Article

ሐጅ “الحج”

 

ሐጅ

የሐጅና የዑምራ ትሩፋት

ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

“… ለአላህም፣ በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ በሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፣ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡”

ነቢዩም (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል፡-

“የዑምራ ሥርዓተ ጻሎት እስከ ተከታዩ የዑምራ ሥርዓተ ጻሎት ድረስ በሁለቱ መካከል ላለው ኃጢአት ማበሻ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ኃጢአትና አመጽ (መዕስያ) የሌለበትና (ነቢዩ በፈጸሙት መሰረት) በትክክል የተፈጸመ ሥርዓተ ሐጅ ከገነት በስተቀር ሌላ ምንዳ የለውም፡፡”

“ተገቢ ያልሆነ መጥፎ ነገር ከአንደበቱ ሳይወጣና የአላህን ትዕዛዝ ምንም ሳይጥስ ሐጅ ያደረገ ሰው ልክ እናቱ እደወለደችዉ ቀን ከኃጢአቶቹ ጠርቶ ይመለሳል፡፡”

“የሐጅ ሥርዓተ ጻሎት ሕጎቻችሁን ከኔ ቅሰሙ፡፡”

ለደርሶ መልስ የሚበቃህ!ሙስሊም ወንደሜ ገንዘብ በኖረህ ጊዜ የሐጅ ግዴታህን ለማውረድ ተፋጠን፡፡
ከሐጅ መልስ ስላሉት እንደ ስጦታዎች ላሉት ወጪዎች ምንም ግምት አትሰጥ፡፡
አንዴ ደርሶ ለመመለስ ችሎታ ካገኘህ በኋላ ሊደርስብህ ስለሚችለው መሰናክል አላህ ምክንያት አይቀበልም ከመታመመምህ ከመደህየትህ ወይም የአላህን ትዕዛዝ ሳትፈጽም አመጸኛ ሆነህ ከመሞትህ በፊት ሐጅህን በፍጥነት ፈጽም፣ ሐጅ ከእስላም አበይት መስረቶች አንዱ ነውና፡፡ ለሐጅና ዑምራ ግዴታ መፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ሐጁ ከአላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ንጹሕ ሐላልና ከጠራ ሀብት የተገኘ መሆን አለበት፡፡
ሴት ለሐጅም ሆነ ለሌላ ጉዞ በጋብቻ መገናኘት ከማትችለው ዘመዷ ወይም ከባሏ (ከመህረም) ጋር ካልሆነ መሣፈር ሐራም (እርም) ነው፡፡
ይህም ቀጥሎ በተመለከተው የነቢዩ (ሰዐወ) ቃል መሠረት ነው፡-
“ሊያገባት የማይችል ዘመዷ ወይም ባልዋ ከሆነ ሰው ጋር ካልሆነች በሰተቀር ሴት ብቻዋን ለጉዞ አትሳፈርም፡፡”

ከተጣላሃቸው ሰዎች ታረቅ፣ ዕዳ ካለብህ ክፈል፣ ቤተሰቦችህ በጌጣጌጥ በመኪናዎች በጣፋጭ ምግቦች በእርድና በሌሎች ነገሮችም ብኩን እንዳይሆኑ ምከራቸው፣ ተናዘዝላቸው፡፡ ይህም ቀጥሎ ከሰፈረው የአላህ ቃል በመነሳት ነው
“.. ብሉም ጠጡም፣አታባክኑም” (አል-አዕራፍ (7)፡31)
ሐጅ ሙስሊሞች የሚተዋወቁት የሚዋደዱበት ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚረዳዱበት ዓለማዊም ሆኑ
ኃይማኖታዊ ጥቅሞችን የሚቀስሙበት ትልቅ ስብሰባ (ጉባኤ) ነው፡፡
ዋነኛው ነገር ችግሮችን መፍታት ለመቻል በአላህ ረድኤት መታገዝና እሱን ብቻ መማጸንና መገዛት ነው፡፡

አላህእንዲህ ብሏልና፡-

“እኔ የምገዛው ጌታዬን ብቻ ነው፣ በርሱም አንድንም አላጋራም በል፡፡” (አል-ጂን (75)፡20)

የዑምራ ሥርዓተ-ጸሎት በማንኛውም ወቅት ሊፈጸም ሲችል በወርኃ ረመዳን ውስጥ መፈጸሙ ግን ቀጥሎ በተመለከተው ነቢያዊ ፈለግ መሰረት የበለጠ ይመረጣል፡-

“በወርኃ ረመዳን የተደረገ ዑምራ (ምንዳው) እንደ ሐጅ ይቆጠራል፡፡”

መካ በሚገኘው የተከበረው መስጊድ (መስጂደል-ሐራም) ውስጥ የሚሰገደው ሶላት ሌላ ቦታ ከሚሰገደው መቶ ሺህ ሶላት ይበልጣል፡፡ ነቢዩ (ሰዐወ) ይህን በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፡

“በዚህ መስጊድ ውስጥ የሚሰገደው ሶላት የተከበረው (የመካ) መስጂድ ብቻ ሲቀር ከተቀሩት ሌሎች መስጂዶች ውስጥ ከሚሰገደው መቶ ሺህ ሶላት ይበልጣል፡፡”

“በተከበረው መስጊድ የሚሰገድ አንድ ሶላት በዚህ መስጊድ (የመዲና መስጊድ ውስጥ ከሚሰገደው መቶ ሶላት ይበልጣል

የመጀመሪያው ዑምራ ተደርጎ ካበቃ በኋላ የሚፈጸመውና “ተመትቱዕ” በመባል የሚታወቀው የሐጅ አፈጻጸም ዓይነት እንዳያመልጥህ፡፡

ነቢዩ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋልና፡-

ከናንተ መሐል ሐጅ!“የሙሐመድ ቤተሰቦች ሆይ የሚያደርግ ሰው በሐጅ ውስጥ በዑምራ ይጀምር፡፡”

ሐጅ በማን ላይ ግዴታ ይሆናል

ሐጅ ከእስላም አበይት ማዕዘኖች አንዱ ሲሆን ግዴታ (ዋጅብ) የሚሆነው፡-

- ሙስሊም በሆነ ሰው፣
- አእምሮው ጤነኛ የሆነ፣ የአእምሮ በሽተኛ በሆነ እብድ ላይ ግዴታ አይሆንም፡፡
- ከባርነት ነፃ የሆነ ሰው፣ የሰው ተገዥ በሆነና ነፃነት በሌለው ሰው ላይ ግዴታ አይሆንም፡፡
- ላቅመ አዳም (ሔዋን) የደረሰና የደረሰች፣ በሕፃን ላይ ግዴታ አይሆንም፡፡ ሐጅ ካደረገም፣ በኋላ ሲያድግ ከግዴታው ነፃ አያደርገውም፡፡
- ጤነኛ የሆነ፣ በሽተኛ ሰው እስኪድን ድረስ ግዴታ አይሆንበትም፡
- የሀብት አቅሙ የሚፈቅድለት፣ ለሐጅ የሚያስፈልገው ገንዘብ በሌለው ድሀ ላይ ግዴታ አይሆንም፡፡
በዘመነ ሕይወት አንድ ጊዜ ብቻ፣ ከአንድ በላይ የማድረግ ግዴታ ባይኖርም ቢጨምር ምንዳውን ያገኛል፡፡
ሴት አብሮዋት የሚጓዝ ሙሕረም መገኘት፣ ሴት ባልዋ ወይም በጋብቻ ሊገናኛት የማይችል አንድ ዘመዷ አብሮዋት እንዲጓዝ ካልተገኘ ግዴታ አይሆንባትም፡፡ ነቢዩ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋልና፡-
‹ሊያገባት የማይችል ዘመዷ ወይም ባልዋ ከሆነ ሰው ጋር ካልሆነች በስተቀር ሴት ብቻዋን ለጉዞ አትሳፈርም፡፡›


This website its a part of the DA’AWA-FOCUSED NETWORK