሀይሎችን አሳልፋለች።ቢሆንም ግን፤ እንደ ነቢዩ ሙሐመድ ሁለገብ ሰው ሆኖ፣ ስሙ ሁሌም ለዘላለም በሁሉም አፍ የሚወሳ ማግኘት ይሳናል።

እንዴት ነቢዩ ሙሐመድን ማፍቀር እንችላለን?

ይህ ወሳኝ ጥያቄ ነው። ከባድ መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው። ፍቅር ማለት በቃላት ውርጅብኝ የሚገለፅ የስሜት ዱላ አይደለም። ነገር ግን ፍቅር እውነትን ያዘለ፣ ቁርጠኝነት የታከለበት፣ ወደ ጥሩ ስራ የሚመራ መንገድ ነው። የእውነት ፍቅር ልብን ያርበደብዳል፤ አያስቀምጥም ለመልካም ስራ ያተጋል፤ ለእውነትና ለፍትህ ዘብ ያቆማል። በጥሩ ስራም ይገለፃል። በልብ የተቃኘው እና በምላስ የተላወሰው እንዲሁም በአካላት መልካም እንቅስቃሴ የታጀበው ፍቅር፤ እውነትኛ ፍቅር ይሰኛል።

ነቢያችን (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- “እናንተ ዘንድ እኔ ከወላጆቻችሁ፣ ከልጆቻችሁና፣ ከሰው ልጆች ሁሉ በላይ ተወዳጅ እስካልሆንኩኝ ድረስ የአንዳችሁም እምነት አልሞላም”   (ቡኻሪ)።

የነቢዩ ፍቅር ደስታን ይለግሳል፣ በሀሴት ይሞላል። የምር ያዝናናል ወደ ቀጥተኛውም መንገድ ይመራል። እስቲ እነዚህን ቀጥሎ የተጠቀሱትን አምስት ነጥቦች ልብ እንበላቸው።

1. የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክንና ፈለግ (ሱና) እንማር። ህይወታቸውን ስናውቀው ይበልጥ እናፈቅራቸዋለን። ፈለጋቸውን ስናነብ ብሎም ተግባራዊም ስናደርግ ይበልጥ እንወዳቸዋለን። የነቢዩ ሙሐመድ ፈለግ እንዲሁ የአንድና የሁለት መፅሀፎች ጥርቅም ሳይሆን የህይወት መስመር ነው። ረሱል የፍቅር መምህር ነበሩ። ሳር ቅጠሉን፣ ጠላት ወዳጃቸውን፣ ዘመድ አዝማዱን፣ የሚያፈቅሩ ድንቅ መምህር ናቸው። ይህን አይነት ስብዕና መላበስ የሚቻለው ደግሞ ስናውቀው ብቻ ነው።

قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ  وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ [٣١-٣:٣٢]

“በላቸው፡ አላህን የምትወዱ ከሆናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኃጢያታችሁንም ለናንተ ይምራልና አላህ መሃሪና አዛኝ ነው።” (አሊ ኢምራን 3፤ 31-32)

2. የፍቅራችን ማጠናከሪያ ድንቅ መሳሪያ ነውና ሁሌም ስማቸውን ስናወሳና ሲወሳ፣ የአላህ ሰላምና ሶላት ብሎም እዝነት (ሶለዋት) በርሳቸው ላይ ይሆን ዘንድ መለመን አለብን። ቁርኣን፡-

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ  يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا [٣٣:٥٦]

“አላህና መላዕክቱ በነብዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፤ እላንተ ያመናችሁ ሆይ! በርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ” (አል-አህዛብ 33፣56)።

3. ፍቅራችን ሙሉ ሊሆን ይገባዋል። እነዚያ አብረዋቸው የነብይነትን የአብዬት እንቅስቃሴ ከግብ ለማድረስ የመከራውን ቀንበር አብረዋቸው ተሸክመው ከግብ ያደረሱትን ቤተሰቦቻቸውን (አህለልበይት)፣ ድንቅ ሶሃባዎች (ባልደረባዎቻቸውን) ልንወዳቸውና ልናከብራቸው ይገባል። እንዲሁም አርአያቸውን መከተል የግድ ይላል።

4. ነብዩን መውደድ ማለት ሕዝባቸውን (ኡማቸውን) መውደድ ማለትም ጭምር ነው። ለኡማቸው አባላት ጥንቃቄ ልናደርግና ለነርሱም አንድነትና ህብረት ልንሠራ ይገባል። በማንም ሠው ላይ (በተለይም በሙስሊም ላይ) መጥፎ ነገር ልናስብ ወይም ቂም ልንይዝ አይገባም። ረሱልን የወደደ፣ እርሳቸው ያፈቀሩትን ሁሉ ያፈቅራል፤ ያከበሩትን ሁሉ ያከብራል። ነቢዩ ፍጡርን ሁሉ ይወዱና ለነሱም ይሳሱ ነበር። እኛም ለፍጡራን ሁሉ ልንሳሳና ልናዝን ይገባናል። ለአንዳቸውም የጥላቻ መንፈስ በውስጣችን ልናሳድር አይገባም። ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ያፈቅሩትን እኛ ጠልተን እንዴት የሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ወዳጅ መሆን እንችላለን? አነስ ኢብኑ ማሊክ ነቢዩ እንዲህ በማለት መከሩኝ ይላል፡- “ልጄ ሆይ! ቀንንና ምሽትህን ለማንም የጥላቻ መንፈስ ሳይኖርህ ማሳለፍን አትዘንጋ!” ከዚያም እንዲህ አሉኝ “ልጄ ሆይ! ይሄ የኔ ፈለግ ነው፣ ፈለጌን የወደደ በእርግጥ እኔን ወደደ፣ በእርግጥ እኔን የወደደ ከኔ ጋር በጀነት ይሆናል” (ቲርሚዚ)።

5. የፍጥረታት መሪው ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የተላኩት ለዓለማት እዝነት ነው። በአለም ላሉ ፍጥረታት ሁሉ እዝነት። በዚህ ቃል የታነፀ የነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ወዳጅ በእርግጥ ለሰው ልጅና ለፍጥረታት ሁሉ ያዝናል። ከዚህች ዓለም ላይ ድህነትን፣ ችግርን፣ ሰቆቃንና ረሀብን ለማጥፋት ይጥራል። ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ኢ-ፍትሀዊነትን ለማጥፋት ተልከዋል። ሙሐመድን (ሶ.ዐ.ወ) የሚወድ ሁሉ ለሰላምና ፍትህ፣ ለነፃነትና መረጋጋት ዘብ ይቆማል። ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የሰውን ልጅ ከዚያ ከባድ የእሳት ቅጣት ለመታደግ ተልከዋል። የነቢዩ አፍቃሪ ሁሌም ለሰው ልጆች የእውነትንና የስኬትን መንገድ ይሰብካል። በትህትናና በርህራሄ ወደ አላህ ይጠራል- ድንቅ ምሳሌ፣ ድንቅ እዝነት፣ ድንቅ ትህትና፣ ድንቅ ሰው፣ ከታላቅ መልዕክት ጋር!!!

 

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

ረመዳን እንዴት እንቀበለው كيف نستقبل الرمضان

314075 268497756596786 552414807 n 300x225 ረመዳን እንዴት እንቀበለው      كيف نستقبل الرمضان

 

እረመዳን በእስልምና ያለዉ ደረጃ  درجات رمضان في الاسلام

= እረመዳን በዲናችን ትልቅ ደርጃ አለዉ

1- እረመዳን ከእስልምና መሰረቶች ዉስጥ አራተኛው መሠረት ነው

  • ሸሃደቱ አና ላኢላሃ ኢለ አላህ ወአና ሙሃመድ ረሱል አላህ

  • ኢቃመቱ ሰላት  ሠላት መሥገድ

  • ኢታዉ ዘካ መጽዋት መሥጠት

  • ወሰዉም ረመዳን  የረመዳንን ወረ መፆም

  • ወሃጁል በይት ሊመን እስተጣቃ ኢለይሰቢላ (የአላህን ቤት መጐብኝት)

2- አላህ (ሱ ወ)እንዲህ ይላል፦ የረመዳን ወር ቁረን የወረደበት ወር ነዉ ይላል ።

قوله تعالى: ( شهر رمضان الذي أنزل فيه القرآن)  

3- በዚህ በረመዳን ወር ዉስጥ አንዲት ለሊት አለች ከአንድ ሺ ወር በላይ ዋጋ ያላት ። አላህ ሱ ወ አንዲህ ይላል ፦ የተላቀች ለሊት ከአንድ ሺህ ወራት ትልቃለች ።

(ليلة القدر خير من ألف شهر)  قوله تعالى :

4- በዚህ በርመዳን ወር የጃነት በሮች ይከፋፈታሉ የጀሃነም በሮች ይዘጋጋሉ ሸይጣኖችም ይታሰራሉ ።

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( إذا جاء رمضان فُتّحت أبواب الجنة ، وغُلّقت أبواب النار ، وصُفّدت الشياطين )

ነብያችን(ሰ አ ወ) አንዲህ ብለዋል ፦ እርመዳን ሲመጣ የጃነት በሮች ይከፋፈታሉ የጀሃነም በሮች ይዘጋጋሉ ሸይጣኖችም ይታሰራሉ ።

5- አነፍሉ ቱእተበሩ ከልፈርድ ሱና ሶላቶች ይርፈርድ ያህል ዋጋ ይሰጣቸዋል ሱና 2 እረካተይን ስትሰግድ ፈርድ እንደሰገድክ አድርጐ ነው እሚቆጠር ።

አንድ ፈርድ ስትሰግድ ደሞ ሰባ ፈርድ እንደሰራህ አድርጐ ይቆጠርልሃል ። ለምሳሌ ፦ አንድ ዙህር ብትሰግድ ሰባ ዙህር እንደሰገድክ አድርጐ ይቆጠራል ።

6-ለጾመኞች ኣላህ ጀነት ዉስጥ ለየት ያለ በር አዘጋጂቷል። ነብያችን አንዲህ ብለዋል ፦ ጀነት ዉስጥ አንድ በር አለ ስሙ ረያን እሚባል የዉመል ቂያማ ጾመኞች ይገቡበታል ከነሱ ዉጭ ማንም አይገባም የዉምውቂያማ ካአላህ ፊት ተሰብስበዉ ይጠራሉ እነዚያ ጾመኞች የታሉ ይቆማሉ ጀነትም እረያን በሚባለዉ በር ይገባሉ  ከገቡ በሃላ በሩ ይዘጋል ከነሱ ዉጭ ማንም አይገባም  ለጾም ለየት ያለ በር መዘጋጀቱ ጾም ለየት ያለ ደርጃ መኖሩን ያሳያል ። ከጾሞች ሁሉ ደሞ እርመዳን ነዉ ።  ነብያችን አንዲህ ብለዋል በዱንያ ላይ ጾም አብዝቶ የሄደ እረያን በሚባለዉ በር ይገባሉ ።

قال رسول الله صلى الله علية وسلم : “إِنَّ فِي الْجَنَّةِ بَابًا يُقَالُ لَهُ الرَّيَّانُ ، يَدْخُلُونَ مِنْهُ الصَّائِمُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةَ ، لا يَدْخُلُ مَعَهُمْ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ ، يُقَالُ : أَيْنَ الصَّائِمُونَ ؟ فَيَقُومُونَ ، فَيَدْخُلُونَ مِنْهُ ، فَإِذَا دَخَلَ آخِرُهُمْ ، أُغْلِقَ فَلَمْ يَدْخُلْ مِنْهُ أَحَدٌ”

7- አላህ ጅነቱን በየቀኑ ያስዉባታል እረመዳን ወር ገብቶ እስኪወጣ ድርስ ያስዉባታል ። አላህ ለጀነት እንዲህ ይላታል እነዚያ ደጋግ ባሮቸ የዱንያን ጣጣ ጨርሰዉ ወደንችኮ ይመጣሉ ስለዚህ በጥሩ ሁኔታ ልታስተናግጃቸው ይገባል ይላታል ሱባህን አላህ ። 

8- እርመዳን የመጀመሪያዉ እዝነት ነው ። ማህከለኛዉ ማህርታ ነው ። መጨርሻዉ ደግሞ ከጀሃነም ነጻ የምንሆንበት ወር ነው ።

«أول شهر رمضان رحمة، وأوسطه مغفرة، وآخره عتق من النار»

የመጃመሪያዉ10 ቀናት እረህማ (እዝነት)ነዉ ። ማህከለኛዉ 10 ቀናት መቅፊራ (አላህ ባሮቹን እሚምርበት) ነዉ ። የመጨርሻዉ10 ቀናት ደግሞ አትቁን ሚን አናር (ከጃሃነም ነጻ አዉጥቻችሃለዉ እሚልበት ቀን ነው ።

9- ተስተቅፊሩ አልመላኢካ ሊሳኢሚን ሃታ የፍጥሩን ፦ ለጾመኞች መላኢኮች እስትቅፋር ያደርጋሉ እስኪያፈጥሩ ድረስ ።

  تستغفر الملائكة للصائمين حتى يفطروا .

እረመዳንን እንዴት እንቀበለዉ   كيف نستقبل رمضان

  • Ø ነብዩስ እረመዳንን እንዴት ነው እሚቀበለው ባልደርቦቹስ እንዴት ነዉ እሚቀበሉት ።

ü   ነብያችን (ሰ ዐ ወ)እረመዳንን በትልቅ ሁኔታ ነው እሚቀበሉት የነበር ። ከረመዳን በፊት ያለዉ ፪ ወር ረጀብ ሻእባን ከዛ እረመዳን ገና ረጀብ ሲገባ አላህ ሆይ ረጀብና ሻእባንን ባርክልን ለረመዳንም አድርሰን ይላሉ ። እንዲህ ነበር ነብያችን እረመዳንን በጉጉት እሚጠባበቁት እሚቀበሉት።

  • Ø ቀደምንት ሰለፎቻችን ደግሞ ፦እረመዳን ገና ፮ ወር ሲቀርዉ ዱአ ያደርጋሉ አላህ ለርመዳን እንዲያደርሳቸዉ ። አላህ እረመዳንን ሲያደርሳቸዉ ኢባዳቸዉን አጠንክረዉ ቁረኣን ሲቀሩ ይዉላሉ አላህን ሲገዙ የአምልኮት አይነቶችን ያበዛሉ አላህን በመገዛት ያሳልፉታል ። ከዝም እረመዳን ሲወጣ ፭ ወር ይቀመጣሉ ዱአ እያደረጉ አላህ ሆይ እረመዳናቺን ተቀብለህን ይሆን እባክህ ተቀበለን እያሉ ያደርጋሉ ። ከነሱ አመቱ በሙሉ በአምልኮት ነዉ እሚያሳልፉት ።

  • Ø እያንዳንዳችንም ይህንን ታላቅ እንግዳ በትልቅ ሁኔታ ልንቀበለዉ ይገባል ። ሰላት የተወ ከንግዲህ ላለመተዉ ቶብቶ ወደ አላህ መመለስ ኣለበት የሰው ሃቅ የወሰደ መመለስ ይቅርታ በመባባል ዘመድን በመተየቅሰዉ እምናማ ሰዉ ከዚህ ቡሃላ ላለማማት ተብተንወደ አላህ መመለስ አለብን  በዚህ ታላቅ እንግዳ ህይወታችን መወየር አለብን ወደኣላህ መመለስ አለብን እንሻአላህ አላህ ይርዳንና ።

  • Ø እያንዳንዳችን እራቻችን እንመርምረዉ ስንት ሰዉ የዛሬ አመት እናጋር አብረዉ የጾሙ ነበሩ ዘንድሮግን የሉም የት ሄዱ አፈር ተጭናቸዉ ጠባብ ጉድጓድ ዉስጥ ነው ያሉት እኛን አላህ እረዳን እድል ሰጠን ስለዚህ በተዉባ ወደአላህ ልንመለስ ይገባል ንጹህ ሁነን ወደኣላህ እንመለስ ።

በረመዳን የሚወደዱ ጡሩ ጡሩ ስራዎች  الإعمال التي يستحب بالرمضان

  • Ø ቁራን በመቅራት ጠንክርን መነሳት አለብን ።

شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِيَ أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَى وَالْفُرْقَانِ 

አላህ ሱ ወ እንዲህ ይላል ፦ አላህ ትጾሙት ዘንድ የወሰነዉ የረመዳን ወር ለሰዉ ዘር መመሪያ የሆነው መለኮታዊ አመራር አዉነትን ከሃሰት ለመለየት የሚያስችሉ ግልጽ አናቅጽ የሰፈሩበት ቁርአን ነው ።                                                                                      አል በቀራ ፦185

ስለዚህ በሮመዳን ቁራን ልናበዛ ይገባል ። ቀደምት ሰለፎች በረመዳን ወር ቁራአንን በጣም ያዘወትሩ ነበር ። ጂብሪል አ ሰ በርመዳን በየለሊቱ አየወርደ ነብያቺንን ቁራን ያስተምራቸዉ ነበር ።

ኢማሙ ዙህሪ እረመዳን ሲገና አንዲህ ይላሉ ፦ እረመዳን ይህ ወር እኮ ምስኪኖችን የምናበላበት ወር ነው ቁራን የምንቀራበት ወር ነው ። አርመዳን መልካም ስራዎች የሚበዙበት ወር ነው መልካም ስራዎቺን ማብዛት አላብን ።

  • Ø ሌላዉ ደግሞ በርመዳን የሚወደደዉ ኡምራ ማድረግ ነው ።

ነብያችን እንዲህ ብለዋል ፦ በረመዳን የሚደርግ ኡምራ ከሃጅ ጋር እኩል ነዉ (ሃጂ አንዳደርግሺ ይቆጠራል )ደሞ ከነብያችን ጋር ሃጂ እንዳደርግን ይቆጠራል ።

  • Ø ሌላዉ ደሞ ዱአ ማብዛት አለብን በተለይ ልናፈጥር ስንል ዱአ ለጾመኛ ሰዉ ሙሉ ቀን ማድረጉ የተወደደ ነው ።

የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል icon sad ረመዳን እንዴት እንቀበለው      كيف نستقبل الرمضان ሦስት ሰዎች ጸሎታቸው አይመለስም ጾመኛ እስኪያፈጥር ድረስ፤ፍትሐዊ መሪ እና የተበደለ ግለሰብ።)

قال رسول الله صلى الله عليه وآله وصحبه وسلم ( ثلاثة لا تُرد دعوتهم : الصائم حتى يفطر ، والإمام العادل ، ودعوة المظلوم يرفعها فوق الغمام وتُفتح لها أبواب ُ السماء ، ويقول الرب : وعزتي وجلالي لأنك ولو بعد حين)

 قال تعالى : (وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ)

አላህ ሱ ወ እንዲህ ብላል ፦ ሙሃመድ ሆይ ፦ ባሮቸ ስለኔ በጠየቁህ ጊዜ ተከታዩን መልእክቴን አስተላልፍ ፦ እኔ ቅርብ ነኝ ። የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለው ። ስለዚህ በኔ ይመኑም ቅኑን ጎዳና ይቀበሉ ዘንድ ። 

 ومن دعوات رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا أفطر يقول : ( اللهم لك صمت ، وبك آمنت ، وعلى رزقك أفطرت ، ذهب الظمأ ، وابتلت العروق ، وثبت الأجر إن شاء الله تعالى)

  • Ø ሌላው ደግሞ ጾመኛን ማስፈጠር ይወደዳል ። ጾመኛን ማስፈጠር  ሠዋብ(ምንዳ)ያስገኛል::  

قال رسول صلى الله عليه وسلم : من فطر صائما كان له مثل أجره أنه لا ينقص من أجر الصائم شيئا .

ነብያችን እንዲህ ብለዋል አንድ ጾመኛን ያስፈጠር ልክ እንደጾመኛዉ አጂር ይኖረዋል ከጾመኛዉ ግን ምንም አይቀነስበትም የሱ አንዳለ ሁኖ ለስፈጣሪዉም የጾመኛዉን ያህል ይሰጣል

  • Ø ሌላዉ ደግሞ በርመዳን የሚወደደዉ አሊትካፍ አል ኢትካፍ ማለት ነፍስን ለአላህ ብለን ትንሽ አስረን በኢባዳ (በአምልኮት) ማቆየት ማለት ነው ። ነብያችን በርመዳን የመጨረሻ 10 ቀናትን በቲካፈ ከመስጊድ ይቆዩ ነበር ።

  • Ø አል ሰደቀቱ ፊረመዳን በርመዳን ሰደቃ መስጠት እጃቺንን መስጠት ማስለመድ አለብን ለደሃ ለምስኪን ለተጨገሩት ወገኖቻችን መርዳት አለብን ።

  • Ø ሌላዉ ደግሞ ለይለተል ቀድር እምትባል አለች በርመዳን የመጨረሻዉ ፲ ቀናት ነዉ ያለች ይችን የተክበርች ለሊት ለመግኝት መራራጥ አለብን ።

(ليلة القدر خير من ألف شهر)  قوله تعالى :

አላህ ሱ ወ አንዲህ ይላል ፦ የተላቀች ለሊት ከአንድ ሺህ ወራት ትልቃለች ።

አላህ የፈለገዉን ይመርጣል ከዚህ ሁሉ ለሊት ኣንዲት ለሊትን ለይለተል ቀድርን መርጠ ። አላህ ሱ ወ ስለመምረጥ ሲናገር ለሙሳ (ለሙሴ) እንዲህ አሉት የሙሳ ከሰዎች ሁሉ አንተን መልእክተኛ በማድረግና በማነጋገር መርጥኩህ ይላቸዋል ።

መሬምንም (ማሪያምንም) እንዲሁ በዘመና ከነበሩ ሴቶች ሁሉ እንደመርጣት ሲናገር መላኢኮችም ለመሬም እንዲህ ባሉ ጊዜ አዉሳ አንተ መሃመድ ፦ አንች መሬም ሆይ ፡ አላህ መረጠሺ አጸዳሺ በዘመንሺም ካሉ ሴቶች አንችን የበላይ አድርጐ መረጠሺ ይላታል ። አላህ የፈለገዉን ይመርጣል ። አንዱን የቲም አሳዳጊ ስንት ሃብታሞች ተቀምጠዉ አንዱን መስጊድ ሰሪ ያደርገዋል አንዱን ወደ አላህ ዳአዋ እሚያደርግ ያደርገዋል አላህ የፈለገዉን ይመርጣል ።

አላህ ሱ ወ ከሰዉ ልጆች አንብያዎችን መረጠ ከኣንብያዎች ደግሞ ሩሱሎችን መረጠ(መልእክተኞችን)ከሩሲሎች ድግሞ ኡሉል አዝም የሚባሉ ታላላቅ ነብዩች አሉ አነሱን መረጠ ታላላቅ ነብዩች ፭ ናቸዉ እነሱም ፦ ኑህ አ ሰ ፡ ኢሳ (እየሱስ) አ ሰ ፡ ሙሳ(ሙሴ) አ ሰ ፡ ኢብራሂም (አብራሃም) አ ሰ ፡ ነብያችን ሙሃመድ ሰ አ ወ እነዚህ ኡሉል አዝም ይባላሉ ታላላቅ ነብያት ። ካምስቶች ደሞ ነብያችንን ሙሃመድን ሰ አ ወ መርጠ አይነታቸዉና መደምደሚያቸዉ አደረገዉ ። ካለፉት ህዝቦች ሁሉ የነብያችንን ሙሃመድ ሰ አ ወ ህዝቦች መረጠ እናንተ በላጭ ህዝቦች ናችሁ አለ ። ከህዝቦቹ ደሞ ሳህቦችን የነብያችንን ባልደርቦች መርጠ በነብያችን እያሉ የነበሩትን የነብያችንን ጐደኞች መርጠ ።ከዛ ቡሃላ ሻሂዶችን መርጠ ባአላህ ዲን ደማቸዉ ፈሶ የሞቱትን ላላህ ብለዉ ሲዋጉ የነበሩትን መርጠ ። ከመላኢኮች ደሞ ጂብሪልን (ገብሬልን) መርጠ ። ካሃግር ደሞ መካን መረጠ ። ከቀናት የዚል ሂጃ ቀናትን መረጠ ከኢድ አል አረፋ በፊት ያለዉን ፲ ቀናት እንዲሁም እለተ ጁመአን (አርብ)ቀንን መረጠ ።  ከወራቶች ደሞ የረመዳንን ወር መረጠ ። ከለሊቶች ደሞ ከአመቱ ካለዉ ለሊት ደሞ አንዳን ለሊት መረጠ ስሟንም ለይለቱል ቀድር የተላቀች ለሊት አላት በስሞም ቁራን አወረደ (ሱረቱል ቀድር)የሚለዉ ምእራፈ አወረደ ።

  • ሌላዉ በዚህ ወር ዉስጥ ልንሰራዉ የሚገባዉ ነገር ቅያሙለይል ወሰላት ተራዊህ (የለሊት ሰላት ማብዛት ተራዊህን መስገድ)የርመዳን ለሊቶችን በኢባዳ ማሳለፍ አለብን ።

وعن أبى هريرة رضي الله عنه قال :قال رسول الله صلى الله عليه وسلم ((من صام رمضان إيماناً واحتساباً غفر الله له ماتقدم من ذنبه))رواه أحمد وأصحاب السنن.

አቡ ሁርይራ(ረ።አ)እንዳሉት የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ)እንዲህ ብለዋል ፦ ((የረመዷንን ወር ጾም አምኖበትና ከአላህ ምንዳ አገኛለሁ  በሚል ጽነእ  አቋም  የጾም ሰዉ ቀደም ሲል የፈጸማቸዉን ወንጀሎች ይቅር  ይባላል))በማለት ተናግረዋል።(በአህመድና በሱነን ተጠቅሷል።)

عن المغيرة بن شعبة رضي الله عنه قال : ” قام النبي -صلى الله عليه وسلم- حتى تورمت قدماه فقيل له: غفر الله لك ما تقدم من ذنبك وما تأخر، قال: (أفلا أكون عبدا شكوراً؟ ) ” متفق عليه واللفظ للبخاري .

وفي رواية أخرى عن عائشة رضي الله عنها أنها قالت : ” لم تصنع هذا يا رسول الله وقد غفر الله لك ما تقدم من ذنبك وما تأخر؟ فقال : (أفلا أحب أن أكون عبدا شكورا؟ ) فلما كثُرَ لحمه صلّى جالسا”.

ነብያችን ሰ አ ወ አላህ ያለፈዉን የሚመጠዉን ወጀላቸዉን የማረላቸዉ እግራቸዉ እስኪሰነጠቅ ድረስ ለሊት ይሰግዱ ነበር የአላህ መልእክተኛ ሆን አላህ ያለፈዉን የሚመጠዉን ወንጀለወን ምሮለወታል ለምን ነው እግረወ እስኪሰነጠቅ ድርስ እሚሰጉት ብለዉ ጠየቃቸዉ አሳቸውም አንዲህ በማለት መለሱ ታዲያ አመስጋኝ ባሪያ አልሆንም እንዴ አሉ ።

እና እኛም ሁሌም መልካም ሰራት ለመስራት መራራጥ አለብን ሁሌም አላህን መለመን አለብን ለረመዳን ብቻ ሳይሆን ከረመዳን ቡሃላም በዚሁ መልካም ስነምግባር እንድንቀጥል ሰላታችንን አንዳናቃጥ ቁራአናቺንን በመቅራት እንድንቀጥል የጾምነዉን አላህ አንዲቀበልልን አላሕኝ እንለምን ።

የረመዳን ወር የትኩረት አቅጣጫዎች

  1. ልቦናዎች የሚደብቁትን ሁሉ የሚያየውና የሚያውቀው አላህ (ሱ.ወ) የኢማናችንን ጥንካሬ በዚህ ፆም ሊፈትነን እንደፈለገ በመገንዘብ ከፍተኝ ትኩረት መስጠት፤

  2. ረመዳንን ስንፆም በኒያ (አስበንና ወስነን) መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ያለ ኒያ የፆመ ሰው ምንዳ የለውምና።

  3. ቀኑን በሙሉ በመኝታ ከማሳለፍ መቆጠብ አለበን።

  4. ቁርኣንን ከሌላው ጊዜ በተሻለ በብዛት መቅራት አለብን።

  5. ከፈጣሪያችን ጋር ተውባ (ወደሱ መመለስ) ማደስ ያስፈልጋል።

  6. የረመዳንን ሌሊቶች በጫወታና ጠቃሚ ባልሆኑ ነገሮች ከማሳለፍ መቆጠብ አለብን።

  7. በረመዳን ወር ዱዓ፣ ከአላህ ማህርታ መጠየቅና ወደሱ መዋደቅ ማብዛት አለብን።

  8. አምስት ወቅት ሶላቶችን በመስጂድ ጀመዐ ጠብቀን መስገድ ያስፈልጋል።

  9. ሙሉ አካላችን አላህ (ሱ.ወ) ከከለከላቸው ነገሮች በመቆጠብ መፆም ይኖርባታል።

ቁርኣን የወረደበት የረመዳን ወር ይህ ነው፤ ይህ ወር ከጀነት የሚቀረብበትና ከእሳት የሚራቅበት ጊዜ ነው። እድሜህን ሁሉ ያለ ኢባዳ ያባከንክ፣ በረመዳንና በሌላውም ጊዜ ከኢባዳ ወደ ኋላ የቀረህ፣ ዛሬ ነገ እያልክ በቀጠሮ ወደ አላህ መመለስን ያዘገየህ፣ ረመዳንንና ቁርኣንን በቸልተኝነት እያለፍክ ያለህ ሰው ሆይ! እስኪ በአላህ ይሁንብህ ንገረኛ እስከመቼ በንዲህ አይነት ህይወት ትቀጥላለህ? አይቀሬው ሞት ድንገት ከተፍ ቢል ጌታህ ፊት ምን ይዘህ ትቀርባለህ?… ከወዲሁ ቆም ብለህ ልታስብበት ይገባል!

በተከበረው ረመዳን ከምግብ ብቻ ተከልክለህ አይንህን፣ አንደበትህንና አጠቃላይ ውሎህን ያልገራሀው ወንድሜ ሆይ! ድካምህ በከንቱ እንዳይቀር እያሰብክበት ነውን? ስንት ፆመኛ አለ ከፆሙ ራሀብንና ጥምን እንጅ የማያተርፍ! ስንት ሰጋጅ አለ ከሶላቱ እንቅልፍ ማጣትና ድካምን እንጅ ሌላ የማያተርፍ! ማንኛውም ከመጥፎ ተግባርና ከወንጅል የማይከለክል ቂያም (የሌሊት ሶላት) ለባለቤቱ ከአላህ መራቅ እንጂ ሌላን አይጨምረውም፤ እንደዚሁም ማንኛውም ከሐራም የማይከለክል ፆም ለባለቤቱ መጠላትንና መከልከልን እንጂ አይጨምረውም።

ሰዎች ሆይ! የአላህን ተጣሪ ሲሰሙ ፈጣን ምላሽ ከሚሰጡ፣ የአላህ አንቀፆች ሲነበቡላቸው ልባቸው ጥርት ከሚል ሰዎች፣ ሲፆሙ ደግሞ ምላሳቸው፣ ጆሯቸውና አይኖቻቻው ከሚፆሙ ሰዎች አኳያ እኛ የት ነው ያለነው? በነሱ ፈለግ ልንከተል አይገባምን? ያአላህ! ሁኔታችንን ወደ አንተ አቤት እንላለን፤ ያአላህ! እዝነትህን አደራ! ንግግሮች እያማሩ በሄዱ ቁጥር ስራዎች እየከፉ ሄዱ፤ ያ አላህ አንተ በቂያችንና መጠጊያችን ነህ!

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment

ኢስላም ምንድነው? ما هو الاسلام ؟

393874 149484045164825 1818565999 n1 ኢስላም ምንድነው?       ما هو الاسلام ؟

ኢስላም ምንድነው?                 ما هو الاسلام ؟ 

ኢስላም ማለት በአንድ አምላክ አላህ ማመን ነው፡፡ ይህም አምላክ አንድ የሆነ ሀያል ፣ጌታ ምስልና ቅርፅ የሌለው የሆነና ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡ በአረብኛ ቋንቋ ኢስላም የሚለው ቃል ብዙ ትርጉሞች ያሉት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ራስን መስጠት፣ ማደግደግ፣ ሰላምና ደህንነት ሲሆን ሰላም ደግሞ ከአላህ መልካም ስሞች አንዱ ነው፡፡ ሙስሊም ማለት ደግሞ አላህን ለማምለክ ራሱን ለአላህ የሰጠ ሲሆን በአላህ አንድነት አምኖ በቀድሞ ዋነኛ መልክእቶች እንዲሁም በሁሉም ነቢያቶች ከአደም ጀምሮ በኑህ፣ በሙሳ ፣በኢሳ እስከ ሙሀመድ ድረስ ያመነ ሙስሊም ይባላል፡፡ ኢስላም ለሰው ልጅ ምህረት የተደነገገ  ሲሆን ይህን መልዕክት የሚያብራራ የአላህ ቃል የሆነ ቁርአን ከ1433 ዓመታት በፊት ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ምንም ለውጥ ያልታየበት ነው፡፡ ይህ መፅሐፍ ከነቢዩ ምሳሌያዊ የህይወት ተግባር(ሱና) ጋር በመሆን በሁሉም ቁሳዊና መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ ሰዎች እንዴት ለፈጠሪያቸው ትዕዛዝ ምግባራቸውን እንደሚያንፁ ያሳተምራል።

Scridb filter
Posted in All | Leave a comment