(ص ) بلال مؤذن الرسول ኢትዮጵዊዉ ቢላል3094170876_c05639e5b4_b
የመልክተኛው ሙሀመድ (ሙአዚን)
ባሪያ
የእስልምና ሃይማኖት በአረብ ደሴት እየተባለ በሚታወቀው አካባቢ ከመመሰቱ በፊት የዓረቦች ሁኔታ ከእንሳት የተሻለ አልነበረም።
መብላት መጠጣት መደሰት ፤ ልጅን መግደል በተለይ ሴት ልጅ ስትወለድላቸው ወደፊት የነውር ሥራ ትሰራ ይሆናል በሚል ሳቢያ በቁሟ ከነህይወቷ ይቀብሯት ነበር። የህብረተሰቡ ሁኔታ ተልቁ ትንሹን የሚበላበት በዝሙትና በመጠጥ የተመረዘ የቁማር ጨዋታ የሰፈነበት በአላህ አንድነት ሳይሆን ለጣዖታት መገዛት ነበር።
የባሪያም ሥርዓት በዓረብ ደሴት ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የሰፈነ ነበር። ሰው እንደ እቃ ይሸጥ ይለወጥ ነበር። ባሪያ ማለትም የቆዳው ቀለም የጠቆረ ብቻ ሳይሆን ነጭም ቢሆን በጦርነትና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከተማረከ ባሪያ ነው የሚባለው።
ከእለታት አንድ ቀን ጌታ ኡመያህ ኢብን ኽሊፍ የተባለ የቁረይሽ ባላባት የሆነ ጥቁር ረጂም ቀጭን የሆነ ትከሻዎቹ ትናንሽ የሆኑ ፊቱ የገረጣ ፀጉሩ ችምችም ያለውን ባሪያ አስከትሎ ካእባ አካባቢ ሲደርስ ፍጥነቱን ቀንሶ ወደ ኋላው ዞር ብሎ <ቢላል የኛን ጐሳ ሸቀጣ ሸቀጥ በሙሉ ባንተ ሃላፊነት ወደ ምድረ ሻም (ሱሪያ) ወስደህ ባለፈው ጊዜ እንደ አደረገው ደህና ትርፍ እንድታስገኝልን ተስፍ እያደረኩኝ ካልተሳካልህ ግን<<<< ብሎ ጌታ ኢመያህ ንግ ግሩም ሳይጨርስ ቢላል ፈጠን ብሎ የኔ ጌታ አትጠራጠር አለው።
በአሁኑ ጉዞ ልጄ ዓሊ ካንተ ጋር አይሄድም። ስለዚህ ሃላፊነቱን ለብቻህ ነው የምትሸከመው ብሎት ጌታ ኡመያህ ወደ ካእባ አመራ። በዚህ ጊዜ ይቁረይሽ የተከበሩ ሰዎች ዙሪያ ክብ ተቀምጠው የጋለ ውይይት ይዘው ነበር። ኡመያም ወደ ባሪያው ዘወር በማለት ከፈለከኝ ከነዚህ ሰዎች ጋር ነው የምታገኘኝ ብሎ ከተከበሩ የቁረይሸ ሰዎች ጋር አብሮ ተቀመጠ።
በዚህ ጊዜ ቢላል ታላቁ የቁረትሾች አምላክ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ሁበል ዘንድ ገጸ በረከት ይዞ ወደካእባ አመራ።
ሁበል የተባለው ጣዖት ከወርቅ የተሰራ ነው። በሁለት እግሮቹ ሰባት የሚሽከረከሩ ጣሳዎች አሉት።
ቢላል ወደ ታላቁ ሁበል በደረሰበት ጊዜ ሁለት ሰዎች ማለት ባልና ሚስት ለፍርድ ቁመው ሚስቲቱ ልጅ ታቅፍ በብዙ ሰዎች ተከበው የሁበል ካህንም ጣሳዎችን እየመታ ፍርዱን ይጠባበቁ ነበር። ጉዳዩ ባል ሚስቱነ ስለተጠራጠረ ልጁ ከሱ አብራክ የወጣ መሆኑን ፍርዱን ለታላቁ ሁበል በያኔ እንዲሰጥበት ይጠይቃል
በዚህ ጊዜ በሚስት ፊት ይታይ የነበረው ጭንቀትና መረበሽ ግልፅ ነበር። ስለዚህ የሁበልን ውሳኔ ባልና ሚስት እንዲሁም በዚያ የነበረው ህዝብ በፍርሃትና በጉጉት ይጠባበቅ ነበር። የሁበል ውሳኔም ከሰባቱ ጣሳዎች ባንጉ ላይ ተፅፎ ወጣ ውሳኔው ወጣ።ውሳኔውም ሴቷንየሚገግፍ ልጂም ከአባቱ አብራክ የተከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ስለነበረ ሴትየዋ በጣም ደስ አላት። ወደ ባለቤቷ ጠጋ ብላ በጆሮው አየህ ታላቁ አምላክ ሁበል የመጨረሻውን ፍርድ በማያጠራጥር ሁኔታ በየነ፧ አለችው።
ከባልና ሚስት ፍርድ ብኋል የተሰበሰበው ህዝብ ወደመጣበት ተበታተና። ቢላል ግን ብቻውን ቀር። ፍርሃት በተሞላበት ሁኔታ ወደ ሁበል ካህን ጠጋ ብሎ ለአምላክ ሁበል የሚጋባወን ገፀ በረከት ካበረከተ በኋላ ፈገግ በማለት ይህቺን አነስተኛ ገፀ በረከት ለታላቁ አምላካችን ሁበል ሳበረክት ለረጅሙ ጉዞ ጥበቃውና ርህራሄው እንዳይለየን ተስፍ በማድረግ ነው። አለው ቢላል። ካህኑም ገፀ በረከቱን ከተቀበል በኋላ ጣሳዎችን መምታት ጀመረ። በዚህ ጊዜ ቢላል በፍርሃት ተዋጥ። እንደፈራውም ይሁበል ውሳኔ በጣሳዎቹ ባንዱ ላይ ተፅፎ ወጣ። ውሳኔውም በዛሬው እለት ጉዞ ማድረግ የለብህም። የሚል ነበር። የአምላክ ውሳኔ ቢላልን እጅግ አዽርጐ አሳዘነው ። ካህኑም የቢላልን ድንጋጤና መረበሽ ተመልክቶ ለምን እንደገና ለሁበል ሌላ ገፀ በረከት አታበረክትለትም ችግርህን ተመልክቶ ፍርዱን ያስተካክል ይሆናል አለው። ስለዚህ እንደተባልው አደረገ ጣሳዎች ከተሽከረከሩ በኋላ የተሳካ ጉዞ ይሁንልህ የሚል ፅሁፍ ወጣ ቢላልም ደስ እያለው ወደ ጌታው ኡመያህ ወደ አለበት ቦታ አመራ።

 

የቁረይሽ ነጋዴዎች በውይይት ላይ ሳሉ ቢላል አልፎ ሲሄድ ከነሱ ጋር እንዲቀመጥ ጠየቁት ። ተቀመጠ በዚህ ጊዜ አቡበከር ኢብን አቢ ቁሃፍ ድምፅህ እንዴት አስደሳች ነው ቢላል የጉዟችንን አሰልችነትና እርዝማኔ አስረሳን ፥ አሳጠረልን አለው።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *