በበጎ ነገር ያዛል ፣ ከመጥፎ ይከለክላል

በበጎ ነገር ያዛል ፣ ከመጥፎ ይከለክላል
በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል የእዋ አስኳል ነው። እናም ዳኢ ሙስሊም በመልካም የሚያዝና ከመጥፎ የሚከለክል ነው። መጥፎን ነገር የሚችል ከሆነና ሌላ መጥፎ ነገር የማያስከትል ከሆነ በእጁ ይከላከላል። ካልቻለ በምላሱ እውነቱን ይገልጻል። መጥፎውን ያወግዳል። ይህም ካልሆነለት በቀልቡ ይጠላዋል። ከስሩ ነቅሎ ሊጥለው ይዘጋጃል፧ ተከታዩ የአላህ መልእተኛ (ሰአወ) ቃል የሚያሳያው ይህንኑ ነው፦
<መጥፎ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው። ካልቻለ በምላሱ ይቀይረው። ካልሆነለት በቀልቡ (ይጥላው) ይህ የመጨረሻው የእምነት ደረጃ ነው።> (ሙስሊም)
ሙስሊም በመልካም ሲያዝና ከመጥፎ ሲከለክል ለሙስሊሞች ታማኝ የመሆኑ አካል ነው።
ዲን ማለት ታማኝነት ነውና። ዲን ማልት ታማኝነት ከሆነ፣ መመካከር፣ምተባበረ ከሆነ በመለካም ማዘዝና ከመጥፎ መከለከል የግድ ነው። ይህ ሲሆነ ተከታዩ የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) ቃል ይረጋገጣል፦
<ዲን ማለት ታማኝነት (እና ምክክር) ነው።> አሉ ለማን ትበብለው ሲጠየቁ ለአላህ፣ ለመጽሀፍ፣ ለመልእክተኛው፣ ለሙስሊም መሪዎችና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ሲሉ ተናገሩ።
ይህ ባህሪ ሙስሊምን ከግፈኞች ፊት እውነትን ሳይፈራ እንዲናገር ያደረገዋል። የዚህ ኡምማ ህልውና የተመሰረተው በእንዲህ አይነት ጀግናና ነጻ ልጆቹ ነውና። በዳይን <አንተ ግፈኛ ነህ> ማለትን በማይፈሩ ጀግኖች። እንዲህ አይነት አባላትን ኡምማው ሲያጣ አብይ ባህሪውን አጥቷል። የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) እንዲህ ብለዋል፦
<ተከታዮቼ ግፈኛ ግፈኛ ነህ ላማለት ሲፈሩ ካየህ ከነርሱ ተሰናበት።>(አህመድ)
በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ወኔና ጀግንነትን የሚረጩ በርካታ ሀዲሳዊ መክእክቶች ተላልፈዋል። መሞትን ወይም በረሀብ መሰቃየትን ሳይፈሩ በድፍረት የእውነትን መልእክት እንዲያስተላልፍ የሚያነሳሱ መልእክቶች ሰፍረዋል። ጥቂቶችን እንመልከትእ፤ የአላህ መልእክተኛ(ሰአወ) እንዲህ ብለዋል፦
<ከናንተ አንዳጩ ሰዎችን መፍራት እውነትን ከመናገር አያግደው። ምክንያቱም እውነትን መናገር የመሞቻ ጊዜን አያቃርብም።>(ተርሚዚ)
አንድ ሰው ወደነቢዩ (ሰአወ)ዘንድ ሄደ። ሚንበር ላይ ነበሩ። < ከሰዎች መካከል መለካሙ የትኛው ነው፧ ሲል ጠየቃቸው። ይበልጥ አዋቂ፣ ይበልጥ አላህን ፈሪ፣ በጥሩ የሚያዝና ከመጥፎ የሚከለክል፣ እንዲሁም ዝምድናውን የሚቀጥል> አሉ።(አህመድና ጦበራኒ)
በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል በሙስሊሙ ህብረተሰብ ስንልቦና ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጽ በመደረጉ አባላቱ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ግፈኞችን ተጻርረው ድንቅ አቋሞችን እንዲይዙ አስቻላቸወ። እጅግ የሚያስደንቁ ጀግንነቶች ተስተዋሉ። አላህ ከፉን ነገር በዝምታ የሚያልፍ ፈሪዎችን ሳይሆን ጀግኖችን እንደሚረዳ የነኝህ ጀግኖች ድርጊት ምስክር ሆነ። የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ)እንዲህ ብለዋል፦
<ክብሩን በሚጎድልበት እና መብቱ በሚነካበት ሁኔታ ውስጥ ያለን ሙስሊም ያልረዳ የአላህን እገዛ በሚሻ ሰአት አላህ እገዛውን ይነፍገዋል። ክብሩ በሚጎድልበት እና መብቱ በሚነካበት ሁኔታ ውስጥ ያለን ሙስሊም የረዳ የአላህን እገዛ በሚሻ ሰአት አላህ ይረዳዋል።>(አህመድና አቡ ዳውድ)
እናም ሙስሊም ሀቅን ከመናገር ወደ ኋላ አይልም። ግፍ ሲስፍፍ፣ ጸያፍ ነገር ሲንሰራፍ በዝምታ አይመለከትም። መጥፎን ነገር ለመቀየር ሁሌም ይጥራል። እኩይን በዝምታ በመመልከት ከአላህ ዘንድ የሚመጣን ቅጣት ለመከላከል። አቡበከር ኸሊፍ በሆኑ ጊዜ ሚንበር ላይ ወጡና አላህን አመሰገኑ ። ከዚያም እንዲህ አሉ፦
<ሰዎች ሆይ፣<እናንተ ያመናችሁ ሆይ፣ እናንተ ከተቀናችሁ የጠመመ አይጎዳችሁም።> የሚለውን የቁአን አንቀጽ ታነባላችሁ። ያለቦታው እየተጠቀማችሁበት ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
<ሰዎች እኩይ ነገርን እያዩ ካልቀየሩት አላህ በቀጣቱ ያካብባቸዋል።>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *