ሶላት የመተዉ አደጋ الترهيب من ترك الصلاة
አላህ(ሱ.ወ) ሶላትን ደንግጎል ። የኢስላም ምሶሶና አስካል አድርጎታል ።ነቢዩ ሙሀመድ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ፦ «የነገሩ ሁሉ ራስ ኢ
ላም ነዉ። ሶላት ምስሶዉ ነዉ።ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ጂሀድ ደግሞ ጣራዉ (ሻኛዉ ) ነዉ ።»
ከኢባዳዎች ሁሉ በቅድሚያ ግዴታ የተደረገዉ ሶላት ነዉ -ነብዩ ወደ ሰማይ ባረጉበት ሌሊት ። አዎ በዚያች በተከበረች ሌሊት ያለማንም አገናኝ (መለክት አስተላላፊ) አላህ (ሱ.ወ) ነቢዩን የሶላትን አስፈላጊነትና ግዳጅነት በቀጥታ አሳወቃቸዉ ።
ለዚህ ነዉ ሶላትን ሆን ብሎ የተወ ሰዉ ወደ ክህደትና ጥመት ደረጃ ደርሳል ወይም ከሀዲ ነዉ የሚል ብይን የሚሰጠው ።
በርግጥ ከሶላት የራቀ ሰዉ ከኢስላም ርቃል ፤ ጌታዉን አስቆጥታል ፤ ራሱንም ለጥፋት ዳረጋል ፤
መልካም ስራዉንም አዉድማል ። ቁርአን እንዲህ ይላል፦
{وأقم الصلاة طرفي النهار وزلفا من الليل إن الحسنات يذهبن السيئات ذلك ذكرى للذاكرين}
«ሶላትንም በቀን ጫፎች ;እሌሊት ክፍሎች ፈጽም ፤ መልቻም ስራዎች ሀጢአቶችን ያስወግዳሉና ፤ይህ ለተገሳጮች ግሳጤ ነዉ ።»(ሁድ-114)
إنَّ الصَلاَةَ تَنْهَى عَنِ الفَحْشَاءِ وَالْمُنْكَرِ
«….ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ ፤ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች ፤…»(አል-አንከቡት 45)
“فإذا اطمأننتم فأقيموا الصلواة إن الصلاة كانت على المؤمنين كتاناً موقوتا ”
«…በረጋሁም ጊዜሶላት አሞልታችሁ ስገዱ። ሶላት በመመናን ላይ በጊዜያት የተወስነች ግዴታ ናትና ።»(አል-ኒሳእ-103)
Scridb filter
