ሐጅ- ሥርዓትና ድንጋጌዎች

ሐጅ- ሥርዓትና ድንጋጌዎች 

إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَّقَامُ إِبْرَاهِيمَ وَمَن دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ 

“ለሰዎች (መጸለያ) መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ነው። በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አልለ። ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል። ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው። የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው።” (አሊ ዒምራን 3፤ 96-97)

ትርጓሜው

የአላህን ትእዛዝ በመቀበል፣ ውዴታውን በመፈለግ፣ ጥንታዊውን ቤት ለመዞር፣ በሶፋና መርዋ መሀል ለመሮጥ፣ ዓረፋ ሜዳ ላይ ለመቆም እና ሌሎችንም አምልኮዎች ለመፈፀም መካን ማሰብና ወደርሷ መሄድ ሐጅ ይባላል። ሐጅ ከአምስቱ የኢስላም መሰረቶች አንዱ ነው። ከእስልምና መሆኑ እያንዳንዱ ሙስሊም ሊያውቀው የሚገባ የአምልኮ ዘርፍም ነው። ሐጅ ዋጂብ (ግዴታ) አይደለም ያለ ሰው ይከፍራል፤ ከእስልምና ይወጣል። ሐጅ ግዴታ የሆነው- እንደ አብዝሀ ልሂቆች (ጅምሁረል ዑለማ) አስተያየት- ከሒጅራ በኋላ ስድስተኛው አመት ላይ ነው።

ቱሩፋቱ

በብዙ ሐዲሶች ላይ ሐጅ የሚያስገኘውን ትርፍ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አብራርተዋል። ከእነዚህ መሀል ጥቂቱን እንይ፡-

1. አቡ ሁረይራ እንደዘገቡት፡-

سئل رسول اللّه صلى الله عليه وسلم، أي الأعمال أفضل ؟ قال: “إيمان بالله ورسوله”. قيل: ثمَّ ماذا ؟ قال: “ثم جهاد في سبيل الله”. قيل: ثم ماذا ؟ قال: “ثمَّ حَج مَبْرُور

“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ‘የትኛው ስራ በላጭ ነው?’ ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ‘በአላህ ማመን!’ ብለው መለሱ። ‘ከዚያስ?’ ተባሉ። ‘በአላህ መንገድ ላይ መታገል (ጂሀድ)’ አሉ። ‘ከዚያስ?’ አሏቸው። ‘መልካም ሐጅ!’ አሉ።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል))

መልካም ሐጅ (ሐጁን መብሩር) ማለት ሐጢያት ያልተቀላቀለው ሐጅ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *