አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ተውበት ለማድረግ የሚደረጉነጥቦች وجوب التوبة

አላህዘንድተቀባይነትያለውተውበት  ለማድረግየሚደረጉነጥቦች

وجوب التوبة

የተውበትግዴታነት     images (16)

ኢማም ነዋዊ (አላህ፧ሱ ወ ይዘንላቸውና) ተውበርን በተመለከት ኡለማዎች ወይም የኢስላም ታላላቅ ምሁራን ከማንኛውም አይነት ወንጀል ተውበት ማድረግ ወይም ወደ አልህ(ሱ ወ)  መመለስና ምህረትን መጠየቅ ግዴታ ነው ብለዋል ይላሉ። የተሰራው ወንጀል በአላህ(ሱ ወ) እና በግለሰቡ መካከል ከሆን፣ ማለትም የሰውን መብት የማይነካና ከሰው መብት ጋር የማይያያዝ ሆኖ ከተገኘ ግለሰቡ ሦስት ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ተውበት ማድረግ ይኖርበታል። እነሱም፦

1. ከሰራው ወንጀል ሙሉ ለሙሉ መውጣት ይጠበቅበታል፣

2. ወንጀሉን ወይም ሽተቱን በመስራቱ መፀፀት እና መቆጨት ይጠበቅብታል፣

3. ከዚህ በኋላ ዳግም ወንጀሉን ላለመስራት መቁረጥና ወደወንጀሉ ላለመመለስ መወሰን ይጠበቅበታል።

አንድ ሰው እነዚህን ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ ተውበት ማድረግ ሲጠበቅበት ሆኖም ግን ከነዚህ ሦስት መስፈርቶች መካከል አንዱን እንኳ ቢያጓድል ተውበቱ ወይም ወደ አላህ(ሱ ወ) ለመመለስ ያደረገው ሙከራው ትክክለኛ ላይሆንና ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል።

 

 • ነገር ግን የተፈፀመው ወንጀል ከአደም ልጆች (ከሰዎች) ጋር የሚያያዝና በነሱ መብት ላይ የተንጠለጠለ ከሆነ ከላይ የተገለጹት ሦስቱ የተውበት ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው በአራተኝነት የሚጨመር ሌላው መስፈርት ቢኖር ከሰው ጋር የተያያዘውን መብይ (ማንኛውንም ነገር) ላባለቤቱ መመለስና ይቅርታን በመጠየቅ መንፃት ነው።
 • ገንዘብ ነክ ከሆነ ለባለቤቱ መመለስ፤ ስድብ፤ የሰውን ክብር መንካትና ሀሜት፣ ወዘት ከሆን ደግሞ ጥፍተኛ ሆነው በመቅረብ ክልብ ይቅርታን መጠየቅና እንዲሁም ሰውዬው ላይ የሰራውን (የፈፀመበትን በድል ወንጀል) በመንገር ግለሰቡ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ለርሱ እራሱን አሳልፎና አመቻችቶ መስጠት ይጠበቅበታል።

በአጠቃላይ መልኩ ከተሰሩ ወንጀሎች አንፃር ለሁሉም ወንጀሎች ተገቢ በሆነ ሁኔታ ተውበት ማድረግና ምህረትን መጠየቅ ግዴታ ነው።

وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴿٣١﴾

እናተ ምእመናን ሆይ  ትድኑ ዘንድ በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፤ (ሱረህ አን ኑር፡31)

وَاسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ  ۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٌ وَدُودٌ﴿٩٠﴾

”ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት፣ ከዚያም ወደ እርሱ ተመለሱ፤ ጊታዬ አዛኝ

ወዳድ ነውና“፤ (ሱረቱ ሁድ፡90)

 

 

 

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا تُوبُوا إِلَى اللَّـهِ تَوْبَةً نَّصُوحًا عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَن يُكَفِّرَ عَنكُمْ

سَيِّئَاتِكُمْ وَيُدْخِلَكُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ

”እናንተ ያመናችሁ (ሰዎች) ሆይ ንጹህ የሆነችን ጸጸት በመጸጸት  ወደ አላህ ተመለሱ፤ ጌታችሁ ከእናንተ ኃጢአታችሁን ሊሰርዝላችሁ እና ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችን ሊያስገባችሁ ይከጅላልና፤“ (ሱረህ አት ተህሪም፡8

من أسباب قبول التوبة ومغفرة الذنوب

ተውበት  ተቀባይነት እንዲኖረውና ምህረትን ለማግኘት የሚረዱ ምክንያቶች

1) تعجيل التوبة وعدم تسويفها

1) ፍጥነትተውበት (ንሰሀ) ማድርግእናአለማዘግየት

አንድ ሰው በድንገት ወንጀል ሰርቶ ሲያበቃ ለወንጀሉ ክብደት ሰጥቶ ወዲያውኑ ምህረትን ካልጠየቀና ወደ አላህ (ሱ ወ) ካልተመለሰ ሸይጣን ይደሰታል። ጊዜውገና ነው፡ ለወደፊቱ  ትቶብታልህ (ትመለሳለህ) እያለ ያዘናገዋል። እርሱም ወንጀሉን እየተላመደ በመምጣት ለሌላ ሽተትና ጥፍት ሊዳረግ ይችላል። ለዚህም ነው ነብዩ(ሰ አ ወ) አቢ ሙሳ አል አሸዐሪይ (ረ አ) ባስተላለፈው ዘገባ እንዲህ ያሉት፦

 

 

عن أبي موس الأشعري  رضي الله عنه, عن :“ إن الله تعالى يبسط يده بالليل ليتوب مسيء النهار ويبسط يده بالنهار ليتوب مسيء الليل حتى تطلع الشمس من مغربها“

 • አላህ (ሱ ወ) ቀን ሲያጠፍ ለነበሩ ተውበታቸውን ሊቀበላቸው በለሊት (የምህረት) እጁን ይዘረጋል።ለሊት ሲያጠፍና ወንጀል ሲሰሩ ለነበሩት ደግሞ ይቅር ሊላቸው በቀን (የምህረት)እ ጁን ይዘረጋል። (ይህ ሁኔታ የሚቀጥለው) ፀሀይ ከመጥለቂያዋ (ከምእራብ)እስክትወጣ ድረስ ነው። (ሙስሊም ዘግበውታል)
 • ክዚህ በመነሳት ማንኛውም የአላህ(ሱ ወ) ባሪያ ከሰራው ውንጀልና ሽተት ለመመለስ (ተውበት) ለማድረግ  ሊቻኮል ይጠበቅበታል።ለሰራው ወንጀልምጌታውን ምህረት መጠየቅና ወደ ጌታው በፍጥነት መመለስ ይኖርበታል።

2)تكرار التوبة والاستغفار

2) በተደጋጋሚተውበትማድረግናምህረትንመጠየቅ

 • መቼምቢሆንየሰውልጅከሽተትየፀዳይሆናልተብሎአይጠበቅም።በተለያዩየሰውነትክፍሎቹየተለያዩወንጀሎችንበየአጋሚውሊሰራስለሚችልበተደጋጋሚምህረትመጠየቅ (እስቲግፍር) ማብዛትናተውበትማድረግይኖርበታል።

 

 

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال : سمعت رسول الله صلى عليه وسلميقول:“ولله إني لأ ستغفر الله , وأتوب,ليه في اليوم أكثر من سبعين مرة“   رواه البخاري

 • በዚህ ዘገባ ላይ አቡ ሁረይራ(ረ ዐ)እንዲህ ይላል፦ እኔ የአላህ መልእክተኛ(ሰ አ ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ (ወላሂ) በአላህ እምላለሁ፣ እኒ በቀን ከ70 ጊዜ በላይ አላህን ምህረት እጥይቀዋለሁ። ወደ እርሱም እመለሳለሁ።(ቡኻሪ ዘግበውታል)
 • በዚህ ዘገባ መሰረት ከኚህ ታላቅ የሰው ልጅ ሞዴል የምንማረው ዋናው ቁም ነገር ቢኖር በእያንዳንዱ የህይወት እንቅስቃሴያችን ውስጥ ወደ አላህ(ሱ ወ) መመለስ (ተውበት ማድረግ) እና ምህረትን በመጠየቅ ይበልጥ ወደርሱ መቃረብ እንዳለብን ነው።

3)التوبة قبل حضر الموت

3)ጣረሞት ከ፣አ፣ጣቱ በፊት ተውበት ማድረግ(ወደ አላህ መመለስ)

 • አላህ (ሰ ወ) ለሰው ልጅ ካለው እዚነትና ርህራሄ የተነሳ የንሰሀ(የተውበትን) በር ክፍት አድርጎታል። ስለዚህ ማንኛውም ሰው በህይወት እስካል ድረስ የተውበት (የንሰሀ)እድል ተሰጥቶታልና ሊጠቀምበት ይገባል። ነገር ግን ጥን ጥሩ እድል ሳይጠቀም ቀርቶ ሞት ከመጣበት ለከባድ ኪሳራ የሚዳረግ ይሆናል። እናም ጣረሞት ከመምጣቱ በፊት ሁሉም ተውበት(ንሰሀ) እንዲያደርግ ተጋብዟል።

عن عبدا لله بن عمر ابن الخطاب رضي الله عنهما عن النبي صلى علي الله عليه وسلم قال: ” إن الله عزوجل يقبل توبة العبد مالم يغرغر ”  رواه الترمذي

አብደሏህ ቢን ኡመር ቢን አል ኸጣብ(ረ አ) ንብዩ(ሰ አ ወ) እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦ አላህ(ሱ ወ)አንድ ባሪያ ጣርሞት ላይ እስካልሆነ ድረስ ተውበቱን ይቀበለዋል።     (ቲርሚዚ ዘግበውታል)

 • ከዚህ በመነሳት አንድ የአላህ(ሱ ወ)ባሪያ ሞት፣ የሞት ጣር እንዲሁም የሞት ጣጣ እሱ ላይ ከመስፈኑ በፊት ትክክለኛ ተውበት ለማድረግና ወደ አላህ(ሱ ወ)ለመመለስ መጓጓትና ከፍተኛ ጥረት ማደረግ ትኖርበታል።

 

4) التوبة قبل أشراط الساعة

 (4የቂያማምልክቶችከመከሰታቸውበፊትተውበትማደግ

በርካታ የቂያማ ምልክቶች እንዳሉ ይታወቃል። ነገር ግን ከነኚህ ምልክቶች መካከል ታላላቅ የቂያማ ምልክቶች ናቸው የሚባሉ ፲ ዋና ዋና ክስተቶች አሉ። ከነሱ ውስጥ ከፊሎቹ ከተከሰቱ በኋላ የሚደረግ ማንኛውም ተውበት ተቀባይነት ስለሌለው ከወዲሁ ለተውበት መቻኮል ተገቢ ይሆናል። አንድ ሰው  የሚሞትበት የመጨረሻው ቁርጥ ሰአት  ከመድረሱ በፊት ተውበት ማድረጉ ከተውበት ሸርጦች አንዱ ነው። ይህን ሐሳብ የሚያጠናክርል ነብያዊ ሐዲስ ቀጥለን እንመልከት።

عن أبى هريرة رضي الله عليه وسلم :“ من تاب قبل أن تطلع الشمس من مغربها تاب الله عليه ” رواه مسلم

 • አቡ ሁረይራ(ረ አ) ባስተላለፈው ዘገባ ላይ የአላህ መልእክተኛ(ሰ አ ወ) እንዲህ ማልታቸውን ጠቅሰዋል፦ ፀሐይ ከመጥለቂያዋ (ከምእራብ) ከመውጣቷ በፊት ተውበት ያደረግ ሰው አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል። (ሙስሊም ዘግበውታል)

 

الإخلاص في التوبة والحرص عليها ومجانبة أهل الشر 9-5

 ومكان المعصية, وسؤال أهل العلم

5-9ለአላህ() ብሎተውበትማድረግ፣ከሽርክተግባሪዎችናከወንጀሉስፍራመራቅ፣ እንዲሁምየእውቅትባለቤቶችንመጠየቅ

ሁሌም ቢሆን ሰው እንደመሆናችን መጥን በተለያዩ ወንጀሎችና ከተለያዩ መጥፎ ግልሰቦች ጋር ቅርርብ ሊኖረን ይችላለ። ነገር ግን ተውበት ማድረግ ወይም ወደ አላህ መመለስ በምንፈልግበት ሰአት ከእነዚህን ሰዎችና መጥፎ ተግባር ስንፈጽምበት ከነበረው አካባቢ መራቅና መገለል ይሆናል። ለዚህም ምርጥ ምሳሌ የሚሆን ታሪክ ነብዩ(ሰ አ ወ)ይተርኩልናል። በዚህ ታሪክ ውስጥ ታልቅ የሆነን ቁም ነገር እንደምናገኝ ጽፍ አደርጋለሁ።

አቡ ሰኢድ፡ ሰኢድ ኢብን ማሊክ ኢብን ሲናን አል ኹድሪይ(ረ አ) እንዳስተላለፍት የአላህ መልእክተኛ(ሰ አ ወ) እንዲህ በማለት ተናግረዋል፦ከናንተ በፊት በነበረው ዘመን አንድ የዘጠና ዘጠኝ ሰዎችን ነፍስ ያጠፍ ሰው ነበር። (እርሱም) ምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይበልጥ አዋቂው ማን እንደሆን ጠየቀ። ወደ አንድ መናኝ ባህታዊ አምላከቱት።ከርሱ ዘንድ ሄደ ዘጠና ዝጠኝ የሰው ነፍስ እንዳጠፍና ተውበት ቢያደርግ የቀባይንት ያገኝ እንድሆን (ለማወቅ) ጠየቀው። መናኙ (ምንም ምህረት) አታገኝም አለው። (ከዚያም) እርሱን ገደለውና መቶ ሞላ።.

ከዚያም ምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይበልጥ አዋቂው ማን እንደሆነ በድጋሚ ጠየቀ። ወደ አንድ አዋቂ ሰው አመላከቱት። አንድ የመቶ ሰዎችን ህይወት ያጠፍ ሰው ተውበት ቢያደርግ ተቀባይነት ያገኝ እንደሆነ ጠየቀው። አሊሙ <አዎ፦(ተቀባይነት ያገኛል) በርሱና በተውበቱ መካከል ግርዶ የሚፈጥረው ማን ነው፧፦(አለውና ከዚያም) እገሌ ወደ ተባለ ቦታ ሂድ እዚያ ሥፍራ ላይ አላህን ብቻ የሚያመልኩ ሰዎች አሉ ከነርሱ ጋር አብረህ አላህን አምልክ ወደ ነበርክበት ሀገር አትመለስ የክፍት ሥፍራ ነውና>አለው። ወደ ተጠቆመው ሀገር ተጓዘ። መንገዱን እንዳጋመስ ሞት ነጠቀው። የእዝነት(የጀነት) እና የቅጣት(የአዛብ)መላኢኮት(እኛ እንወስደዋለን በሚል)ተሟገቱ። የጀነት መላኢኮች(እርሱ እኮ) <ቶብቶና ቀልቡን ወደ አላህ አዙሮ ነው የመጣው> አሉ። የአዛብ መላኢኮች ደግሞ(እርሱ) <በጐ ተግባር ፈጽሞ አያውቅም አሉ። አንድ መላኢካ በሰው ተመስሎ ወደነርሱ መጣ።ብይን ይሰጣቸው ዘንድ ጋበዙት። <ሁለቱ መሬቶች (የመጣበትና የሚሄድበት) ከሞተበት ስፍራ ያላቸውን ርቀት ለኩ። መሄድ ወደ ጀመረበት ስፍራ ቀረብ ብሎ አገኙት። የጀነት መላኢኮች ወሰዱት። (ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል)

 

ከዚህሀዲስከምንማራቸውቁምነገሮች

 መካከልጥቂቶቹንእንይ፦

 • የመልእክተኛው(ሰ አ ወ)በተጨባጭ ምሳሌዎች የታጀበ ድንቅ የትምህርት    አሰጣጥ ስልት፡
 •  ካለፍት ህዝቦች ክንውኖች መካከል ከኢስላም ጋር የሚጣጣሙትን መዘከር     የሚፈቀድ መሆኑን፡
 •  መላካምን መንገድ ለመከተል ዝግጁነት ያላት ልቦና በተወሰነ አጋጣሚ በስሜት በመሸነፍ የስኬትን ፍኖት ብት ስትም ወደ ትክክለኛ መስመር የመመለስ እድሏ የሰፍ መሆኑን፡
 •  እውቀት (ኢልም)ከጥቂት ኢባዳ ጋር እንኳን ቢሆን በብዙ ኢባዳዎች ከታጀበ ድንቁርና(ጃሂል) ይበልጥ ጠቃሚ ነው፤ምክንያቱም ጃሂል መልካም ተግባራትን የፈፀመ እየመሰለው ሊያጥፍና ሌሎችንም ለጥፍት ሊዳርግ ይችላል። አዋቂዎች(አሊሞች) ግን ብእውቀት ብርሀን እየተመሩ ትክክለኛውን መስመር በመያዝ ለራሳቸው ተጠቅመው ሌሎችንም ይጠቅምሉ፡
 • የተውበት ደጃፍ ክፍት ነው።ተውበት የሚያደርጉ ሰዎች ወንጀላቸው የቱንም ያህል የበዛ ቢሆንም ተቀባይነት የማግኘት እድል አላቸው።
 •  ወንጀለኞች ከወንጀላቸው እስካልታቀቡ ድርስ ከነርሱ ጋር የሚኖርንን ግንኙነት ማቋረጥ እንዲሁም አላህን ክሚፈሩ ሰዎች ጋር ግንኙነትን ማጥናከር ተገቢ ነው።
 •  የአላህ(ሱ ወ) ባሮች ወደርሱ በተውበት ሲመለሱ መልካም አርአያነት ለመከተል ከፍተኛ ጥረትና ትግል ማድረግ በዚህ ሂደት የሚገጥሙ ፈተናዎችንና ችግሮችን መሸከም ለተውበት ያለን ጉጉት የሚያሳይ ምልክት ነው።

እውነተኝነት በሁሉም የህይወት እንቅስቃሴያችን ውስጥ ሊስተዋል የሚገባ መሰረታዊ ባህሪ እንድሆነ ሁሉ ተውበትም ላይ እውነተኛና ትክክለኛ ተውበት አድራጊዎች መሆን ይጠበቅብናል። ይህም እውነተኝነት በተግባር፣ በንግ ግርና በመላው ሁኔታችን ላይ ሊስተዋል ይገባል።

እውነተኝነት የአላህን እዝነት፥ በረከትና ትሩፍትን ለማግኘት ዋናው ምክንያይ ነው። በዚህም አላህ(ሱ ወ)ልአንድ ባሪያው ተውበቱን ሊቀበለው ውንጀሉን ሊምረውና እንዲሁም ደረጃውን ከፍ ሊያደርግለት ይችላል። ኢብኑ ማሊክ ፤እና የጓደኞቹን ታሪክ በአስተማሪነት ማቅረብ ይቻላል።

ይቀጥላል …….

አላህን በምን መልክ ማወቅ እንችላለን?

አላህን በምን መልክ ማወቅ እንችላለን? 

ከእውቀት ሁሉ የላቀና እጅግ የሚያኮራው አላህን ማወቅ ነው። የመንፈስ  እ ርካታና የተረጋጋ ህይወት መሰረትም ይኸው ነው።

ስለ ነቢያትና መልክተኞች ማንነት ታማኝነታቸውን የተጣለባቸውን አደራ ባህሪያቶቻቸውን የተልእኳቸውን አስፈላጊነት ያሳዩአቸውን ተአምራት እንዲሁም ለሰው ልጅ መመሪያ ይሆን ዘንድ ይዘዋቸው የመጡ መለኰታዊ መመሪያዎችን ሁሉ ልናውቅ የምንችለው በቅድሚታ አላህን ሰናውቅ ነው።

ከተጨባጩ አለም ውጭ ያሉና እንደ መላእክት አጋንንት ሩህና የመሳሰሉትን ማወቅ የምንችለውም በአላህ

` ላይ ካለን ግንዛቤ በመነሳት ነው። የህይወትን ሂደት በመካነ መቃብር ውስጥ ስለሚኖረው ሁኔታ የትንሳዔ ህይወት መቀስቀስ ሂሳብ ምንዳን መቀበል ጀነት ጀሀነም  ሰለምንላቸው ጉዳዩች ሁሉ ማወቅ የምንችለው በአንደኛ ደረጃ አላህን ስናውቅ ነው።

 

አላህን ለማወቅ ሁለት አበይት ዘዴዎችን መጠቀም እንችላለን።

አንደኛ ፦ አእምሮን በመጠቀምና ተፈጥሮን በማጤን።

ሁለተኛ ፦ የአላህን ስሞችና ባህሪያት በማጥናት።

አዎ፨ በአንድ ወገን ህሊናችንን በመጠቀም በሌላ በኩል ደግሞ መለኮታዊ ማንነቱን የሚገልፁ ስሞቹንና ባህሪያቱን በማጥናት የሰው ልጅ ፈጣሪውን ሊያውቅና ወደርሱ ሊቃረብ ይችላል።

 

አእምሮን በመጠቀም… አላህን ማወቅ

እያንዳንዱ የሰውነት ክፍል የራሱ የሆነ ሚና አለው። የአእምሮ ሚናናየስራ ድርሻ ማስተንተን መመራመርና ማገናዘብ ነው። ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን አእምሮ ስራ ይፈታል መችጫወት ያለበትን ሚና በመነፈጉም ሰውዩው ጭፍንና ግትር ይሆናል ። የህሊና ሞት ይገጥመዋል። ኢስላም አ፤ምሮ ተገቢውን ክንውን እንዲፈፅም ለማድርግ መመረመር ግራና ቀኝ መመልከትና ማጤን የእያንዳንዱ ግለሰብ ግዴታ መሆኑንም አሳውቋል።

[ قل انظروا ماذا في السموات والأرض ]

<በሰማያትና በምድር ያለውን (ታምር) ተመልከቱ በላቸው፤> (ዩኑስ፥101)

[  قل انما أعظكم بواحدة أن تقوموا لله مثنى وفراد ثم تتفكروا ]

<የምግስጻችሁ ባንዲት ነገር ብቻ ነው (እርሷም) ሁለት ሁለት፥ አንድ አንድም ኾናችሁ ለአላህ እንድትነሱ ከዚያም…መርምራችሁ እንድትረዱ ነው፤…(ሰበእ፥46)

 

የአእምሮን ፀጋ የማይቀበሉ ለተፈጠረለት አላማ የማያውሉትና የአላህን ተፈጥሮአዊ ተአምራት ተሚዘነጉ ለሆኑ ሰዎች መለኰታዊ  ዛቻ ወርዶባቸዋል። ይጠንቀቁ፨

[  وكأين من آية في السموات والأرض يمرون عليها معرضون ]

<በሰማያትና በምድርም ካለችው ምልክት፥ ብዙይቱ እሱን ከርሷ ዘንጊዎች ኾነውበርሷ ላይ ኣልፍሉ።>(ዩሱፍ፥105)

[وما تأتيهم  من أية من أيات ربهم إلا كانوا عنها معرضين]

<ከጌታቸውም ታምራት ማንኛይቱም ታምር አትመጣላቸውም ከርሷ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጅ።> (ያሲን፥46

አእምሮ ተገቢውን ሚና እንዳይጫወት ማድረግ የሰውን ልጅ ከእንስሳት ጐራ መፈረጅ ነው። ኧረ ከዚህያም በታች፦

ولقد ذرأنا لجهنم كثيرا من الجن والانس لهم قلوب  لايفقهون بها ]

 ولهم أعين لايبصرون بها ولهم آذان لايسمعون بها أولئك  كالأنعام بل

[ هم أضل أولئـك  هم الغافلون

<ከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሁነም በእርግጥ ፈጠርን ለነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው ለነሱም በሳቸው የሚያዩባቸው አይኖች አሏቸው ለነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሏቸው እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው እነዚያን ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፤>(አል፡ አእራፍ፥179)

 

ጭፍንነት የአእምሮ ጋሬጣ ነው

ከአባቶች ከባህለና አካባቢ በዘልማድ የሚነገሩና የሚተገበሩ ድርጊቶችን ያለ ምንም ጥያቄ መጥፎና ጥሩነታቸውን ሳይመዝኑ በጭፍን መውረስና መከተል ብሎም ማስተጋባት (ተቅሊድ) የአእምሮ ጋሬጣ ነው። የህሊናን ስልጣን መጋፍት ነው። ለዚህ ነው አላህ (ሱ ወ)በቅዱስ ቁርአን አሰስገሰሱን ሁሉ የማይቀበሉና ፍሬውን ከገለባው ለመለየት የሚሞክሩትን ሲያወደስ የምንመለከተው፦

         فبشر عبادى  الذين يستمعون القول  فيتبعون أحسنه أولئـك الذين هداهم الله وأولئـك هم أولوا الألباب

<እነዚህያን ንግርን የሚያዳምጡትንና መልካሙን የሚከተሉትን (አብስር) እነዚያ እነርሱ አላህ የመራቸው ናቸው።እነዚያም እነሱ ባለ አእምሮዎች ናቸው።>(አል፡ዙመር፥17-18)

በአንፃሩ በሌሎች ጭንቅላት ማስብ የሚሹትን የትናንቱን ብቻ ጐጂ ቢሆንም እንከተላለን የሚሉትንና ጠቃሚ ለውጥ ጆሮ ዳባ ልበስ የሚሉትን ያወግዛል ቁርአን

 واذا قيل لهم لتبعوا ماأنذل الله قالوا بل نتبع ماالفينا عليه آباءنا أولو كان آباؤهم لايعقلون شيئا ولايهتدون

<ለነርሱም አላህ ያወረደውን ተከተሉ በተባሉ ጊዜ አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር እንከተላለን ይላሉ አባቶቻችው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ (ይከተሉዋቸዋልን )(አል በቀራህ፥ 170)

የአእምሮአድማስናወሰን

ኢስላም እወቁ ተመራመሩ አስተንትኑ እያለ ቢያበረታታም አእምሮ ግን ወሰን የለሽ ሁሉን አዋቂና እንከን አልባ መሳሪያ ነው የሚል እምነት የለውም። እያንዳንዱ የአካል ክፍል ገደብ እንዳለው ሁሉ አእምሮአችንም የተወሰነ አድማስና ወሰን ያለው መሆን መዘንጋት የለብንም።

ኢስላም ተፈጥሮን እንድንመረምር ያስገድደናል። ሰማያትን ምድርን ከዋክብትን የሰውን ልጅ አፈጣጠር ማህበራዊ ስብጥሩን እና የመሳሰሉትንጉዳዩች የመፈላፈል ፈቃድ ሰጥቷል።  በአንድ ጉዳይ ብቻ ጊዜ ማጥፍት አንደሌለብን ያስገነዝባል  በአላህ (ዛት)(አካላዊ ውቅረት)።ለምን፨፨ከህሊና የማሰብ ሀይል በላይ ነውና!

ነቢዩ መሀመድ(ሰ አ ወ) እንዲህ ብለዋል፦ <አላህ የፈጠረውን አለም መርምሩት ስለ አላህ አካልና ውቅረት ግን አትመራመሩ። ምክንያቱም ይህን ሊገነዘብ የሚችል ሀትል የላችሁም።> (አቡ ናኢም ዘግበውታል።)

ቁርአን ዩኒቨርሱን በመቃኘት ረገድ አያሌ አንቀጾችን አስፍሯል።

[ كذلك يبين الله لكم الآيات لعلكم تتفكرون فى الدنيا  والآخرة  ]

<በቅርቢቱ አለምና በመጨረሻቱ ታስተነትኑ ዘንድ (አንቀጾችን ይገልጽላችኋል)… >(አል- በቀራህ፥220)

 

የምርምርአላማ

ኢስላም ንቃተ – ህሊናእንዲኖረን አእምሯችንን ለተፈጠረለት አላማ እንድናውል የሚሻበት ዋና ምክንያት የሰውን ልጅ ትክክለኛውን የህይወት ህግና ጐዳና ለማስያዝ ነው። የመፈጠሩን ቁምነገር ይዩኒቨርሱን ቀመርና የነገሮችን እውነተኛ ገፅታ እንዲረዳ ለማድረግ ነው። ምርምሩ የአላማችንን ጅምር ወጣኝ (ኦሪጂኔተር) የሆነውን አምላክ ህልውና ብሎም ምንነት በማስጨበጥ የጥበቦች ጥበብ የሆነውን ታላቅ ፀጋ – አላህን ማወቅ-   ማጐናፀፍ ነው።

 

 

 

አላህን ማወቅ የብልህና የንፁህ አእምሮ ፍሬ ንው። ቁርአን በተፈጥሮ አድማስ ላይ ማነጣጠር እንዳለብን የሚያሳስበው የአላህን ምሉእ ባህሪያት ግርማ ሞገሱን አልፉና ኦሜጋ የሆነ እውቀቱንና ችሎታውን መገንዘብ  እንድንችል ነው። እንዲሁም አለማችንን ሲፈጥር ረዳትና ተባባሪ ያልነበረው መሆኑንም እንድናጤን ነው። እስቲ የሚከተለውን ቁርአናዊ አንቀጽ እናስተውል፦

   قُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ وَسَلَامٌ عَلَىٰ عِبَادِهِ الَّذِينَ اصْطَفَىٰ ۗ آللَّهُ خَيْرٌ أَمَّا يُشْرِكُونَ (59) أَمَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَأَنْزَلَ لَكُمْ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَنْبَتْنَا بِهِ حَدَائِقَ ذَاتَ بَهْجَةٍ مَا كَانَ لَكُمْ أَنْ تُنْبِتُوا شَجَرَهَا ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ بَلْ هُمْ قَوْمٌ يَعْدِلُونَ (60) أَمَّنْ جَعَلَ الْأَرْضَ قَرَارًا وَجَعَلَ خِلَالَهَا أَنْهَارًا وَجَعَلَ لَهَا رَوَاسِيَ وَجَعَلَ بَيْنَ الْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ(61) أَمَّنْ يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَا تَذَكَّرُونَ (62) أَمَّنْ يَهْدِيكُمْ فِي ظُلُمَاتِ الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَمَنْ يُرْسِلُ الرِّيَاحَ بُشْرًا بَيْنَ يَدَيْ رَحْمَتِهِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ تَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ (63) أَمَّنْ يَبْدَأُ الْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُ وَمَنْ يَرْزُقُكُمْ مِنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَعَ اللَّهِ ۚ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِنْ (64) كُنْتُمْ صَادِقِينَ

< ሙሀመድ ሆይ …ምስጋና ለአላህ ይግባው በነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሰላም ይውረድ አላህ በላጭ ነውን? ወይስ ያ የሚያጋሩትን? …ወይም ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለናንት ውሀን ያወረደው? (ይበልጣል? ወይስ የሚያጋሩት) በርሱም ባለውበት የኾኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታብቅሉ ለናንተ ችሎታ ያልነበራችሁን አበቀልን ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? (የለም) ግን እነሱ (ከውነት)የሚያዘነብሉ ህዝቦች ናቸው። ውይም ያ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካካሏም ወንዞችን ያደረገ ለርሷም ጋራውዎችን ያደረገ በሁለቱ ባህሮችም(በጣፍጩና በጨው ባህር) መካከል ግርዶን ያደረገ(ይበልጣል፨ ወይስ የሚያጋሩት)?…ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። ወይም ያችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋጩ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሰጹም። ወይም ያ በየብስና በባህር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ነፍሶችንም ከዝናሙ በፊት አብሳሪ ኾነው የሚልክ(ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አላን? አላህ (በርሱ) ከሚያጋሩዋቸው ሁሉ ላቀ። ወይም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አምላክ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አማላክ  አለን?እውነተኞች እንደኾናችሁ፤ ማስረጃችሁን አምጡ በላቸው።>

(አል-ነምል፥59-64)

ታዲያ ከዚህ ቁርአናዊ መረጃ ውጭ ሌላ የጠላቀና አርኪ እማኝ ይገኝይሆና፨ የሰው ልጅ ህሊና ለእንዲህ አይነቱ አስረጅ ካልተቨነፈ ልምንና ልማን አሜን ይል ይሆን፨

[ومن لم يجعل الله له نورا فما له من نور ]

<አላህም ለርሱ ብርሀንን ያላደረገለት ሰው ለርሱ ምንም ብርሀን የለውም።>(አል- ኑር፥40)

ጊዜ(Time)

images (6)

 

ጊዜ

*<<ጊዜ ሰይፍ ነው፤ ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል>(አረቦች)

ከቀደምት የአላህ  ባሪያዎች አንዱ ሲናገሩ፦

 • <ያለ ስራ ጀነት መፈለግ ወንጀል ነው፤
 • የነብዩን (ሶ አ ወ) ሱና ሳይከተሉ የሳቸውን ሸፈዓ (ትዳጌ)መመኘት ራስን ማታለል ነው፤
 • ሀጢአት እየሰሩ የአላህን ምህረት ተስፍ ማረግ ሞኝነትና ድንቁርና ነው> ብለዋል።

ሀሰን እንዲህ ይሉ ነበር፦<እናንተ ሰዎች ሆይ ከምኞት ተጠንቀቁ። ምኞት የዋሆች የሚወድቁበት ሸለቆ ነው። ወላሂ ፥ አላህ በአዱንያም ሆነ በአኼራ በምኞት ለባሮቹ የሚሰጠው ነገር የለም።>

<አቅለኛ ሰው አራት ሰዓታት ሊኖሩት ይገባል። ከነዚህ አንዱ ራሱን በራስ የሚመረምርበት ሰዓት ነው።>

የሙእሚኖች መሪ ኡመር ኢብኒል ኸጣብ (ረ አ)፦ <ምርመራ ሳይደረግባችሁ በፊት ራሳችሁን መርምሩ፤ ሳይመዘንባችሁ በፊት ስራችሁን መዝኑ> በማለት ያስጠነቅቁ ነበር። በያቀኑ ደግሞ ዛሬ ምን ሰራሁ በማለት ራሳቸውን ይመረምሩ ነበር።

መይሙን ኢብን መህራን የተባሉ ታቢኢይ (በሶሀባዎች ዘመን የነበሩ) ታላቅ ሰው፦ <አላህን የሚፈራ ሰው(ተቂይ)ክስስታም ወይም ንፍግ የስራ ሸሪክ ይበልጥ ራሱን በራሱ የሚመረምር ነው> ይሉ ነበር።

ሀሰን በበኩላቸው<ሙእሚን የራሱ የነፍሱ ተቆጣጣሪ ነው። ለአላህ ሲል ይቆጣጠራታል። የሂሳብ ምርመራ የሚቀንሰው በአዱንያ ራሳቸውን ለመረመሩ ሰዎች ሲሆን፥ ሂሳብ የሚበረታው ደግሞ ራሳቸውን ባልተቆጣጠሩ ሰዎች ላይ ነው> ብለዋል።

አዒሻ ቢንት አቡበከር አዒሻ (ረ አ)

 

images (5)

 

አዒሻ ቢንት አቡበከር «በእርግጥ እኔ የምሻው አላህን፣ መልእክተኛውን፣ እንዲሁም ዘውታሪ የሆነውን የመጭውን ህይወት መኖሪያ (ጀነት) ነው።» አዒሻ (ረ አ) የአዒሻ የህይወት ታሪክ ሴት ልጅ እንደ ተቃራኒ ፆታዋ አዋቂና የምሁራን መምህር ለመሆን ብቃት እንዳላት ያረጋግጥልናል። በተጨማሪም ሴት ልጅ በወንዶች አስተሳሰብ ላይ ተፅእኖ በመፍጠር የአመለካክትና የአመራር ምንጭ መሆን እንደምትችል ፥ አልፎ ተርፎም በእንስትነቷ ለባልተቤቷ የደስታና የምቾት ምንጭ ለመሆን ብቃት እንዳላት ግልፅ ማስረጃነት አለው። አዒሻ የአንድም ዩኒቨርስቲ ምሩቅ አልነበረችም። እንዲያውም በዘመኗ ዩኒቨርስቲም አልነበረም። ግና እንደማር ያንቆረቆረቻቸውን ንግግሮቿ በቋንቋ መካነ ጥናቶች እየተጠኑ ነው። ህግን በሚመለከት የተናገረቻቸው በህግ ኮሌጆች ይጠናሉ። እንዲሁም ከህይወት ታሪኳ የሚነበቡ ድርጊቶችዋ የሙስሊሞችን ታሪክ በሚያጠኑ ተማሪዎችና ምሁራን ከሺህ አመታት በላይ እረተዳሰሱ ነው። አዒሻ የእውቀት ባህር ለመሆን የበቃችው ገና በወጣትነት እድሜዋ ነው። ልጅ ሆና ያደገችው በአዋቂነታቸውና በመልካም ስነ ምግባራቸው በሚታወቁት በአባቷ በአቡበከር ቤት ነው። አኢሻ በማራኪው ውበቷና በአስደናቂው የማስታወስ ችሎታዋ የታወቀች ነበረች። በወጣትነት ጊዜዋ የነብዩ የልብ ተፈቃሪና ታሳቢ ለመሆን በቅታለች። በሚስትነትም የቅርብ ወዳጃቸው ለመሆን በመታደሏ ሌሎች ሴቶች ሊያካብቱት ያልቻሉትን እውቀት ከርሳቸው ለማግኘት ችላለች። የነቢዩ ሚስት የሆነችው የ10 አመት ልጅ ሳለች በመካ ሲሆን፥እስከሁለተኛው አመተ ሂጅራና በግምት የ14 ናየ15 አመት ወጣት እስከሆነችበት ጊዜ ድረስ ሰርጓ አልተከናወነም። የሰርጓን ስነ ስርዓት በተመለከተ እንዲህ ስትል ተርካልናለች፦ «አንድ ቀን እየተጫወትኩ ነበር። ረጅሙና ዘንፍላው ፀጉሬ በወጉ አልተጐነጐነም። ቤተሰቦቼ ከምጫወትበት ቦታ መጥተው ወደቤት በመውሰድ ለሰርግ እንድዘጋጅ አደረጉኝ። በባህሬይን የተሰራ ቀይ ሰረዝ ያለው የሙሽራ ልብስ አለበሱኝ ። እናቴም ጥቂት የመዲና ሴቶች ከበር ላይ ቆመው ወደሚጠብቁባት አዲሱ ጐጆዬ ወሰደችኝ። (ጋብቻሽ ለመልካምና ለደስታ ይበለው ሁሉም ያማረ ይሁንልሽ) ስሉም በደስታ ተቀበሉኝ። ከዚያም በፈገግታ የተሞሉት ነቢይ በተገኙበት የዋንጫ ወተት ቀረበ። ነቢዩ (ሰ አ ወ) ከወተቱ ተጐንጭተው ሰጡኝ ። እኔም ስላፈርኩኝ በእጄ እንደያዝኩት ቀረሁ። ቢሆንም እንድጠጣ ስላደፍፈሩኝ ጠጣሁ። ቀሪውን ከ አጠገቤ ተቀምጣ ለነበረችው እህቴ ለአስማ አሳለፍኩ። በዚህ አይነት ሁኔታ ሁሉም እየተቀባበሉ ተጐነጩለት። በዚህ እጅግ ቀላልና የተባረከ በሆነ መልክ ነበር የጋብቻ ስነስር አቱ የተካሄደው።» የነብዩ ሚስት መሆኗ የጨዋታ ህይወቷን አልገታውም። ወጣት ጓደኞቿ ከቤት ሊጐበኟት አዘውትረው ይመጡ ነበር። ስለዚህም ሁኔታ እንዲህ ስትል ተናግራለች፦ «ጓደኞቼ ከሆኑ ልጃገረዶች ጋር በመጫወት ላይ ሳለሁ ነቢዩ በሚገቡበት ጌዚ ጓደኞቼ ቤቱን ለቀው ይወጣሉ። ነቢዪም የእነርሱ ከኔ ጋር መሆን እንደሚያስደስተኝ ስለሚያውቁ ለኔ ውዴታ ሲሉ እንዲመለሱ ያደርጓቸዋል። እንዲያም ሲል በጨዋታቸው ላይ ይሳተፍሉ።» የአዒሻ የመጀመቲያው የመዲና ህይወቷ ትጋትና ጥንካሬን የሚጠይቅ ፈታኝ አጋጣሚ ነበር። በ አንድ ወቅት አባቷና ከርሱ ዘንድ ያረፍ ሁለት አስሃባዎች በመዲና በተወሰኑ ወቅቶች የተለመደ በሆነ አደገኛ ትኩሳት ታመሙ። በዚያን ጊዜ አዒሻ አንድ ጠዋት አባቷን ለመጐብኘት እንደሄደች ሦስቱም በሽተኞች ተዳክመውና ሰውነታቸው ሟሾ ስላገኘቻቸው ከባድ ድንጋጤና ተስፍ የመቁረጥ ስሜት አደረባት። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አባቷ ምን እንደሚሰማቸው ስትጠይቅ፥ ትርጓሜው ባልገባት የቁርአን ምእራፍ መለሱላት። በሁኔታው እጅግ ተረብሻ ወደቤቷ በመመለስ ለነቢዩ፥ «በሽታው ስለጠናባቸው ይቃዣሉ።» አለቻቸው። ነቢዩም ምን እንዳሉ ጠየቋት። ምንም እንኳ ትርጓሜው ባይገባትም የሰማችውን ንግ ግር ቃል በቃል ነገረቻቸው። ከንግግሯም ነቢዩ የበሽተኞቹን ሁኔታ ለመረዳት ቻሉ። ይህ ገጠመኝ እጅግ አስደናቂ የሆነውን የማስታወስ ችሎታዋን ያሳየናል። ይህም ችሎታዋ ጊዜ እየገፍ በሄድ ቁጥር በዋጋ ሊተመኑ የማይችሉ የነቢዩን ንግግሮች አንድታክማች አግዟታል። ነብዩ በመዲና ሳሉ ከሚስቶቻቸው ሁሉ አዒሻን ይበልጥ ይወዱ እንደነበር ግልፅ ነው። አንዳንዱ ባልደረባዎቻቸው አዘውትረው «የ አላህ ልዑክ ሆይ በዓለም ላይ እጅግ በጣም የሚወዱት ማንን ነው?» ሲሉ ይጠይቋቸው ነበር። ለዚህም ጥያቄ የሚሰጡት ምላሽ እንደ ጥያቄው ባህሪ የሚለያይ ነበር። ለሴት ልጆቻቸውና ለነርሱም ልጆች፥ ሌላ ጊዜ ለ አቡበከር፥ ለዓሊ፣ ለዘይድና ለልጁ ለኡሳም ውዴታ እንዳላቸው አሳውቀዋል። ከነቢዩ ህልፈት በኋላ አዒሻ ለ50 አመታት ያህል ኖራለች። የትዳር ዘመኗ አስር አመታት ብቻ ሲሆኑ ከእነዚህ ጊዜያቶች አብዛኛውን ያሳለፈችው የአላህ መመሪያ የሆኑትን ሁለት ታላላቅ የእውቀት ምንጮች ቁርአንና ሱናን በማጥናት ነበር። አኢሻ ቁርአንን በልባቸው ከቋጠሩት ሦስት የነቢዩ ሚስቶች አንዷ ነበረች ። ሁለቱ ሀፍሷ እና ኡሙ ሰላማ ነበሩ።ሀፍሷ እና አዒሻ ነብዩ ካለፉ በኋላ የተከተበ የቁርአን ቅጅ ነበራቸው። ዓኢሻ (ረ አ) የጋን መብራት አልነበረችም። እውቀቷን ለሌሎች በማስተላለፍና ማህበራዊ መሻሻሎችን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክታለች። ብምታስተምርበት ጊዜ ልብን የሚስብና ግልፅ የሆነ የነግግር ለዛ ነበራት። የንግግር ኃይሏ በንፅፅር ሁኔታ አል አህናፍ በተባለ ሰው እንደተከተለው ተገልጿ፦ «የአቡበከርንም ሆነ የኡመርን ንግግሮች አድምጫለሁ። የኡስማንን ፣ የዓሊን ፣ እንዲሁም እስካለሁበት ገዜ ድረስ ያሉ ተተኪዎችን እንደዚሁ። ነገር ግን በእውነቱ ከዓኢሻ አፍ እንደሰማሁት ያለ እጅግ የሚማርክና በጣም የተዋበ ንግግር ከማንም አልሰማሁም።» እውቀት ለመገብየት ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ድንበር አቋርጠው ይመጣሉ ። የሴቶቹ ቁጥርም ከወንዶቹ እንደሚበልጥ ይነገራል። ለሚቀርብላት ጥያቄ መልስ ከመስጠቷ በተጨማሪ በጥበቃዋ ስር በርሷ መመሪያ መሰረት የምታስጠናቸው የቲም የሆኑ ልጆችና ልጃገረዶች ነበሯት። እነርሱም ከርሷ መመሪያ ከሚቀበሉት ዘመዶቿ ተጨማሪ ናቸው። ከዚህም የተነሳ ቤቷ ት /ቤት ነበር ለማለት ይቻላል። ዓኢሻና የአላህ ፍራቻዋ መልእክተኛው (ሰ አ ወ ) ለተወዳጇ ሚስታቸው የነበራቸውን ፍቅር የማያውቅ ማን አለ? ከማንም በላይ ማንን እንደሚወዱ ሲጠየቁ ዓኢሻን ብለው መልስ ሰጥተዋል።በኢስላማዊ ህግጋት ከፍተኛ እውቀት የነበራት ከመሆኑ የተነሳ ታላላቅ ሶሀባዎች በዚህ ዘርፍ መፍትሄ ፍለጋ ወደ እሷ ይሄዱ ነበር። ጅብሪል (አሰሰላሙ አለይኩም) በማለት ሰላምታ ያቀርብላት ነበር። መልክተኛውም በአንድ ወቅት በጀነትም ባለቤታቸው እንደምሆን ነግረዋታል። በሙናፍቃን ስትታማ አላህ ከሀሜቱ ነፃ መሆኗን ያረጋገጠላት የቁርአን አንቀጽ በማውረድ ነበር። ኢብን ሰእድ እንደጠቀስነው ዓኢሻ (ረ አ) በአንድ ወቅት አላህ ከሌሎች የመልእክተኛው ሚስቶች በተለየ የሰጣትን አስርያህል ጥሩ ባህሪዋን ቆጥራልች።እነዚህ ባህራዎች ቢኖሯትም አላህን ከመፍራቷ ይተነሳ የሚከተሉትን ስትል ትደመጥ ነበር። «ሁል ጊዜ አላህን በማወደስ እንድጠመድና በፍርዱ ቀንም ነፃ እንድወጣ ዛፍ አርጐ ፈጥሮኝ በነበር!» «ድንጋይ ወይንም አፈር ባደረገኝ!» «ቅጠል ወይንም ሳር ባደረገኝ!» «ባልተፈጠርኩ!» ከታላቋ ኸዲጃና ከፍጢመቱ ዘህራእ(አንፀባራቂዋ) (ረ አ) ቀጥሎ ዓኢሻ በኢስላም ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣት ድንቅ ሴት ናት። በነበራት ጠንካራ ሰብእና በሁሉም መስክ ማለትም በእውቀት፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በፓለቲካና በጦር ሜዳ የመሪነት ስፍራ ይዞ ነበር። ዓኢሻ በዘመኗ ከነበሩ ሴቶች የክብርትነትን ደርጃ ለማግኘትና መልካም አርአያ ለመሆን በቅታለች። በ 58 ኛው ዘመን ሂጅራም በወርሀ ረመዷን ከዚህ አለም በሞት ተሰናበተች። በኑዛዜዋ መሰረት በመዲና በቂእ በተሰኘው የቀብር ስፍራ ከሌሎች የነቢዩ አስሀባዎች ጋር አስክሬኗ አረፈ። እኛንም ኢንሻአላህ ከእሷ ብዙ ትምህርቶችን የምንማር አላህ ያድርገን እላለሁኝ።

بعض النصائح لمن يقرأ القرآن الكريم ጥቂትምክርለቁርአንአንባቢዎች

بعض النصائح لمن يقرأ القرآن الكريم ጥቂትምክርለቁርአንአንባቢዎች
* የአላህን ስምና ባህሪያት (ሲፍት) ስትሰማ ልብህ በአንድናቆት፣በውለታ፣ በፍቅር እና በተመሳሳይ ስሜቶች ይዋጥ።

* ስለአላህ መልእክትኞች ስታነብ ልብህ እነሱን የመከተል የፍላጎት ደም በሰውነት ትርጭ። ልተቃዋሚዎቻቸውም የሚያንቀጠቅጥ ጥላቻ ይሰማህ።

ስለ ፍርዱ ቀን (የውመል ቂያማ) ስታነብ የጀነት ናፍቆት በአንድ በኩል፣ የጀሀነም እሳት ፍርሃት በሌላ በኩል በሚንጡህ ሁን።

* ስላመፁ ሰዎችና ህዝቦች በአመፃቸው ስለደረሰባቸው ጥፍትና ቅጣት ስታነብ ድርጊታቸውን በእጅጉ መጥላትና አላህ ከነርሱ ዓይነቶች እንዳያደርገህ ዱዓ ማድረግ አለብህ።

ሷሊህ የሆኑና ተቅዋ ያላቸው የአላህ ባሪያዎች የተናፀፍትን ምንዳ ስታነብ እነሱን ለመሆን በጣም መመንኘት ይኖርብሃል።

* በዚህ ዓለም ጥሩ ነገሮችንና ክብርን በመጪው ዓለም ደግሞ ይቅርታንና እዝነትን በማስታወስ ተስፍ የሚሰጡ አንቀፆች ስታነብ የቃልኪዳኑ ተቋዳሽ ትሆን ዘንድ የመስራትና በስተመጨረሻም በእጅህ የማስገባት ጠንካራ ፍላጎት ይሰማህ።

* ለቁርአን ደንታ ስለሌላቸውና  ፊታቸውን ከአላህ  መፀሀፍ ስላዞሩት ስለማይቀበሉትና ህይወታቸውን በመጽሀፍ  ስለማይመሩት ስታነብ ከእነሱ አንዱ እንዳትሆን ፍርሃትና ቆራጥነት ይሰማህ።

* አላህን እንድትገዛና በርሱ መነገድ እንድትታገል የሚጠራ(የሚጋብዝ) አንቀጽ ስታነብ ምላሽ ለመስጠት እና ያዚህ አይነት ምላሽ ከመስጠት የሚገኘውን ደስታ ለመጎናፀፍ ቁረጥ።

   የአላህንውዴታእንዴትእንደሚያተርፉያውቃሉ?

* ከሚሰሩት ሁጢያት ጊዜ ሳያባክኑ ፊትዎን ወደ አላህ በመመለስ ተውባ ያድርጉ፤ ምህረቱን ይለምኑ።

* በዚህ አለም ጥሩ ነገሮችንና ክብርን በመጪው አለም ደግሞ ይቅርታንና እዝነትን በማስታወስ ተስፍ የሚሰጡ አንቀፆች ስታነብ የቃልኪዳንኑ ተቋዳሽ ትሆን ዘንድ የመስራትና በስተመጨረሻም በእጅህ የማስጋባት ጠንካራ ፍላጎት ይሰማህ።

ሐጅ- ሥርዓትና ድንጋጌዎች

ሐጅ- ሥርዓትና ድንጋጌዎች 

إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَالَمِينَ فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَّقَامُ إِبْرَاهِيمَ وَمَن دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ 

“ለሰዎች (መጸለያ) መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ነው። በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አልለ። ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል። ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው። የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው።” (አሊ ዒምራን 3፤ 96-97)

ትርጓሜው

የአላህን ትእዛዝ በመቀበል፣ ውዴታውን በመፈለግ፣ ጥንታዊውን ቤት ለመዞር፣ በሶፋና መርዋ መሀል ለመሮጥ፣ ዓረፋ ሜዳ ላይ ለመቆም እና ሌሎችንም አምልኮዎች ለመፈፀም መካን ማሰብና ወደርሷ መሄድ ሐጅ ይባላል። ሐጅ ከአምስቱ የኢስላም መሰረቶች አንዱ ነው። ከእስልምና መሆኑ እያንዳንዱ ሙስሊም ሊያውቀው የሚገባ የአምልኮ ዘርፍም ነው። ሐጅ ዋጂብ (ግዴታ) አይደለም ያለ ሰው ይከፍራል፤ ከእስልምና ይወጣል። ሐጅ ግዴታ የሆነው- እንደ አብዝሀ ልሂቆች (ጅምሁረል ዑለማ) አስተያየት- ከሒጅራ በኋላ ስድስተኛው አመት ላይ ነው።

ቱሩፋቱ

በብዙ ሐዲሶች ላይ ሐጅ የሚያስገኘውን ትርፍ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አብራርተዋል። ከእነዚህ መሀል ጥቂቱን እንይ፡-

1. አቡ ሁረይራ እንደዘገቡት፡-

سئل رسول اللّه صلى الله عليه وسلم، أي الأعمال أفضل ؟ قال: “إيمان بالله ورسوله”. قيل: ثمَّ ماذا ؟ قال: “ثم جهاد في سبيل الله”. قيل: ثم ماذا ؟ قال: “ثمَّ حَج مَبْرُور

“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ‘የትኛው ስራ በላጭ ነው?’ ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ‘በአላህ ማመን!’ ብለው መለሱ። ‘ከዚያስ?’ ተባሉ። ‘በአላህ መንገድ ላይ መታገል (ጂሀድ)’ አሉ። ‘ከዚያስ?’ አሏቸው። ‘መልካም ሐጅ!’ አሉ።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል))

መልካም ሐጅ (ሐጁን መብሩር) ማለት ሐጢያት ያልተቀላቀለው ሐጅ ነው።


(ص ) بلال مؤذن الرسول ኢትዮጵዊዉ ቢላል3094170876_c05639e5b4_b
የመልክተኛው ሙሀመድ (ሙአዚን)
ባሪያ
የእስልምና ሃይማኖት በአረብ ደሴት እየተባለ በሚታወቀው አካባቢ ከመመሰቱ በፊት የዓረቦች ሁኔታ ከእንሳት የተሻለ አልነበረም።
መብላት መጠጣት መደሰት ፤ ልጅን መግደል በተለይ ሴት ልጅ ስትወለድላቸው ወደፊት የነውር ሥራ ትሰራ ይሆናል በሚል ሳቢያ በቁሟ ከነህይወቷ ይቀብሯት ነበር። የህብረተሰቡ ሁኔታ ተልቁ ትንሹን የሚበላበት በዝሙትና በመጠጥ የተመረዘ የቁማር ጨዋታ የሰፈነበት በአላህ አንድነት ሳይሆን ለጣዖታት መገዛት ነበር።
የባሪያም ሥርዓት በዓረብ ደሴት ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የሰፈነ ነበር። ሰው እንደ እቃ ይሸጥ ይለወጥ ነበር። ባሪያ ማለትም የቆዳው ቀለም የጠቆረ ብቻ ሳይሆን ነጭም ቢሆን በጦርነትና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከተማረከ ባሪያ ነው የሚባለው።
ከእለታት አንድ ቀን ጌታ ኡመያህ ኢብን ኽሊፍ የተባለ የቁረይሽ ባላባት የሆነ ጥቁር ረጂም ቀጭን የሆነ ትከሻዎቹ ትናንሽ የሆኑ ፊቱ የገረጣ ፀጉሩ ችምችም ያለውን ባሪያ አስከትሎ ካእባ አካባቢ ሲደርስ ፍጥነቱን ቀንሶ ወደ ኋላው ዞር ብሎ <ቢላል የኛን ጐሳ ሸቀጣ ሸቀጥ በሙሉ ባንተ ሃላፊነት ወደ ምድረ ሻም (ሱሪያ) ወስደህ ባለፈው ጊዜ እንደ አደረገው ደህና ትርፍ እንድታስገኝልን ተስፍ እያደረኩኝ ካልተሳካልህ ግን<<<< ብሎ ጌታ ኢመያህ ንግ ግሩም ሳይጨርስ ቢላል ፈጠን ብሎ የኔ ጌታ አትጠራጠር አለው።
በአሁኑ ጉዞ ልጄ ዓሊ ካንተ ጋር አይሄድም። ስለዚህ ሃላፊነቱን ለብቻህ ነው የምትሸከመው ብሎት ጌታ ኡመያህ ወደ ካእባ አመራ። በዚህ ጊዜ ይቁረይሽ የተከበሩ ሰዎች ዙሪያ ክብ ተቀምጠው የጋለ ውይይት ይዘው ነበር። ኡመያም ወደ ባሪያው ዘወር በማለት ከፈለከኝ ከነዚህ ሰዎች ጋር ነው የምታገኘኝ ብሎ ከተከበሩ የቁረይሸ ሰዎች ጋር አብሮ ተቀመጠ።
በዚህ ጊዜ ቢላል ታላቁ የቁረትሾች አምላክ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ሁበል ዘንድ ገጸ በረከት ይዞ ወደካእባ አመራ።
ሁበል የተባለው ጣዖት ከወርቅ የተሰራ ነው። በሁለት እግሮቹ ሰባት የሚሽከረከሩ ጣሳዎች አሉት።
ቢላል ወደ ታላቁ ሁበል በደረሰበት ጊዜ ሁለት ሰዎች ማለት ባልና ሚስት ለፍርድ ቁመው ሚስቲቱ ልጅ ታቅፍ በብዙ ሰዎች ተከበው የሁበል ካህንም ጣሳዎችን እየመታ ፍርዱን ይጠባበቁ ነበር። ጉዳዩ ባል ሚስቱነ ስለተጠራጠረ ልጁ ከሱ አብራክ የወጣ መሆኑን ፍርዱን ለታላቁ ሁበል በያኔ እንዲሰጥበት ይጠይቃል
በዚህ ጊዜ በሚስት ፊት ይታይ የነበረው ጭንቀትና መረበሽ ግልፅ ነበር። ስለዚህ የሁበልን ውሳኔ ባልና ሚስት እንዲሁም በዚያ የነበረው ህዝብ በፍርሃትና በጉጉት ይጠባበቅ ነበር። የሁበል ውሳኔም ከሰባቱ ጣሳዎች ባንጉ ላይ ተፅፎ ወጣ ውሳኔው ወጣ።ውሳኔውም ሴቷንየሚገግፍ ልጂም ከአባቱ አብራክ የተከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ስለነበረ ሴትየዋ በጣም ደስ አላት። ወደ ባለቤቷ ጠጋ ብላ በጆሮው አየህ ታላቁ አምላክ ሁበል የመጨረሻውን ፍርድ በማያጠራጥር ሁኔታ በየነ፧ አለችው።
ከባልና ሚስት ፍርድ ብኋል የተሰበሰበው ህዝብ ወደመጣበት ተበታተና። ቢላል ግን ብቻውን ቀር። ፍርሃት በተሞላበት ሁኔታ ወደ ሁበል ካህን ጠጋ ብሎ ለአምላክ ሁበል የሚጋባወን ገፀ በረከት ካበረከተ በኋላ ፈገግ በማለት ይህቺን አነስተኛ ገፀ በረከት ለታላቁ አምላካችን ሁበል ሳበረክት ለረጅሙ ጉዞ ጥበቃውና ርህራሄው እንዳይለየን ተስፍ በማድረግ ነው። አለው ቢላል። ካህኑም ገፀ በረከቱን ከተቀበል በኋላ ጣሳዎችን መምታት ጀመረ። በዚህ ጊዜ ቢላል በፍርሃት ተዋጥ። እንደፈራውም ይሁበል ውሳኔ በጣሳዎቹ ባንዱ ላይ ተፅፎ ወጣ። ውሳኔውም በዛሬው እለት ጉዞ ማድረግ የለብህም። የሚል ነበር። የአምላክ ውሳኔ ቢላልን እጅግ አዽርጐ አሳዘነው ። ካህኑም የቢላልን ድንጋጤና መረበሽ ተመልክቶ ለምን እንደገና ለሁበል ሌላ ገፀ በረከት አታበረክትለትም ችግርህን ተመልክቶ ፍርዱን ያስተካክል ይሆናል አለው። ስለዚህ እንደተባልው አደረገ ጣሳዎች ከተሽከረከሩ በኋላ የተሳካ ጉዞ ይሁንልህ የሚል ፅሁፍ ወጣ ቢላልም ደስ እያለው ወደ ጌታው ኡመያህ ወደ አለበት ቦታ አመራ።

 

የቁረይሽ ነጋዴዎች በውይይት ላይ ሳሉ ቢላል አልፎ ሲሄድ ከነሱ ጋር እንዲቀመጥ ጠየቁት ። ተቀመጠ በዚህ ጊዜ አቡበከር ኢብን አቢ ቁሃፍ ድምፅህ እንዴት አስደሳች ነው ቢላል የጉዟችንን አሰልችነትና እርዝማኔ አስረሳን ፥ አሳጠረልን አለው።

 

كان النبي صلى الله عليه وسلم أحسن الناس خُلُقاً

የነብዩ ሱና የስነ-ምግባር እይታ፡-

ነብዩ /ሶ.ዐ.ወ/ የሚያስመሠግን ስነ-ምግባርን አበረታተውታል። አነስ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና በዘገቡት ሀዲስ፡-

كان النبي صلى الله عليه وسلم أحسن الناس خُلُقاً )متفق عليه(

ነብዩ /../ ከሁሉም የላቀ ስነምግባር የነበራቸው ነበሩ። (ቡኻሪና ሙስሊም)

ሃያልና አሸናፊው አላህ ነብዩን /ሶ.ዐ.ወ/ ሲያሞካሻቸው፡-

وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ [٦٨:٤]

አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ (አል-ቀለም፣ 4) ይላቸዋል።

አዒሻም አላህ ሥራዋን ይውደድላትና ስለ ነብዩ /ሶ.ዐ.ወ/ ሥነ-ምግባር ስትነግረን፡-

كان خلقه القرآن )رواه مسلم(

የነብዩ /../ ስነምግባራቸው ቁርኣን ነበር (ሙስሊም) ትለናለች።

ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ደግሞ ነብዩ /ሶ.ዐ.ወ/ ባልደረቦቻቸውን በመልካም ስነ-ምግባር እንዲታነፁ ጥሪ ሲያቀርቡላቸው ከመጥፎ ሥነ-ምግባር ደግሞ እንዲርቁም አስጠንቅዋቸዋል። የላቀ ሥነ-ምግባርን የተላበሡ ለሆኑት የላቀ ምንዳና በርካታ ትሩፋት እንደሚያገኙም ቃል ገብተውላቸዋል።

ቲርሚዚ ሀሠኑን ሠሂህ በሆነ ሀዲስ እንደዘገቡት ነብዩ /ሶ.ዐ.ወ/ ፡-

ما من شيء أثقل في ميزان المؤمن يوم القيامة من حسن الخلق، وإن الله يبغض الفاحش البذيَّ رواه الترمذي(

የቂያማ ቀን ምንም ነገር ሚዛን ላይ ከሥነምግባር የበለጠ የሚከብድ የለም፣ አላህ አፀያፊንና ብልግናን ይጠላል ይሉናል። (ቲርሚዚይ)::

ረሡል በአብዛኛው ሠዎችን ጀነት የሚያስገባ ተግባር ምን መሆኑን ተጠይቀው ሲመልሱ፡-

تقوى الله وحسن الخلق )رواه الترمذي(

የአላህ ፍራቻና መልካም ስነምግባር ነው ብለዋል። (ቲርሚዚይ)።

በበጎ ነገር ያዛል ፣ ከመጥፎ ይከለክላል

በበጎ ነገር ያዛል ፣ ከመጥፎ ይከለክላል
በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል የእዋ አስኳል ነው። እናም ዳኢ ሙስሊም በመልካም የሚያዝና ከመጥፎ የሚከለክል ነው። መጥፎን ነገር የሚችል ከሆነና ሌላ መጥፎ ነገር የማያስከትል ከሆነ በእጁ ይከላከላል። ካልቻለ በምላሱ እውነቱን ይገልጻል። መጥፎውን ያወግዳል። ይህም ካልሆነለት በቀልቡ ይጠላዋል። ከስሩ ነቅሎ ሊጥለው ይዘጋጃል፧ ተከታዩ የአላህ መልእተኛ (ሰአወ) ቃል የሚያሳያው ይህንኑ ነው፦
<መጥፎ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው። ካልቻለ በምላሱ ይቀይረው። ካልሆነለት በቀልቡ (ይጥላው) ይህ የመጨረሻው የእምነት ደረጃ ነው።> (ሙስሊም)
ሙስሊም በመልካም ሲያዝና ከመጥፎ ሲከለክል ለሙስሊሞች ታማኝ የመሆኑ አካል ነው።
ዲን ማለት ታማኝነት ነውና። ዲን ማልት ታማኝነት ከሆነ፣ መመካከር፣ምተባበረ ከሆነ በመለካም ማዘዝና ከመጥፎ መከለከል የግድ ነው። ይህ ሲሆነ ተከታዩ የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) ቃል ይረጋገጣል፦
<ዲን ማለት ታማኝነት (እና ምክክር) ነው።> አሉ ለማን ትበብለው ሲጠየቁ ለአላህ፣ ለመጽሀፍ፣ ለመልእክተኛው፣ ለሙስሊም መሪዎችና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ሲሉ ተናገሩ።
ይህ ባህሪ ሙስሊምን ከግፈኞች ፊት እውነትን ሳይፈራ እንዲናገር ያደረገዋል። የዚህ ኡምማ ህልውና የተመሰረተው በእንዲህ አይነት ጀግናና ነጻ ልጆቹ ነውና። በዳይን <አንተ ግፈኛ ነህ> ማለትን በማይፈሩ ጀግኖች። እንዲህ አይነት አባላትን ኡምማው ሲያጣ አብይ ባህሪውን አጥቷል። የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) እንዲህ ብለዋል፦
<ተከታዮቼ ግፈኛ ግፈኛ ነህ ላማለት ሲፈሩ ካየህ ከነርሱ ተሰናበት።>(አህመድ)
በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ወኔና ጀግንነትን የሚረጩ በርካታ ሀዲሳዊ መክእክቶች ተላልፈዋል። መሞትን ወይም በረሀብ መሰቃየትን ሳይፈሩ በድፍረት የእውነትን መልእክት እንዲያስተላልፍ የሚያነሳሱ መልእክቶች ሰፍረዋል። ጥቂቶችን እንመልከትእ፤ የአላህ መልእክተኛ(ሰአወ) እንዲህ ብለዋል፦
<ከናንተ አንዳጩ ሰዎችን መፍራት እውነትን ከመናገር አያግደው። ምክንያቱም እውነትን መናገር የመሞቻ ጊዜን አያቃርብም።>(ተርሚዚ)
አንድ ሰው ወደነቢዩ (ሰአወ)ዘንድ ሄደ። ሚንበር ላይ ነበሩ። < ከሰዎች መካከል መለካሙ የትኛው ነው፧ ሲል ጠየቃቸው። ይበልጥ አዋቂ፣ ይበልጥ አላህን ፈሪ፣ በጥሩ የሚያዝና ከመጥፎ የሚከለክል፣ እንዲሁም ዝምድናውን የሚቀጥል> አሉ።(አህመድና ጦበራኒ)
በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል በሙስሊሙ ህብረተሰብ ስንልቦና ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጽ በመደረጉ አባላቱ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ግፈኞችን ተጻርረው ድንቅ አቋሞችን እንዲይዙ አስቻላቸወ። እጅግ የሚያስደንቁ ጀግንነቶች ተስተዋሉ። አላህ ከፉን ነገር በዝምታ የሚያልፍ ፈሪዎችን ሳይሆን ጀግኖችን እንደሚረዳ የነኝህ ጀግኖች ድርጊት ምስክር ሆነ። የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ)እንዲህ ብለዋል፦
<ክብሩን በሚጎድልበት እና መብቱ በሚነካበት ሁኔታ ውስጥ ያለን ሙስሊም ያልረዳ የአላህን እገዛ በሚሻ ሰአት አላህ እገዛውን ይነፍገዋል። ክብሩ በሚጎድልበት እና መብቱ በሚነካበት ሁኔታ ውስጥ ያለን ሙስሊም የረዳ የአላህን እገዛ በሚሻ ሰአት አላህ ይረዳዋል።>(አህመድና አቡ ዳውድ)
እናም ሙስሊም ሀቅን ከመናገር ወደ ኋላ አይልም። ግፍ ሲስፍፍ፣ ጸያፍ ነገር ሲንሰራፍ በዝምታ አይመለከትም። መጥፎን ነገር ለመቀየር ሁሌም ይጥራል። እኩይን በዝምታ በመመልከት ከአላህ ዘንድ የሚመጣን ቅጣት ለመከላከል። አቡበከር ኸሊፍ በሆኑ ጊዜ ሚንበር ላይ ወጡና አላህን አመሰገኑ ። ከዚያም እንዲህ አሉ፦
<ሰዎች ሆይ፣<እናንተ ያመናችሁ ሆይ፣ እናንተ ከተቀናችሁ የጠመመ አይጎዳችሁም።> የሚለውን የቁአን አንቀጽ ታነባላችሁ። ያለቦታው እየተጠቀማችሁበት ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
<ሰዎች እኩይ ነገርን እያዩ ካልቀየሩት አላህ በቀጣቱ ያካብባቸዋል።>

القلب

ልብ
በሰውነታችን ውስጥ አንዲት ሙዳ ስጋ አለች። እርሳ ከተስተካከለች ሰውነት ሁሉ ይስተካከላል። እርሳ ከተበላሸች ሰውነት ሁሉ ይበላሻል። እሳም ልብ ናት ። ነቢዩ ሙሀመድ (ሶአወ) ቡዃሪና ሙስሊም

ልብ በስድስት ነገች ትበላሻለች
* ተውብት በመከጀል ኃጢያትን መዳፈር
* ኢልም(እውቀት) ኖሮት አለመተግበር
* ስራን ያለ ኢኸላስ መስራት
* የአላህን ሪዝቅ (ሲሳይ)እየበሉ አለማመስገን
* የአላህን ቀደር (ውሳንኔ) አለመውደድ
* የሞተን ሰው እየቀበሩ አማስተንተን።
ሙት ልብ

 • ይህ ልብ ለአላህ ትእዛዝ ዝግ የሆነ ነው። ይህ ልብ የአላህን ጸጋ ያላገናዘበ ነው። ይህ ልብ ከተንኮል፣ ከጥፍትና ከቨርክ ያልወጣ እንዲሁም ከምቀኝነት፣ ከሀሴት፣ ከንፍገት ልክፍት ያልጸዳ ነው።
 • ይህ የሙስሊም ቀልብ አይደለም። ለምን

ተግሳእን የማይቀበል ተመለስ ቢባል አሻፈረኝ የሚል በመሆኑ።
*በተገሰኡም ጊዜ አይመለሱም።*(አልሳፍት )

 • የአላህን ትእዛዝ ጥሶ የአላህን ቁጣና ቅጣት የሚጋብዝ፣በምድሪቱ የጥፉት ሰራዊት የሆነ፣ ለአላህ ትእዛዝ ያሞተ፣ በሰይጣናዊ ጉትጎታ ለነፍስያ ያጎበደደ ሞገደኛ ልብ ነው።
 • አራት ነገሮች ልብ ይገድላሉ
  * ከወንጀል በኃላ ወንጀልን ማስከተል
  *ማግባት ከሚፈቀድላት ተቃራኒ ፆታ (አጅነቢይ) ጋር አላስፈላጊ ንጝር ማብዛት
  *ከሞኝ ጋር መከራር
  *ከበድን (ከሽታም፣ ከበደለኛ) ጋር መቀመጥ
  የፈለከውን ያህል ኑር ሟች ነህ፥
  የፈለግኸውን ውደድ ትለየዋለህ፥
  የፈለግኸውን ስራ በሱ ትመነዳለህ ወይ ትቀጣለህ።