Rabia

Blogging For Islam

አላህን በምን መልክ ማወቅ እንችላለን?

አላህን በምን መልክ ማወቅ እንችላለን?

አላህን በምን መልክ ማወቅ እንችላለን? 

ከእውቀት ሁሉ የላቀና እጅግ የሚያኮራው አላህን ማወቅ ነው። የመንፈስ  እ ርካታና የተረጋጋ ህይወት መሰረትም ይኸው ነው።

ስለ ነቢያትና መልክተኞች ማንነት ታማኝነታቸውን የተጣለባቸውን አደራ ባህሪያቶቻቸውን የተልእኳቸውን አስፈላጊነት ያሳዩአቸውን ተአምራት እንዲሁም ለሰው ልጅ መመሪያ ይሆን ዘንድ ይዘዋቸው የመጡ መለኰታዊ መመሪያዎችን ሁሉ ልናውቅ የምንችለው በቅድሚታ አላህን ሰናውቅ ነው።

ከተጨባጩ አለም ውጭ ያሉና እንደ መላእክት አጋንንት ሩህና የመሳሰሉትን ማወቅ የምንችለውም በአላህ

` ላይ ካለን ግንዛቤ በመነሳት ነው። የህይወትን ሂደት በመካነ መቃብር ውስጥ ስለሚኖረው ሁኔታ የትንሳዔ ህይወት መቀስቀስ ሂሳብ ምንዳን መቀበል ጀነት ጀሀነም  ሰለምንላቸው ጉዳዩች ሁሉ ማወቅ የምንችለው በአንደኛ ደረጃ አላህን ስናውቅ ነው።

 

አላህን ለማወቅ ሁለት አበይት ዘዴዎችን መጠቀም እንችላለን።

አንደኛ ፦ አእምሮን በመጠቀምና ተፈጥሮን በማጤን።

ሁለተኛ ፦ የአላህን ስሞችና ባህሪያት በማጥናት።

አዎ፨ በአንድ ወገን ህሊናችንን በመጠቀም በሌላ በኩል ደግሞ መለኮታዊ ማንነቱን የሚገልፁ ስሞቹንና ባህሪያቱን በማጥናት የሰው ልጅ ፈጣሪውን ሊያውቅና ወደርሱ ሊቃረብ ይችላል።

 

አእምሮን በመጠቀም… አላህን ማወቅ

እያንዳንዱ የሰውነት ክፍል የራሱ የሆነ ሚና አለው። የአእምሮ ሚናናየስራ ድርሻ ማስተንተን መመራመርና ማገናዘብ ነው። ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን አእምሮ ስራ ይፈታል መችጫወት ያለበትን ሚና በመነፈጉም ሰውዩው ጭፍንና ግትር ይሆናል ። የህሊና ሞት ይገጥመዋል። ኢስላም አ፤ምሮ ተገቢውን ክንውን እንዲፈፅም ለማድርግ መመረመር ግራና ቀኝ መመልከትና ማጤን የእያንዳንዱ ግለሰብ ግዴታ መሆኑንም አሳውቋል።

[ قل انظروا ماذا في السموات والأرض ]

<በሰማያትና በምድር ያለውን (ታምር) ተመልከቱ በላቸው፤> (ዩኑስ፥101)

[  قل انما أعظكم بواحدة أن تقوموا لله مثنى وفراد ثم تتفكروا ]

<የምግስጻችሁ ባንዲት ነገር ብቻ ነው (እርሷም) ሁለት ሁለት፥ አንድ አንድም ኾናችሁ ለአላህ እንድትነሱ ከዚያም…መርምራችሁ እንድትረዱ ነው፤…(ሰበእ፥46)

 

የአእምሮን ፀጋ የማይቀበሉ ለተፈጠረለት አላማ የማያውሉትና የአላህን ተፈጥሮአዊ ተአምራት ተሚዘነጉ ለሆኑ ሰዎች መለኰታዊ  ዛቻ ወርዶባቸዋል። ይጠንቀቁ፨

[  وكأين من آية في السموات والأرض يمرون عليها معرضون ]

<በሰማያትና በምድርም ካለችው ምልክት፥ ብዙይቱ እሱን ከርሷ ዘንጊዎች ኾነውበርሷ ላይ ኣልፍሉ።>(ዩሱፍ፥105)

[وما تأتيهم  من أية من أيات ربهم إلا كانوا عنها معرضين]

<ከጌታቸውም ታምራት ማንኛይቱም ታምር አትመጣላቸውም ከርሷ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጅ።> (ያሲን፥46

አእምሮ ተገቢውን ሚና እንዳይጫወት ማድረግ የሰውን ልጅ ከእንስሳት ጐራ መፈረጅ ነው። ኧረ ከዚህያም በታች፦

ولقد ذرأنا لجهنم كثيرا من الجن والانس لهم قلوب  لايفقهون بها ]

 ولهم أعين لايبصرون بها ولهم آذان لايسمعون بها أولئك  كالأنعام بل

[ هم أضل أولئـك  هم الغافلون

<ከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሁነም በእርግጥ ፈጠርን ለነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው ለነሱም በሳቸው የሚያዩባቸው አይኖች አሏቸው ለነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸው እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው እነዚያን ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፤>(አል፡ አእራፍ፥179)

 

ጭፍንነት የአእምሮ ጋሬጣ ነው

ከአባቶች ከባህለና አካባቢ በዘልማድ የሚነገሩና የሚተገበሩ ድርጊቶችን ያለ ምንም ጥያቄ መጥፎና ጥሩነታቸውን ሳይመዝኑ በጭፍን መውረስና መከተል ብሎም ማስተጋባት (ተቅሊድ) የአእምሮ ጋሬጣ ነው። የህሊናን ስልጣን መጋፍት ነው። ለዚህ ነው አላህ (ሱ ወ)በቅዱስ ቁርአን አሰስገሰሱን ሁሉ የማይቀበሉና ፍሬውን ከገለባው ለመለየት የሚሞክሩትን ሲያወደስ የምንመለከተው፦

         فبشر عبادى  الذين يستمعون القول  فيتبعون أحسنه أولئـك الذين هداهم الله وأولئـك هم أولوا الألباب

<እነዚህያን ንግርን የሚያዳምጡትንና መልካሙን የሚከተሉትን (አብስር) እነዚያ እነርሱ አላህ የመራቸው ናቸው።እነዚያም እነሱ ባለ አእምሮዎች ናቸው።>(አል፡ዙመር፥17-18)

በአንፃሩ በሌሎች ጭንቅላት ማስብ የሚሹትን የትናንቱን ብቻ ጐጂ ቢሆንም እንከተላለን የሚሉትንና ጠቃሚ ለውጥ ጆሮ ዳባ ልበስ የሚሉትን ያወግዛል ቁርአን

 واذا قيل لهم لتبعوا ماأنذل الله قالوا بل نتبع ماالفينا عليه آباءنا أولو كان آباؤهم لايعقلون شيئا ولايهتدون

<ለነርሱም አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን ይላሉ አባቶቻችው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ (ይከተሉዋቸዋልን )(አል በቀራህ፥ 170)

የአእምሮአድማስናወሰን

ኢስላም እወቁ ተመራመሩ አስተንትኑ እያለ ቢያበረታታም አእምሮ ግን ወሰን የለሽ ሁሉን አዋቂና እንከን አልባ መሳሪያ ነው የሚል እምነት የለውም። እያንዳንዱ የአካል ክፍል ገደብ እንዳለው ሁሉ አእምሮአችንም የተወሰነ አድማስና ወሰን ያለው መሆን መዘንጋት የለብንም።

ኢስላም ተፈጥሮን እንድንመረምር ያስገድደናል። ሰማያትን ምድርን ከዋክብትን የሰውን ልጅ አፈጣጠር ማህበራዊ ስብጥሩን እና የመሳሰሉትንጉዳዩች የመፈላፈል ፈቃድ ሰጥቷል።  በአንድ ጉዳይ ብቻ ጊዜ ማጥፍት አንደሌለብን ያስገነዝባል  በአላህ (ዛት)(አካላዊ ውቅረት)።ለምን፨፨ከህሊና የማሰብ ሀይል በላይ ነውና!

ነቢዩ መሀመድ(ሰ አ ወ) እንዲህ ብለዋል፦ <አላህ የፈጠረውን አለም መርምሩት ስለ አላህ አካልና ውቅረት ግን አትመራመሩ። ምክንያቱም ይህን ሊገነዘብ የሚችል ሀትል የላችሁም።> (አቡ ናኢም ዘግበውታል።)

ቁርአን ዩኒቨርሱን በመቃኘት ረገድ አያሌ አንቀጾችን አስፍሯል።

[ كذلك يبين الله لكم الآيات لعلكم تتفكرون فى الدنيا  والآخرة  ]

<በቅርቢቱ አለምና በመጨረሻቱ ታስተነትኑ ዘንድ (አንቀጾችን ይገልጽላችኋል)… >(አል- በቀራህ፥220)

 

የምርምርአላማ

ኢስላም ንቃተ – ህሊናእንዲኖረን አእምሯችንን ለተፈጠረለት አላማ እንድናውል የሚሻበት ዋና ምክንያት የሰውን ልጅ ትክክለኛውን የህይወት ህግና ጐዳና ለማስያዝ ነው። የመፈጠሩን ቁምነገር ይዩኒቨርሱን ቀመርና የነገሮችን እውነተኛ ገፅታ እንዲረዳ ለማድረግ ነው። ምርምሩ የአላማችንን ጅምር ወጣኝ (ኦሪጂኔተር) የሆነውን አምላክ ህልውና ብሎም ምንነት በማስጨበጥ የጥበቦች ጥበብ የሆነውን ታላቅ ፀጋ – አላህን ማወቅ-   ማጐናፀፍ ነው።

 

 

 

አላህን ማወቅ የብልህና የንፁህ አእምሮ ፍሬ ንው። ቁርአን በተፈጥሮ አድማስ ላይ ማነጣጠር እንዳለብን የሚያሳስበው የአላህን ምሉእ ባህሪያት ግርማ ሞገሱን አልፉና ኦሜጋ የሆነ እውቀቱንና ችሎታውን መገንዘብ  እንድንችል ነው። እንዲሁም አለማችንን ሲፈጥር ረዳትና ተባባሪ ያልነበረው መሆኑንም እንድናጤን ነው። እስቲ የሚከተለውን ቁርአናዊ አንቀጽ እናስተውል፦

   قُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ وَسَلَامٌ عَلَىٰ عِبَادِهِ الَّذِينَ اصْطَفَىٰ ۗ آللَّهُ خَيْرٌ أَمَّا يُشْرِكُونَ (59) أَمَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَأَنْزَلَ لَكُمْ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَنْبَتْنَا بِهِ حَدَائِقَ ذَاتَ بَهْجَةٍ مَا كَانَ لَكُمْ أَنْ تُنْبِتُوا شَجَرَهَا ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ بَلْ هُمْ قَوْمٌ يَعْدِلُونَ (60) أَمَّنْ جَعَلَ الْأَرْضَ قَرَارًا وَجَعَلَ خِلَالَهَا أَنْهَارًا وَجَعَلَ لَهَا رَوَاسِيَ وَجَعَلَ بَيْنَ الْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ(61) أَمَّنْ يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَا تَذَكَّرُونَ (62) أَمَّنْ يَهْدِيكُمْ فِي ظُلُمَاتِ الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَمَنْ يُرْسِلُ الرِّيَاحَ بُشْرًا بَيْنَ يَدَيْ رَحْمَتِهِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ تَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ (63) أَمَّنْ يَبْدَأُ الْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُ وَمَنْ يَرْزُقُكُمْ مِنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِنْ (64) كُنْتُمْ صَادِقِينَ

< ሙሀመድ ሆይ …ምስጋና ለአላህ ይግባው በነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሰላም ይውረድ አላህ በላጭ ነውን? ወይስ ያ የሚያጋሩትን? …ወይም ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለናንት ውሀን ያወረደው? (ይበልጣል? ወይስ የሚያጋሩት) በርሱም ባለውበት የኾኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታብቅሉ ለናንተ ችሎታ ያልነበራችሁን አበቀልን ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? (የለም) ግን እነሱ (ከውነት)የሚያዘነብሉ ህዝቦች ናቸው። ውይም ያ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካካሏም ወንዞችን ያደረገ ለርሷም ጋራውዎችን ያደረገ በሁለቱ ባህሮችም(በጣፍጩና በጨው ባህር) መካከል ግርዶን ያደረገ(ይበልጣል፨ ወይስ የሚያጋሩት)?…ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። ወይም ያችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋጩ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሰጹም። ወይም ያ በየብስና በባህር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ነፍሶችንም ከዝናሙ በፊት አብሳሪ ኾነው የሚልክ(ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አላን? አላህ (በርሱ) ከሚያጋሩዋቸው ሁሉ ላቀ። ወይም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አምላክ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አማላክ  አለን?እውነተኞች እንደኾናችሁ፤ ማስረጃችሁን አምጡ በላቸው።>

(አል-ነምል፥59-64)

ታዲያ ከዚህ ቁርአናዊ መረጃ ውጭ ሌላ የጠላቀና አርኪ እማኝ ይገኝይሆና፨ የሰው ልጅ ህሊና ለእንዲህ አይነቱ አስረጅ ካልተቨነፈ ልምንና ልማን አሜን ይል ይሆን፨

[ومن لم يجعل الله له نورا فما له من نور ]

<አላህም ለርሱ ብርሀንን ያላደረገለት ሰው ለርሱ ምንም ብርሀን የለውም።>(አል- ኑር፥40)

1 Star2 Stars3 Stars4 Stars5 Stars (No Ratings Yet)
Loading...

Leave a Reply