ሐጅ “الحج”

 

ሐጅ

የሐጅና የዑምራ ትሩፋት

ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፡

“… ለአላህም፣ በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ በሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፣ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡”

ነቢዩም (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል፡-

“የዑምራ ሥርዓተ ጻሎት እስከ ተከታዩ የዑምራ ሥርዓተ ጻሎት ድረስ በሁለቱ መካከል ላለው ኃጢአት ማበሻ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ኃጢአትና አመጽ (መዕስያ) የሌለበትና (ነቢዩ በፈጸሙት መሰረት) በትክክል የተፈጸመ ሥርዓተ ሐጅ ከገነት በስተቀር ሌላ ምንዳ የለውም፡፡”

“ተገቢ ያልሆነ መጥፎ ነገር ከአንደበቱ ሳይወጣና የአላህን ትዕዛዝ ምንም ሳይጥስ ሐጅ ያደረገ ሰው ልክ እናቱ እደወለደችዉ ቀን ከኃጢአቶቹ ጠርቶ ይመለሳል፡፡”

“የሐጅ ሥርዓተ ጻሎት ሕጎቻችሁን ከኔ ቅሰሙ፡፡”

ለደርሶ መልስ የሚበቃህ!ሙስሊም ወንደሜ ገንዘብ በኖረህ ጊዜ የሐጅ ግዴታህን ለማውረድ ተፋጠን፡፡
ከሐጅ መልስ ስላሉት እንደ ስጦታዎች ላሉት ወጪዎች ምንም ግምት አትሰጥ፡፡
አንዴ ደርሶ ለመመለስ ችሎታ ካገኘህ በኋላ ሊደርስብህ ስለሚችለው መሰናክል አላህ ምክንያት አይቀበልም ከመታመመምህ ከመደህየትህ ወይም የአላህን ትዕዛዝ ሳትፈጽም አመጸኛ ሆነህ ከመሞትህ በፊት ሐጅህን በፍጥነት ፈጽም፣ ሐጅ ከእስላም አበይት መስረቶች አንዱ ነውና፡፡ ለሐጅና ዑምራ ግዴታ መፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ሐጁ ከአላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ንጹሕ ሐላልና ከጠራ ሀብት የተገኘ መሆን አለበት፡፡
ሴት ለሐጅም ሆነ ለሌላ ጉዞ በጋብቻ መገናኘት ከማትችለው ዘመዷ ወይም ከባሏ (ከመህረም) ጋር ካልሆነ መሣፈር ሐራም (እርም) ነው፡፡
ይህም ቀጥሎ በተመለከተው የነቢዩ (ሰዐወ) ቃል መሠረት ነው፡-
“ሊያገባት የማይችል ዘመዷ ወይም ባልዋ ከሆነ ሰው ጋር ካልሆነች በሰተቀር ሴት ብቻዋን ለጉዞ አትሳፈርም፡፡”

ከተጣላሃቸው ሰዎች ታረቅ፣ ዕዳ ካለብህ ክፈል፣ ቤተሰቦችህ በጌጣጌጥ በመኪናዎች በጣፋጭ ምግቦች በእርድና በሌሎች ነገሮችም ብኩን እንዳይሆኑ ምከራቸው፣ ተናዘዝላቸው፡፡ ይህም ቀጥሎ ከሰፈረው የአላህ ቃል በመነሳት ነው
“.. ብሉም ጠጡም፣አታባክኑም” (አል-አዕራፍ (7)፡31)
ሐጅ ሙስሊሞች የሚተዋወቁት የሚዋደዱበት ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚረዳዱበት ዓለማዊም ሆኑ
ኃይማኖታዊ ጥቅሞችን የሚቀስሙበት ትልቅ ስብሰባ (ጉባኤ) ነው፡፡
ዋነኛው ነገር ችግሮችን መፍታት ለመቻል በአላህ ረድኤት መታገዝና እሱን ብቻ መማጸንና መገዛት ነው፡፡

አላህእንዲህ ብሏልና፡

“እኔ የምገዛው ጌታዬን ብቻ ነው፣ በርሱም አንድንም አላጋራም በል፡፡” (አል-ጂን (75)፡20)

የዑምራ ሥርዓተ-ጸሎት በማንኛውም ወቅት ሊፈጸም ሲችል በወርኃ ረመዳን ውስጥ መፈጸሙ ግን ቀጥሎ በተመለከተው ነቢያዊ ፈለግ መሰረት የበለጠ ይመረጣል፡-

“በወርኃ ረመዳን የተደረገ ዑምራ (ምንዳው) እንደ ሐጅ ይቆጠራል፡፡”

መካ በሚገኘው የተከበረው መስጊድ (መስጂደል-ሐራም) ውስጥ የሚሰገደው ሶላት ሌላ ቦታ ከሚሰገደው መቶ ሺህ ሶላት ይበልጣል፡፡ ነቢዩ (ሰዐወ) ይህን በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፡

“በዚህ መስጊድ ውስጥ የሚሰገደው ሶላት የተከበረው (የመካ) መስጂድ ብቻ ሲቀር ከተቀሩት ሌሎች መስጂዶች ውስጥ ከሚሰገደው መቶ ሺህ ሶላት ይበልጣል፡፡”

“በተከበረው መስጊድ የሚሰገድ አንድ ሶላት በዚህ መስጊድ (የመዲና መስጊድ ውስጥ ከሚሰገደው መቶ ሶላት ይበልጣል

የመጀመሪያው ዑምራ ተደርጎ ካበቃ በኋላ የሚፈጸመውና “ተመትቱዕ” በመባል የሚታወቀው የሐጅ አፈጻጸም ዓይነት እንዳያመልጥህ፡፡

ነቢዩ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋልና፡-

ከናንተ መሐል ሐጅ!“የሙሐመድ ቤተሰቦች ሆይ የሚያደርግ ሰው በሐጅ ውስጥ በዑምራ ይጀምር፡፡”

ሐጅ በማን ላይ ግዴታ ይሆናል

ሐጅ ከእስላም አበይት ማዕዘኖች አንዱ ሲሆን ግዴታ (ዋጅብ) የሚሆነው፡-

– ሙስሊም በሆነ ሰው፣
– አእምሮው ጤነኛ የሆነ፣ የአእምሮ በሽተኛ በሆነ እብድ ላይ ግዴታ አይሆንም፡፡
– ከባርነት ነፃ የሆነ ሰው፣ የሰው ተገዥ በሆነና ነፃነት በሌለው ሰው ላይ ግዴታ አይሆንም፡፡
– ላቅመ አዳም (ሔዋን) የደረሰና የደረሰች፣ በሕፃን ላይ ግዴታ አይሆንም፡፡ ሐጅ ካደረገም፣ በኋላ ሲያድግ ከግዴታው ነፃ አያደርገውም፡፡
– ጤነኛ የሆነ፣ በሽተኛ ሰው እስኪድን ድረስ ግዴታ አይሆንበትም፡
– የሀብት አቅሙ የሚፈቅድለት፣ ለሐጅ የሚያስፈልገው ገንዘብ በሌለው ድሀ ላይ ግዴታ አይሆንም፡፡
በዘመነ ሕይወት አንድ ጊዜ ብቻ፣ ከአንድ በላይ የማድረግ ግዴታ ባይኖርም ቢጨምር ምንዳውን ያገኛል፡፡
ሴት አብሮዋት የሚጓዝ ሙሕረም መገኘት፣ ሴት ባልዋ ወይም በጋብቻ ሊገናኛት የማይችል አንድ ዘመዷ አብሮዋት እንዲጓዝ ካልተገኘ ግዴታ አይሆንባትም፡፡ ነቢዩ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋልና፡-
‹ሊያገባት የማይችል ዘመዷ ወይም ባልዋ ከሆነ ሰው ጋር ካልሆነች በስተቀር ሴት ብቻዋን ለጉዞ አትሳፈርም፡፡›


الإسراء والمعراج

 

الإسراء والمعراج
አል-ኢስራእ ወል-ሚእራጅ

سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَى بِعَبْدِهِ لَيْلاً مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ
إِلَى الْمَسْجِدِ الأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
“ያ:ባሪያውን (ሙሃመድን) ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ:ዙርያውን ወደ ባርክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያገባው:: ከታምራቶቻችን ልናሳየው:(አስኼድንው)እነሆ: እሱ:(አላህ) ሰሚው:ተመልካቺው ነው::
(ሱረቱ አል-ኢስራእ ምእ:17 ቁ:1)
ኢስራእ:- ማልት ከመካ ወደ በይተልመቅደስ በሌሊት ያደረጉት ጉዞ ነው::
አል-ሚእራጅ:- ደግሞ ከበይተልመቅደስ ወደ ሰማይ የተፈፀመው ጉዞ ነው::
“የአላህ መለክተኛ (ሰ.አ.ወ)
ከመስጂደል ሃራም በአካላቸው በሌሊት ጉዞ በቡራቅ ላይ ከጅብሪል(አ.ስ) ጋር ሆነው በይተልመቅዲስ ደረሱና ከቡራቁ ወርደው ላለፉት ነብያት ኢማም ሆነው አሰገዱ::
ከዚህ በኋላ ወደ አንድኛው ሰማይ (ሰማአዱኒያ) እየተባለ ወደ ሚጠራው አረጉ:: ጅብሪል(አ.ሰ) በሩ እንዲከፈትላቸው ጠየቀና ተከፈተላቸው::
መጀመሪያ አባታችን አደምን አዩ:: ሰላምታ ሰጣቻው: አደምም ሰላምታውን መለሱ:: ነብይ መሆንህንም አረጋግጣለው አሉ:: በዚህ ጊዜ በስተቀኛቸው የቅንና ስኬታማ ሰዎችን ነፍስ: በስተግራ በኩል ደግሞ የእድለ ቢሶችንና የሀጢያተኞችን ነፍስ አላህ(ሱ.ወ) አሳያቸው::
  በዚህ አይነት ወደ ሰማይ በማረግ ቀጥለው በሁለተኛው ሰማይ ላይ የህያኢብን ዘከሪያና ኢሳ ኢብን መርየምን(አ.ሰ) አገኙ:: ነብዩ ሰላምታ አቀረቡ:: እነርሱም አፀፋውን መለሱ:: “እንኳን ደህና መጣህ” አሏቸው:: ነብይ እንደሆነ አረጋገጡላቸው:: ከሶስተኛው ሰማይ ላይ ነብዩላህ ዩሱፍን አዩ:: ነብዩ ሰላምታ አቀረቡ:: ዩሱፍም አፀፋውን መለሱ:: ወደ አራተኛው ሰማይ አረጉ ነብዩላህ ኢድሪስን አዩ:: ወደ አምስተኛው ሰማይ አረጉ: ነብዩላህ ሀሩንን አዩ:: ወደ ስድስተኛው ሰማይ አረጉ ነብዩላህ ሙሳን አገኑ:: ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.አ.ወ) ሙሳን አልፈው ወደ ሰባተኛው ሰማይ ሲሻገሩ ሙሳ አለቀሱ: የሚያለቅሱበትን  ምክንያት ሲጠየቁ “ከኔ በኋላ የተላኩ ጀነት የሚገቡ የርስዎ ኡመት ከኔ ኡመት በብዛት የሚበልጡ በመሆናቸው ነው ::የማለቅሰው” አሉ::
በመጨረሻም ወደ ሰባተኛው ሰማይ አረጉ: ነብዩላህ ኢብራሂምን አገኙ::
በዚህ ጉዟቸው ሁሉም ነብያት ሰላምታ እንዲሁም ነብዩ መሆናቸውን አረጋግጠውላቸዋል::
  በዚህ ታሪክ ጉዞ ሀምሳ ሶላት ግዴታ እንደተደረገባቸው ከአላህ (ሱ.ወ) ተገለፀላቸው:: ነብዩላህ ሙሳም “በቀን ስንት ሶላት አላህ አዘዘህ? ” ብለው ጠየቃቸው::”ሀምሳ ሶላት” አሉ ሙሳም “ያንተ ኡመት ደካማዎች ናቸውን በቀን ሀምሳ ሶላት መስገድ አይችሉም ስለዚህ ወደ ጌታህ ተመለስ እና ቀንስልኝ ብለህ ለምነው” አሉ-ሙሳ::
 ነብዩ ሙሀመድም (ሰ.አ.ወ)ትእዛዙ እንዲቀነስላቸው ጌታቸውን ተመልሰው ልመና ባቀረቡት መሰረት ከሀምሳ ሶላት በቀን ወደ አምስት ሶላት እንዲሆን ተደርጎ የአላህ ውሳኔ አረፈበት::”ውሳኔውን ሰጥ ለጥ ብየ በማክበር ተቀብየዋለሁ” አሉ::
በዚህ ጉዞ ላይ ብዙ ነገሮችን አይተዋል::
 የዚህ ጉዞ አላማ በተመላከተ የተነገረውን አጭርና ትልቅ መልክት “ተአምራታችንን ልናሳየው” የሚለውን የቁርአን መልእክት ነው:: አላህ(ሱ.ወ) በሁሉም ነብያት ላይ ተግባርዊ ያደረገው ህግ ነው::

በዲን (በሃይማኖት )ማስገደድ የለም!

በዲን (በሃይማኖት )ማስገደድ የለም!

እስላም ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ጥሪው በማስገደድ ላይ አልተመሰረተም: ጥላቶቹ እንደሚያስተጋቡት በሰይፍ አማካኝነት አልተስፍፍም:: እስላም የተስፍፍው ነፃ በሆነ መልኩ የሰውን ልጅ ወደ ቀናው መንገድ በመምራቱ ነው::የእምነቱ ጠላቶች እውነቱን ለማወቅ ቢሹ ኖሮ;ወይም ትክክላኛውን ነገር ለማግኘት ቢመራመሩ ኖሮ የምንለው ነገር እውነት መሆኑን ባወቁ ነበር::

   ነቢያችን(ሰ.አ.ወ)እንዲሁም በመጀመሪያ እምነቱን የተቀበሉት (ሰሃቦች) በሙሉ በቁሬሽ ካፊሮች ቁጣ ከፍተኛ ሲቃይ ደርሶባቸዋል:: ነቢዩ ከሰሃቦች ለከፊሉ ከነቤተሰቦቻቸው ወደ ኢትዩጵያ እንዲሰደዱ ፈቀዱላቸው::ይህንንም ያደረጉት ከቁሬሾች(በመካ ይኖሩ የነበሩ የአረብ ጐሳ ናቸው) ፍትህ የጎደለው ጥቃት በህይወታቸው ለማምለጥ እንዲችሉ ነው:: ሆኖም ሙሸሪኮች (ለአላህ አጋር የሚያደርጉት) ሰሃቦችን እንዲያባርሯቸውና እንዲይዙዋቸው :ኢትዩጵያም  ከደረሱ በኋላ ንጉሱ ዘንድ በመቅረብ እንዲመለሱ በማድረግ በአዲስ መልክ ሊያሰቃዩዋቸውና ከአባትና ከአያታቸው የመጣላቸውን ጣኦት የማምለክ እምነት ስለተው ሊበቀሉዋቸው ከሔዱበት የሚመልሱዋቸው ሰዎች ላኩባቸው::

  ይህንን ግልጽ የሆነና: የእስላም ጥሪ ታሪክ በግልጽ የሚያሰፍረው ተጨባጭ እውነታን እንዴት ይዘነጋሉ? የእስላም ታሪክ ነቢያችንና ሰሃቦች የቱን ያህል በቁሬሾች እጅ እንደተሰቃዩና ኑሮዋቸውን የምድር ላይ ገሃነም ያደረጉባቸው መሆኑን አላሳያቸውምን? ነቢዩበመስገድ ላይ እያሉ እላያቸው ላይ ትጥሉባቸው የነበረውን ቁሻሻ ረሱትን? ቢላልንና የታሲር ቤተሰቦችን በበረሃፀሃይ ቃጠሎ ዕርቃናቸውን አሸዋው ላይ በማስተኛት ደረታቸው ላይ ቋጥኝ ድንጋይ በመጫን ያሰቃናቸውን የነበረውን ረስተውታልን? ይህም ሆኖ የያሲር ቤተሰብ “ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ማለትን አላቋረጡም::በፈቃዳቸው ከተቀበሉት ሃይማኖት ሊቋቋሙት የማይችሉት ስቃይና መመራ ረሃብና የውሃ ጥም ቢያደርሱባችውም አልተመለሱም:: በዚህ አይነት ስቃት ላይ የያሲር ቤተሰብ እያለ የተመለከቱት ነቢይ “የያሲር ቤተሰብ ጥናቱን ይስጣችሁ: በርቱ: ዬናንተ ቀጠሮ(ቦታ) ገነት ነው ” ብለው ከማጽናናት በቀር ምንም ለማድረግ አልቻሉም::   

ለምድነው ይህን መሰል ኢሰብ አዊ የሆነ ስቃይ ያደረሱባቸው? ምክንያቱ ነቢዩ ከአላህ ዘንድ ያመጡት ዲን ትክክለኛ የማህበራዊ ኑሮን የሚመሰርት: የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ በማረም ከእምነት የልስሽነት ጨለማ ወደ ብሩህና ግልጽ የሆን እምነት የሚያሸጋግር በመሆኑ ነው::ዲኑ የአላህን አንድ መሆን በይፍ ገለጸ: ጣኦታቸውን አወገዘ: በህዝቦች መሃል ነጻነት እኩልነትና ፍትህ እንዲሰፍን አስተማረ: በማእረግና በጎሳ ላይ ተመርኩዞ መኩራትን አስቀረ: ሀብታም ከደሃ: አረብ የሆነው አረብ ካልሆነው አላህን በመፍራት ካልሆነ በቀር ብልጫ የማትኖረው መሆኑን አስተማረ:: ቁርአን በግልጽ ያሰፈረውን አንቀጽ እንጠቅሳለን;  

يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَى وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ

“እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ: እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ: አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው::”(ምእራፍ አል ሀጀራት ቁ.ር.13)

ለዚህም ነው ስልጣናቸውን የፈፈቸውን :ማእረጋቸውን ዝቅ ያድረገውንና ጣኦታቸውን የነቀፈውን ዲን ለመቀበል ቁረሾች እምቢተኛ የሆኑት::  በነብዩና በሰሃቦች ላይ ጥቃት ያደረሱትም በአጥቂነት ላይ ተመርኩዘው በበደል ያገኙትና ሲዝናኑበት የኖሩትን የበላይነት ለማቆየት ነው:: ስቃዩ እየበረታ ሲሄድ:ነቢዩ ወደ የስሪብ(መዲና) እንዲሄዱ ከአላህ በመፈቀዱ ተሰደዱ::አላህም በሚሰደዱበት እለት ቁሬሾች ተንኮልና ሌሊት ሊሰይፍዋቸው ከጠነሰሱት አድማ አዳናቸው::

” እሰላምን” መቀበል የግል ምርጫ ነው
አላህ ክብሩ ይስፍና”እስላም” ምን እንደሆንአ የርሰው ልጅ በነቢያትና በ መ ልክተኞች አማካኝነት እንዲያውቅ ካደረገ በሆላ አሰቀድሞ በዘረጋው ኖላን (እቅድ ) መሰረት ከፍጥረታት ሁሉ መርጦ በምያስበ አእምሮ የካነውን የሰው ልጅ የራሱን ምርጫ እንዲያደርግ ሙሉ ስልጣን ሰጠው ። የሰው ልጅ ከፈለገ “እሰላምን” ተቀብሎ በትክክለኛው ጎዳና እንዲመራና በመጪው ዓለም ወሮታውን እንዲያገኝ : ከፈለገም ” እሰላምን” ሳይቀበል ለፈጸመው በደል ተጠያቂ እንዲሆን ምርጫው የራሱ እንዲሆን ተደርጎዋል ። የመልክተኞች ሚና የአላህን መልክት ማድረስ: ማብራራት: ማስታወስ እና ማስጠንቀቅ እንጂ የሰው ልጅ ቀናውን መንገድ እንዲይዝ የሚያስገድዱ አይደሉም ። አላህ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል:

“በሐይማኖት ማስገደድ የለም: ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ:”(አል-በቀራ : ፪፭፮)
(በሀይማኖት ማስገደድ የሌለ ና “እስላም ” ያልተቀበሉትን ያላስገደደ መሆኑን ራሱን በቻለ ምዕራፍ እናቀርባለን።)
ከላይ እንደተገለጸው “እስላም ” ለእያንዳንዱ ሰው የተላከ ዲን ሆኖ ግለሰቡ አእምሮውን ተጠቅሞ በራሱ ፈቃድ ከወደደ የሚቀበለው እንጂ በጭፍን አባትና እናቱ የተቀበሉት እምነት ስለሆነ ብቻ የሚከተለው ወይም ያለፈቃዱ ተገዶ የሚቀበለው ዲን አለለሆኑ አንባቢ ሊገነዘበው ይችላል።
አላህ ክብሩ ይስፍና አንድ ሰው ቤተሰቡን ስለተቀበለው ብቻ አንድን እምነት የሚከተለውን ሰው አላዋቂነት ሲጠቁም እንዲህ ይላል:
“መጥፎንም ሥራ በሰሩ ጊዜ በርስዋ ላይ አባቶቻችንን አገኘን : አላህም በእርስዋ አዞናል ይላሉ: አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም: በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን ? በላቸው። “(አል-አእራፍ :28)

የዉዱዕ ትሩፍት ( فضل الوضوء)

የዉዱዕ ትሩፍት ( فضل الوضوء)
አቡ ሁረይራ (ረ አ ) እንዳሳተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሰ አ ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ፦ ”የኔ ሕዝቦች በቂያማ ቀን ፊታቸዉን፣ እጃቸዉና እግራቸዉ እያንፀባረቀ ነው የሚነሱት – ይህ የዉዱዕ ፍና ዉጤት ነው ። የሚንፀባረቅ አካሉን ለማስረዘም የፈለገ ፥ በትጋት ይፈጽም (ዉዱዕ ሲያደርግ በሚገባ ይፈትም።)”

የኢማን ጣዕም ( حلاوة الإيمان)

የኢማን ጣዕም ( حلاوة الإيمان)

አንስ (ረ ደ አ ) እንዳወሱት ነቢዩ (ስ አ ወ ) እንዲህ በለዋል ፦ “የሶስት ነገሮች ባለቤት የሆነ ሰው የእምነትን ጣዕም ያገኛል ። አላህንና መልክተኛውን ክሌላ ወገን ይበልጥ ከርሱ ዘንድ ተወዳጅ ያደረገ ሰውን የሚወድ (ገና ) የሚወደው ለአላህ ብቻ ሲል የሆነ ። እሳት ውስጥ መግባትን እንደሚጠላ ሁሉ ወደ ክህደት ውስጥ መመለስን ጠልቶ ሲገን ። ” <>

إطعام الطعام من الإسلام (ምግብ መለገስ የኢማን አካል ነው

አብደ ለህ ኢብን አምር (ር ደ አ ) እንዳስትላለፉት አንድ ግልሰበ የአላህን መልዕክትኛ ጠየቀ ። ” ከ ኢስላም (ስነ -ምግባራት ) የትኛው የበለተጠ (ዋጋ) ያስገኛል? ” በማለት ። እንዲህም አሉት ፦ “ምግብ መልገስ፤ ለምታውቀውም ሆነ ለማታውቀው ሰው ሰላምታ መስጠት።”

ዲን ገር ስለመሆኑ

ዲን ገር ስለመሆኑ
አቡ ሁረይራ (ረአ)እንዳወሱት ነብዩ ሙሐመድ(ሰአወ)እንዲህ ብለዋል:-“ዲን ገር ነዉ; አንድ ሰዉ በሃይማኖቱ (ክንዉን)ላይ ከአቅሙ በላይ ከተሸከመ በዚሁ ሁኔታ አይቀጥልም።ስለዚህ ጽንፈኛ አትሁኑ።ግን ወደ ፍጹምነት ለመቃረብ ስራችሁን በጥራት ለማከናወን ጥረት አድርጉ።ሽልማት የምታገኙ በመሆኑም ደስታ ይሰማችሁ።በጧትም ሆነ በማታ እንዲሁም በሌሊቱ የመጨረሻ ክፍል ጸሎት በማድረግ ታገዙ።(የአላህን እርዳታ ፈልጉ)።
ሰላት የኢማን ክፍል ነዉ
በራእ(ረአ)እንዳስተላለፉት ነብዩ ሙሐመድ (ሰአወ)በመዲና (ከተማ)ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉት የአንሷር(የመዲና ነዋሪዎች)ከነበሩት ከአያቶቻቸዉ ወይም ከአጎቶቻቸዉ(በእናታቸዉ በኩል) ቤት ነበር።ወደ በይተል መቅደስ(እየሩሳሌም)በመዞር ለአስራ ስድስት ወይም ለአስራ ሰባት ወራት ሰግደዋል።ነገር ግን ወደ ከዕባ(መካ)ዞረዉ መስገድ ይፈልጉ ነበር።ለመጀመሪያ ጊዜ (ወደ ከዕባ መዞር)የሰገዱት ሰላት የዓሱር ሰላት ነበር።ከእሳቸዉ ጋር የተወሰኑ ሰዎችም ሰግደዋል።አብረዉ ከሰገዱት ዉስጥ አንዱ ወጣና(ሄ ደ) ።በአንዱ መስጊድ አለፈ።ሰዎች ሩኩዕ ላይ ነበሩ(ወደ እየሩስ ዓለም ዞረዉ።) እንዲህ አላቸዉ :- “በአላህ ስም እምላለዉ ከአላህ መልዕክተኛ ጋር ወደ መካ በመዞር ሰግጃለዉ።” በቅጽበትም አቅጣጫችዉን ቀይሩ ።አያሁዶች (ነብዩ ሙሐመድ )ወደ በይተል መቅደስ (እየሩሳሌም) ዞረዉ በመስገዳቸዉ ደስተኛ ነበሩ።ፊታቸዉን ወደ ከእባ ማዞር ሲጀምሩ ግን ተቃዉሞአቸዉን አሰሙ።

እስላም ማለት ምን ይሆን?(ما هو الإسلام)

እስላም ማለት ምን ይሆን?

ይህ አርስት እስላምን ለተቀበለ አማኝ ብቻ ሳይሆን በሙስሊሞች አካባቢ ለሚኖሩ ወይም ስለ እስላም ለማወቅ ለሚሻ ሁሉ መሰረታዊ መሆኑ አያጠያይቅ ም።

1- እስሰ/ የአላህ መልእክተኞች ባስተማሩት ትምህርት(ዲን)መሐል ልዩነት ለምን ይታያል ?
በየዘመኑ የተላኩት የአላህ መልእክተኞች ያስተማሩት “እስላም”ነዉ፣ከተባለ በኋላ የግዴታ የሚነሳና መልስ ማግኘት የሚገባዉ ጥያቄ አለ።እርሱም ለአላህ መልዕክተኛ ሙሳ፣በተሰጠዉ መጽሐፍ “ተዉራት”(ኦሪት)ለአላህ መልዕክተኛ ዳዉድ በተሰጠዉ መጽሐፍ “ዘቡር”(መዝሙረ ዳዊት)፣ለአላህ መልዕክተኛ ኢሳ፣በተሰጠዉ መጽሐፍ”ኢንጅል”(ወንግየል)እንዲሁም ለአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ በተሰጠዉ መጽሐፍ”ቁርአን”(ቅዱስ ቁርአን)መሐል ልዩነት ስለሚታይና በእምነቱ ተከታዮች መሐልም ልዩነት ስለሚታይ፣ይህ ልዩነት እንዴት ሊከሰት ቻለ?የሚል ነዉ።
የዚህ ጥያቄ መልስ የሚከተሉት ነጥቦች ያቀፈ ይሆናል።
1ኛ/ ማንኛዉም የአላህ መልዕክተኛ የተላከዉ የሰዉ ልጅ አንድን አምላክ ብቻ እንዲያምንና ኢባዳ እንዲያደርግ (እንዲያመልክ)መሆኑን፣
2 ኛ/ ከሙሀመድ በፊት የተላኩ መልዕክተኞች ለሕዝባቸዉ በቀጥታ የተላኩ ሲሆን፣ነብዩ ሙሐመድ ግን ለዓለም ሕዝብ በሙሉ መሆኑን፣
3 ኛ/ መልዕክተኞች የተላኩላቸዉ መጽሐፍ የወረደላቸዉ ህዝቦች መሐል የተፈጠረዉ ልዩነት መጽሐፍ ከወረደ በኋላ እርስ በእርስ በፈጠሩት አለመግባባትና ምቀኝነት ምክንያት መሆኑን፣
4 ኛ/ የተላከዉ ዲን በሰዎች መሐል ፍቅርን የሚመሰርትና ሰዎች በጥል ምክንያት እንዳይራራቁ የሚያስተምር መሆኑን፣
5 ኛ/ እያንዳንዱ ነብይ የተላከለት ሕዝብ በዘመኑ የነበረበትን አስከፊና አስነዋሪ ሁኔታ
እንዲያዉቀዉ እንዲያስተምረዉና እንዲያስወግድለት ሲሆን እንደ ህብረተሰቡ የስልጣኔና የእድገት ደረጃ ለሁኔታዉ ምቹ የሆነ አስተዳደርና ማህበራዊ ጉዳይን የሚመለከቱ ደንቦች በማስፈለጋችዉ በዲን የሚመጡ ደንቦችም እያደጉ የመጡ መሆኑን፣
6ኛ/ ቁርአን ከአላህ ዘንድ ከተላኩት መጽሐፎች መሐል ከሌሎቹ በኋላ በመጨረሻዉ መልዕክተኛ አማካኝነት የተላከ በመሆኑ ይዘቱ የተምላና
አጠቃላይ የሆነ ባህርይ ያለዉ መሆኑን፣
ላም የሚለዉ ቃል ከቋንቋ አንጻር ሲታይ ከአረበኛ ቃል ” ሰሊመ”ከሚለዉ ግስ የመነጨ መሆኑ ይታወቃል።

እስላም ማለት ምን ይሆን?

ትርጉሙም;- ሀ/ ግልጽ ከሆነ ወይም ከተደበቀ ጭንቅ ወይም ችግር መከራ ነጻ ወጣ ማለት ይሆናል።እንዲሁም

ለ/በተጣሉ ወገኖች መሐል እርቅና ሰላም ወረደ ማለት ይሆናል፣እንዲሁም

ሐ/ ራስን ለፈቃድ ማስገዛት ማለትም ይሆናል ።

“ሰሊመ”የ ሚለዉ ቃል ይህንን ሶስት ትርጉም ያጠቃለለ ነዉ።ከዚህም ቃል እስላም የሚለዉ መጠሪያ ስም ሊመነጭ ይችላል።እስላም የሚለዉ መጠሪያ ለነቢዩ ሙሐመድ ሃይማኖት(ዲን)መለያ በማድረግ መላዉ ዓለም ሲጠቀምበት ይታያል።ይህ ሁኔታ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ለማወቅ ያህል እንዲረዳ መግለጹ ጠቃሚ ነዉ።እስላም የሚለዉ መጠሪያ አላህ ሙሐመድ ላስተማሩት ሃይማኖት(ዲን)መጠሪያ እንዲሆን የመረጠዉ መሆኑን ከሚጠቁሙ የቁርአን አያቶች(አንቀጾች)አ ንዱን እንጠቅሳለን።

الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الإِسْلامَ دِينًا'(سورة المائدة ۳)

(ዛሬሃይማኖታችሁን ለናንት ሞላሁላችሁ፣ጸጋዩንም በናንተ ላይ ፈጸምቁ፣ለእናንተም እስልምናን፣ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ።( ሱረቱል ማኢዳዕ 3

ለዚህ አላህ ክብሩ ይስፋና ለነብዩ ሙሐመድ ተከታዮች”እስላም”ሃይማኖት(ዲን)እንዲሆናችዉ በመምረጡ ለሃይማኖቱ መጠሪያ ቃሉ ጸደቀ ማለት ነዉ።በዚህ አይነት የመጣዉና ለዲኑ መጠሪያ የሆነዉ “እስላም” የሚለዉ ቃል ከቋንቋ አንጻር ብቻ ሳይሆን በዲኑ በ ኩል ያለዉን ትርጉም ማየቱ እጅግ ጠቃሚ ይሆናል።

በዲኑ ወይም በሸርያዉ አንጻር “እስላም”ማለት ትርጉሙ አላህ ከራሱ በቀር ሌላ ሸሪክ(አጋር)የሌለዉ መሆኑን አምኖ መቀበልን፣ይህንንም ተገንዝቦ በሙሉ ልብና ቆራጥነት ለእርሱ መገዛትና መታዘዝን ፣ከአላህ ዘንድ የተላኩትን ዲኖች መቀበልና በየዘመኑ ከአላህ ተልኮ ተግባራዊነት ባለዉ ዲን በፍፁም መመራት ማለት ይሆናል።

2- ዲን ወይም”የእስላም”ትምህርት

በየዘመናቱና በየሀገሩ አላህ ለሕዝቦች ነቢያትን መላኩን ከታሪክ እንማራለን።አላህ ነቢያትን የሚልክበት ዋናዉ ምክንያት ለምእምናኑ የአላህ ፈቃድ ምን እንደሆነ እንዲያስተምሩ ና ምእመኑ ከተማሩ በኃላ ለአላህ ፈቃድ ራሱን እንዲያስገዛና እንዲታዘዝ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ነዉ።ከዚህ ዉጭ አላህ ነብያትን የሚልክበት ምንም ምክንያት አይኖርም ።

ይህ መሰረተ ሃሳብ አምነን ከተቀበልን በቀላሉ ዲን “እስላም”መሆኑን ከቃሉ ትርጉምና ከመጡለት (ከተላኩለት)ምክንያትም አንጻር እንረዳለን፣ከዚህ በትክክለኛ አስተሳሰብ ከተደረሰበት መደምደሚያ ባሻገር ነቢያት በሙሉ ያስተማሩት ዲን እስላም ለመሆኑ ከቁርአን አንዳንድ አንቀጾችንመጥቀስ ይጠቅማል።

ሀ/የአላህ መልእተኛ ኑህ እንዲህ ብለዋል፣

وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِينَ “(سورة يونس ٧۲)

ከእስላሞች እንድሆን ታዝዣለሁ።ሱረቱል የኑስ ቁ 72 -“

ለ/የአላህ መልእተኛ ኢብራሂም እንዲህ ብለዋል፣

إِذْ قَالَ لَهُ رَبُّهُ أَسْلِمْ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ (سورة البقرة آية۱٣۱)

“ጌታዉ ለርሱ ታዘዝ ባለዉ ጊዜ (መ ረጠዉ )፣ለአለማት ጌታ ታዘዝኩ አለ።”(ሱረቱ አል-በቀራ ቁ 131 )

ሐ/የአላህ መልእተኛ ዩሱፍ እንዲህ ብለዋል፣

أَنتَ وَلِيِّي فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ( سورة يوسف آية ۱۰۱ )

” አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቱ ነህ ፣እስላም ሆኘ ግደለኝ፣በመልካሞቹም አስጠጋን፣(ሱረቱ ዩሱፍ ቁ 101 )

መ/ የአላህ መልእተኛ ሙሳ እንዲህ ብለዋል፣

يَا قَوْمِ إِن كُنتُمْ آمَنتُم بِاللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُواْ إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ (سورة يونس آية ٨٤)

(ህዝቦቼ ሆይ በአላህ አምናችሁ እንደሆነ፣በርሱ ላይ ተጠጉ ታዛዦች እንደሆናችሁ(በአላህ ላይ ትመካላችሁሱረቱል የኑስ ቁ 84

ሠ/ የአላህ መልእተኛ ኢሳ እንዲህ ብለዋል፣

فَلَمَّا أَحَسَّ عِيسَى مِنْهُمُ الْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِي إِلَى اللَّهِ قَالَ الْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ اللَّهِ آمَنَّا بِاللَّهِ وَاشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ(سورة العمران ۵۲)

ኢሳ ከነርሱ ክህደት በተሰማዉ ጊዜ ወደ አላህ ተጨምረዉ ረዳቶች እነማን ናችዉ ።አለ ፣ሐዋርያት እና የአላህ ሃይማኖት ረዳቶች አላህ አምነናል፣እናም ትክክለኛ ታዛዦች መሆናችንን መስክር አሉ።(ሱረቱ አል

ረ/ አላህ ስለመልክተኛዉ ሙሐመድ እንዲህ ብሎዋል፣

إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَى نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ وَأَوْحَيْنَا إِلَى إِبْرَاهِيمَ (سورة النساء آية ۱٦٣)

እኛ ወደ ኑህና ከርሱ በኃላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ፣ወደ አንተም አወረድን ፣ወደ ኢብራሂም፣ወደ —(ሱረቱ አንሳህ ቁ 163 )

እነዘህ አንቀቶች በሙሉ ቀደም ስል በትክክለኛዉ አስተሳሰብ ከደረስንበት መደምደሚያ በመነሳት አላህ የምልካችዉ መልእክተኞች የእርሱን ፈቃድ የሚያስተምሩና የሰዉ ልጅ ለአላህ ፈቃድ ራሱን ተገዥ እንዲያደርግ የሚመሩ ስለሆን ያስተማሩት ዲን”እስላም”ነዉ፣ያልነዉ በቁራን አላህን

ያረጋገጠዉ መሆኑን ያስረዱናል።

ሰ/ የአላህ መልእክተኞች ባስተማሩት ትምህርት(ዲን)መሐል ልዩነት ለምን ይታያል ?
በየዘመኑ የተላኩት የአላህ መልእክተኞች ያስተማሩት “እስላም”ነዉ፣ከተባለ በኋላ የግዴታ የሚነሳና መልስ ማግኘት የሚገባዉ ጥያቄ አለ።እርሱም ለአላህ መልዕክተኛ ሙሳ፣በተሰጠዉ መጽሐፍ “ተዉራት”(ኦሪት)ለአላህ መልዕክተኛ ዳዉድ በተሰጠዉ መጽሐፍ “ዘቡር”(መዝሙረ ዳዊት)፣ለአላህ መልዕክተኛ ኢሳ፣በተሰጠዉ መጽሐፍ”ኢንጅል”(ወንግየል)እንዲሁም ለአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ በተሰጠዉ መጽሐፍ”ቁርአን”(ቅዱስ ቁርአን)መሐል ልዩነት ስለሚታይና በእምነቱ ተከታዮች መሐልም ልዩነት ስለሚታይ፣ይህ ልዩነት እንዴት ሊከሰት ቻለ?የሚል ነዉ።
የዚህ ጥያቄ መልስ የሚከተሉት ነጥቦች ያቀፈ ይሆናል።
1ኛ/ ማንኛዉም የአላህ መልዕክተኛ የተላከዉ የሰዉ ልጅ አንድን አምላክ ብቻ እንዲያምንና ኢባዳ እንዲያደርግ (እንዲያመልክ)መሆኑን፣
2 ኛ/ ከሙሀመድ በፊት የተላኩ መልዕክተኞች ለሕዝባቸዉ በቀጥታ የተላኩ ሲሆን፣ነብዩ ሙሐመድ ግን ለዓለም ሕዝብ በሙሉ መሆኑን፣
3 ኛ/ መልዕክተኞች የተላኩላቸዉ መጽሐፍ የወረደላቸዉ ህዝቦች መሐል የተፈጠረዉ ልዩነት መጽሐፍ ከወረደ በኋላ እርስ በእርስ በፈጠሩት አለመግባባትና ምቀኝነት ምክንያት መሆኑን፣
4 ኛ/ የተላከዉ ዲን በሰዎች መሐል ፍቅርን የሚመሰርትና ሰዎች በጥል ምክንያት እንዳይራራቁ የሚያስተምር መሆኑን፣
5 ኛ/ እያንዳንዱ ነብይ የተላከለት ሕዝብ በዘመኑ የነበረበትን አስከፊና አስነዋሪ ሁኔታ
እንዲያዉቀዉ እንዲያስተምረዉና እንዲያስወግድለት ሲሆን እንደ ህብረተሰቡ የስልጣኔና የእድገት ደረጃ ለሁኔታዉ ምቹ የሆነ አስተዳደርና ማህበራዊ ጉዳይን የሚመለከቱ ደንቦች በማስፈለጋችዉ በዲን የሚመጡ ደንቦችም እያደጉ የመጡ መሆኑን፣
6ኛ/ ቁርአን ከአላህ ዘንድ ከተላኩት መጽሐፎች መሐል ከሌሎቹ በኋላ በመጨረሻዉ መልዕክተኛ አማካኝነት የተላከ በመሆኑ ይዘቱ የተምላና
አጠቃላይ የሆነ ባህርይ ያለዉ መሆኑን፣

فضل الذكر (የዚክር) ጥቅሞች

ዚክር (ذكر)
አላህን ማሰታወሰ (የዚክር) ጥቅሞች
– ዚክር ሰይጣንን ያባርራል ;ኃይሉንም ያዳክማል
– አላህን የስድሰታል ።
– የአእምሮን ስጋትና ጭንቀት ያስወግዳል።
– በልብ ዉስጥ ደስታን (ፍስሃን)ይፈጥራል።
– ለአካልና ለአእምሮ ብርታትን ይሰጥጣል ።
– ፊትንና ቀልብን ያጠራል (ይወለዉላል) ።
– ለሲሳይ መሰፋት ምክንያት ይሆናል ።
– ለዛንና ክብርን ያጎናፅፋል ።
“መልካም ሥራ መስራት የመንፈስ እርካታ እንደሚሰጥ ሁሉ በአንፃሩም
መጥፎ የሆነ ተግባር የህሊናእሾህ ሆኖ በየሄደበት የኮሰኩሳል።”
– የ አላህን ዉዴታ ይጨምራል።
– ቀልብን ያለመልማል።
– ከአላህ ቁጣ የመዳኛ ሰበብ ይሆናል።
– በዚክር የተጠመደ ሰዉ በመልአኮች የታጀበ ሲሆን ሰላምና ምህረት በእሱነቱ ላይ ይክሰፍናል።
– አላህን ማወደስ(ማጥራት) የገነት አትክልቶች እንዲያብቡ ይረዳል።
– ዛክሩን የቂያማ ቅርብነትና የዓለማዊዉን ሕይወት ርካሽነት እንዲገነዘብ ያደረገዋል።
– ያአልጠግብ ባይነትና የመርሳት ፀባይን ከቀልብ ላይ ይፍቃል ።
– ትርፍ ሶላትና ሌሎች ግድይታ ያልሆኑ ዒባዳዎችን ይተካል ።
– ዚክር ለማንኛዉም አይነት ችግር መፍትሔና ለጐደሎነት ስሜት መድህን ነዉ ።
የሐሳብ ሸክምን ያቃልላል፣የመረበሽ ስሜትን ያስወግዳል።
– ዚክር የቀልብ ዉስጥ ፍርሐትን ይበትናል፣የዚክር ብዛት ከፍርሐት ነፃ የመሆንን ሐይል ይጨምራል ።
-ዚክርን የሚያዘወትሩ በዚህች ዓለም ፊታቸዉ የፈካ ሲሆን በወዲያኛዉ ዓለምም ልዩ ብርሐንን ይጎናፀፋሉ።