Rabia

Blogging For Islam

አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ተውበት ለማድረግ የሚደረጉነጥቦች وجوب التوبة

አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ተውበት ለማድረግ የሚደረጉነጥቦች وجوب التوبة

አላህዘንድተቀባይነትያለውተውበት  ለማድረግየሚደረጉነጥቦች

وجوب التوبة

የተውበትግዴታነት     images (16)

ኢማም ነዋዊ (አላህ፧ሱ ወ ይዘንላቸውና) ተውበርን በተመለከት ኡለማዎች ወይም የኢስላም ታላላቅ ምሁራን ከማንኛውም አይነት ወንጀል ተውበት ማድረግ ወይም ወደ አልህ(ሱ ወ)  መመለስና ምህረትን መጠየቅ ግዴታ ነው ብለዋል ይላሉ። የተሰራው ወንጀል በአላህ(ሱ ወ) እና በግለሰቡ መካከል ከሆን፣ ማለትም የሰውን መብት የማይነካና ከሰው መብት ጋር የማይያያዝ ሆኖ ከተገኘ ግለሰቡ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ተውበት ማድረግ ይኖርበታል። እነሱም፦

1. ከሰራው ወንጀል ሙሉ ለሙሉ መውጣት ይጠበቅበታል፣

2. ወንጀሉን ወይም ሽተቱን በመስራቱ መፀፀት እና መቆጨት ይጠበቅብታል፣

3. ከዚህ በኋላ ዳግም ወንጀሉን ላለመስራት መቁረጥና ወደወንጀሉ ላለመመለስ መወሰን ይጠበቅበታል።

አንድ ሰው እነዚህን ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ ተውበት ማድረግ ሲጠበቅበት ሆኖም ግን ከነዚህ ሦስት መስፈርቶች መካከል አንዱን እንኳ ቢያጓድል ተውበቱ ወይም ወደ አላህ(ሱ ወ) ለመመለስ ያደረገው ሙከራው ትክክለኛ ላይሆንና ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል።

 

 • ነገር ግን የተፈፀመው ወንጀል ከአደም ልጆች (ከሰዎች) ጋር የሚያያዝና በነሱ መብት ላይ የተንጠለጠለ ከሆነ ከላይ የተገለጹት ሦስቱ የተውበት ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው በአራተኝነት የሚጨመር ሌላው መስፈርት ቢኖር ከሰው ጋር የተያያዘውን መብይ (ማንኛውንም ነገር) ላባለቤቱ መመለስና ይቅርታን በመጠየቅ መንፃት ነው።
 • ገንዘብ ነክ ከሆነ ለባለቤቱ መመለስ፤ ስድብ፤ የሰውን ክብር መንካትና ሀሜት፣ ወዘት ከሆን ደግሞ ጥፍተኛ ሆነው በመቅረብ ክልብ ይቅርታን መጠየቅና እንዲሁም ሰውዬው ላይ የሰራውን (የፈፀመበትን በድል ወንጀል) በመንገር ግለሰቡ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ለርሱ እራሱን አሳልፎና አመቻችቶ መስጠት ይጠበቅበታል።

በአጠቃላይ መልኩ ከተሰሩ ወንጀሎች አንፃር ለሁሉም ወንጀሎች ተገቢ በሆነ ሁኔታ ተውበት ማድረግና ምህረትን መጠየቅ ግዴታ ነው።

وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴿٣١﴾

እናተ ምእመናን ሆይ  ትድኑ ዘንድ በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፤ (ሱረህ አን ኑር፡31)

وَاسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ  ۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٌ وَدُودٌ﴿٩٠﴾

”ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት፣ ከዚያም ወደ እርሱ ተመለሱ፤ ጊታዬ አዛኝ

ወዳድ ነውና“፤ (ሱረቱ ሁድ፡90)

 

 

 

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا تُوبُوا إِلَى اللَّـهِ تَوْبَةً نَّصُوحًا عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَن يُكَفِّرَ عَنكُمْ

سَيِّئَاتِكُمْ وَيُدْخِلَكُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ

”እናንተ ያመናችሁ (ሰዎች) ሆይ ንጹህ የሆነችን ጸጸት በመጸጸት  ወደ አላህ ተመለሱ፤ ጌታችሁ ከእናንተ ኃጢአታችሁን ሊሰርዝላችሁ እና ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችን ሊያስገባችሁ ይከጅላልና፤“ (ሱረህ አት ተህሪም፡8

من أسباب قبول التوبة ومغفرة الذنوب

ተውበት  ተቀባይነት እንዲኖረውና ምህረትን ለማግኘት የሚረዱ ምክንያቶች

1) تعجيل التوبة وعدم تسويفها

1) ፍጥነትተውበት (ንሰሀ) ማድርግእናአለማዘግየት

አንድ ሰው በድንገት ወንጀል ሰርቶ ሲያበቃ ለወንጀሉ ክብደት ሰጥቶ ወዲያውኑ ምህረትን ካልጠየቀና ወደ አላህ (ሱ ወ) ካልተመለሰ ሸይጣን ይደሰታል። ጊዜውገና ነው፡ ለወደፊቱ  ትቶብታልህ (ትመለሳለህ) እያለ ያዘናገዋል። እርሱም ወንጀሉን እየተላመደ በመምጣት ለሌላ ሽተትና ጥፍት ሊዳረግ ይችላል። ለዚህም ነው ነብዩ(ሰ አ ወ) አቢ ሙሳ አል አሸዐሪይ (ረ አ) ባስተላለፈው ዘገባ እንዲህ ያሉት፦

 

 

عن أبي موس الأشعري  رضي الله عنه, عن :“ إن الله تعالى يبسط يده بالليل ليتوب مسيء النهار ويبسط يده بالنهار ليتوب مسيء الليل حتى تطلع الشمس من مغربها“

 • አላህ (ሱ ወ) ቀን ሲያጠፍ ለነበሩ ተውበታቸውን ሊቀበላቸው በለሊት (የምህረት) እጁን ይዘረጋል።ለሊት ሲያጠፍና ወንጀል ሲሰሩ ለነበሩት ደግሞ ይቅር ሊላቸው በቀን (የምህረት)እ ጁን ይዘረጋል። (ይህ ሁኔታ የሚቀጥለው) ፀሀይ ከመጥለቂያዋ (ከምእራብ)እስክትወጣ ድረስ ነው። (ሙስሊም ዘግበውታል)
 • ክዚህ በመነሳት ማንኛውም የአላህ(ሱ ወ) ባሪያ ከሰራው ውንጀልና ሽተት ለመመለስ (ተውበት) ለማድረግ  ሊቻኮል ይጠበቅበታል።ለሰራው ወንጀልምጌታውን ምህረት መጠየቅና ወደ ጌታው በፍጥነት መመለስ ይኖርበታል።

2)تكرار التوبة والاستغفار

2) በተደጋጋሚተውበትማድረግናምህረትንመጠየቅ

 • መቼምቢሆንየሰውልጅከሽተትየፀዳይሆናልተብሎአይጠበቅም።በተለያዩየሰውነትክፍሎቹየተለያዩወንጀሎችንበየአጋሚውሊሰራስለሚችልበተደጋጋሚምህረትመጠየቅ (እስቲግፍር) ማብዛትናተውበትማድረግይኖርበታል።

 

 

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال : سمعت رسول الله صلى عليه وسلميقول:“ولله إني لأ ستغفر الله , وأتوب,ليه في اليوم أكثر من سبعين مرة“   رواه البخاري

 • በዚህ ዘገባ ላይ አቡ ሁረይራ(ረ ዐ)እንዲህ ይላል፦ እኔ የአላህ መልእክተኛ(ሰ አ ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ (ወላሂ) በአላህ እምላለሁ፣ እኒ በቀን ከ70 ጊዜ በላይ አላህን ምህረት እጥይቀዋለሁ። ወደ እርሱም እመለሳለሁ።(ቡኻሪ ዘግበውታል)
 • በዚህ ዘገባ መሰረት ከኚህ ታላቅ የሰው ልጅ ሞዴል የምንማረው ዋናው ቁም ነገር ቢኖር በእያንዳንዱ የህይወት እንቅስቃሴያችን ውስጥ ወደ አላህ(ሱ ወ) መመለስ (ተውበት ማድረግ) እና ምህረትን በመጠየቅ ይበልጥ ወደርሱ መቃረብ እንዳለብን ነው።

3)التوبة قبل حضر الموت

3)ጣረሞት ከ፣አ፣ጣቱ በፊት ተውበት ማድረግ(ወደ አላህ መመለስ)

 • አላህ (ሰ ወ) ለሰው ልጅ ካለው እዚነትና ርህራሄ የተነሳ የንሰሀ(የተውበትን) በር ክፍት አድርጎታል። ስለዚህ ማንኛውም ሰው በህይወት እስካል ድረስ የተውበት (የንሰሀ)እድል ተሰጥቶታልና ሊጠቀምበት ይገባል። ነገር ግን ጥን ጥሩ እድል ሳይጠቀም ቀርቶ ሞት ከመጣበት ለከባድ ኪሳራ የሚዳረግ ይሆናል። እናም ጣረሞት ከመምጣቱ በፊት ሁሉም ተውበት(ንሰሀ) እንዲያደርግ ተጋብዟል።

عن عبدا لله بن عمر ابن الخطاب رضي الله عنهما عن النبي صلى علي الله عليه وسلم قال: ” إن الله عزوجل يقبل توبة العبد مالم يغرغر ”  رواه الترمذي

አብደሏህ ቢን ኡመር ቢን አል ኸጣብ(ረ አ) ንብዩ(ሰ አ ወ) እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦ አላህ(ሱ ወ)አንድ ባሪያ ጣርሞት ላይ እስካልሆነ ድረስ ተውበቱን ይቀበለዋል።     (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

 • ከዚህ በመነሳት አንድ የአላህ(ሱ ወ)ባሪያ ሞት፣ የሞት ጣር እንዲሁም የሞት ጣጣ እሱ ላይ ከመስፈኑ በፊት ትክክለኛ ተውበት ለማድረግና ወደ አላህ(ሱ ወ)ለመመለስ መጓጓትና ከፍተኛ ጥረት ማደረግ ትኖርበታል።

 

4) التوبة قبل أشراط الساعة

 (4የቂያማምልክቶችከመከሰታቸውበፊትተውበትማደግ

በርካታ የቂያማ ምልክቶች እንዳሉ ይታወቃል። ነገር ግን ከነኚህ ምልክቶች መካከል ታላላቅ የቂያማ ምልክቶች ናቸው የሚባሉ ፲ ዋና ዋና ክስተቶች አሉ። ከነሱ ውስጥ ከፊሎቹ ከተከሰቱ በኋላ የሚደረግ ማንኛውም ተውበት ተቀባይነት ስለሌለው ከወዲሁ ለተውበት መቻኮል ተገቢ ይሆናል። አንድ ሰው  የሚሞትበት የመጨረሻው ቁርጥ ሰአት  ከመድረሱ በፊት ተውበት ማድረጉ ከተውበት ሸርጦች አንዱ ነው። ይህን ሐሳብ የሚያጠናክርል ነብያዊ ሐዲስ ቀጥለን እንመልከት።

عن أبى هريرة رضي الله عليه وسلم :“ من تاب قبل أن تطلع الشمس من مغربها تاب الله عليه ” رواه مسلم

 • አቡ ሁረይራ(ረ አ) ባስተላለፈው ዘገባ ላይ የአላህ መልእክተኛ(ሰ አ ወ) እንዲህ ማልታቸውን ጠቅሰዋል፦ ፀሐይ ከመጥለቂያዋ (ከምእራብ) ከመውጣቷ በፊት ተውበት ያደረግ ሰው አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል። (ሙስሊም ዘግበውታል)

 

الإخلاص في التوبة والحرص عليها ومجانبة أهل الشر 9-5

 ومكان المعصية, وسؤال أهل العلم

5-9ለአላህ() ብሎተውበትማድረግ፣ከሽርክተግባሪዎችናከወንጀሉስፍራመራቅ፣ እንዲሁምየእውቅትባለቤቶችንመጠየቅ

ሁሌም ቢሆን ሰው እንደመሆናችን መጥን በተለያዩ ወንጀሎችና ከተለያዩ መጥፎ ግልሰቦች ጋር ቅርርብ ሊኖረን ይችላለ። ነገር ግን ተውበት ማድረግ ወይም ወደ አላህ መመለስ በምንፈልግበት ሰአት ከእነዚህን ሰዎችና መጥፎ ተግባር ስንፈጽምበት ከነበረው አካባቢ መራቅና መገለል ይሆናል። ለዚህም ምርጥ ምሳሌ የሚሆን ታሪክ ነብዩ(ሰ አ ወ)ይተርኩልናል። በዚህ ታሪክ ውስጥ ታልቅ የሆነን ቁም ነገር እንደምናገኝ ጽፍ አደርጋለሁ።

አቡ ሰኢድ፡ ሰኢድ ኢብን ማሊክ ኢብን ሲናን አል ኹድሪይ(ረ አ) እንዳስተላለፍት የአላህ መልእክተኛ(ሰ አ ወ) እንዲህ በማለት ተናግረዋል፦ከናንተ በፊት በነበረው ዘመን አንድ የዘጠና ዘጠኝ ሰዎችን ነፍስ ያጠፍ ሰው ነበር። (እርሱም) ምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይበልጥ አዋቂው ማን እንደሆን ጠየቀ። ወደ አንድ መናኝ ባህታዊ አምላከቱት።ከርሱ ዘንድ ሄደ ዘጠና ዝጠኝ የሰው ነፍስ እንዳጠፍና ተውበት ቢያደርግ የቀባይንት ያገኝ እንድሆን (ለማወቅ) ጠየቀው። መናኙ (ምንም ምህረት) አታገኝም አለው። (ከዚያም) እርሱን ገደለውና መቶ ሞላ።.

ከዚያም ምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይበልጥ አዋቂው ማን እንደሆነ በድጋሚ ጠየቀ። ወደ አንድ አዋቂ ሰው አመላከቱት። አንድ የመቶ ሰዎችን ህይወት ያጠፍ ሰው ተውበት ቢያደርግ ተቀባይነት ያገኝ እንደሆነ ጠየቀው። አሊሙ <አዎ፦(ተቀባይነት ያገኛል) በርሱና በተውበቱ መካከል ግርዶ የሚፈጥረው ማን ነው፧፦(አለውና ከዚያም) እገሌ ወደ ተባለ ቦታ ሂድ እዚያ ሥፍራ ላይ አላህን ብቻ የሚያመልኩ ሰዎች አሉ ከነርሱ ጋር አብረህ አላህን አምልክ ወደ ነበርክበት ሀገር አትመለስ የክፍት ሥፍራ ነውና>አለው። ወደ ተጠቆመው ሀገር ተጓዘ። መንገዱን እንዳጋመስ ሞት ነጠቀው። የእዝነት(የጀነት) እና የቅጣት(የአዛብ)መላኢኮት(እኛ እንወስደዋለን በሚል)ተሟገቱ። የጀነት መላኢኮች(እርሱ እኮ) <ቶብቶና ቀልቡን ወደ አላህ አዙሮ ነው የመጣው> አሉ። የአዛብ መላኢኮች ደግሞ(እርሱ) <በጐ ተግባር ፈጽሞ አያውቅም አሉ። አንድ መላኢካ በሰው ተመስሎ ወደነርሱ መጣ።ብይን ይሰጣቸው ዘንድ ጋበዙት። <ሁለቱ መሬቶች (የመጣበትና የሚሄድበት) ከሞተበት ስፍራ ያላቸውን ርቀት ለኩ። መሄድ ወደ ጀመረበት ስፍራ ቀረብ ብሎ አገኙት። የጀነት መላኢኮች ወሰዱት። (ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል)

 

ከዚህሀዲስከምንማራቸውቁምነገሮች

 መካከልጥቂቶቹንእንይ፦

 • የመልእክተኛው(ሰ አ ወ)በተጨባጭ ምሳሌዎች የታጀበ ድንቅ የትምህርት    አሰጣጥ ስልት፡
 •  ካለፍት ህዝቦች ክንውኖች መካከል ከኢስላም ጋር የሚጣጣሙትን መዘከር     የሚፈቀድ መሆኑን፡
 •  መላካምን መንገድ ለመከተል ዝግጁነት ያላት ልቦና በተወሰነ አጋጣሚ በስሜት በመሸነፍ የስኬትን ፍኖት ብት ስትም ወደ ትክክለኛ መስመር የመመለስ እድሏ የሰፍ መሆኑን፡
 •  እውቀት (ኢልም)ከጥቂት ኢባዳ ጋር እንኳን ቢሆን በብዙ ኢባዳዎች ከታጀበ ድንቁርና(ጃሂል) ይበልጥ ጠቃሚ ነው፤ምክንያቱም ጃሂል መልካም ተግባራትን የፈፀመ እየመሰለው ሊያጥፍና ሌሎችንም ለጥፍት ሊዳርግ ይችላል። አዋቂዎች(አሊሞች) ግን ብእውቀት ብርሀን እየተመሩ ትክክለኛውን መስመር በመያዝ ለራሳቸው ተጠቅመው ሌሎችንም ይጠቅምሉ፡
 • የተውበት ደጃፍ ክፍት ነው።ተውበት የሚያደርጉ ሰዎች ወንጀላቸው የቱንም ያህል የበዛ ቢሆንም ተቀባይነት የማግኘት እድል አላቸው።
 •  ወንጀለኞች ከወንጀላቸው እስካልታቀቡ ድርስ ከነርሱ ጋር የሚኖርንን ግንኙነት ማቋረጥ እንዲሁም አላህን ክሚፈሩ ሰዎች ጋር ግንኙነትን ማጥናከር ተገቢ ነው።
 •  የአላህ(ሱ ወ) ባሮች ወደርሱ በተውበት ሲመለሱ መልካም አርአያነት ለመከተል ከፍተኛ ጥረትና ትግል ማድረግ በዚህ ሂደት የሚገጥሙ ፈተናዎችንና ችግሮችን መሸከም ለተውበት ያለን ጉጉት የሚያሳይ ምልክት ነው።

እውነተኝነት በሁሉም የህይወት እንቅስቃሴያችን ውስጥ ሊስተዋል የሚገባ መሰረታዊ ባህሪ እንድሆነ ሁሉ ተውበትም ላይ እውነተኛና ትክክለኛ ተውበት አድራጊዎች መሆን ይጠበቅብናል። ይህም እውነተኝነት በተግባር፣ በንግ ግርና በመላው ሁኔታችን ላይ ሊስተዋል ይገባል።

እውነተኝነት የአላህን እዝነት፥ በረከትና ትሩፍትን ለማግኘት ዋናው ምክንያይ ነው። በዚህም አላህ(ሱ ወ)ልአንድ ባሪያው ተውበቱን ሊቀበለው ውንጀሉን ሊምረውና እንዲሁም ደረጃውን ከፍ ሊያደርግለት ይችላል። ኢብኑ ማሊክ ፤እና የጓደኞቹን ታሪክ በአስተማሪነት ማቅረብ ይቻላል።

ይቀጥላል …….

1 Star2 Stars3 Stars4 Stars5 Stars (No Ratings Yet)
Loading...

Leave a Reply